Tender Detail

Tender Details


በደ/ምዕ/ኢት/ህ/ክልላዊ/መንግስት በከፋ ዞን የገዋታ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት የሴክተር መ/ቤቶችን የሥራ እንቅስቃሴ ለማስፈጸም የሚያስፈልጉ የተለያዩ ዕቃዎችና አገልግሎቶች የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎችን በሎት የተዘረዘሩትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ካፋ ዞን ገዋታ ወረዳ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 01/2019 ዓ.ም

በደ/ምዕ/ኢት/ህ/ክልላዊ/መንግስት በከፋ ዞን የገዋታ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት የሴክተር መ/ቤቶችን የሥራ እንቅስቃሴ ለማስፈጸም የሚያስፈልጉ የተለያዩ ዕቃዎችና አገልግሎቶች የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎችን በሎት የተዘረዘሩትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት
ሎት 1 የጽህፈት መሣሪያዎችና የፅዳት ዕቃዎች
ሎት 2 የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
ሎት 3 የእንስሳት መድሐኒት እና የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች
ሎት 4 የህንፃ መሣሪያዎች
ሎት 5 የውሃ ግንባታ ዕቃዎችና የተለያዩ የውሃ ቧንቧ መለዋወጫ ዕቃዎች
ሎት 6 ፈርኒቸርና የቢሮ ዕቃዎች
ሎት 7 የመኪና ጥገና፣ የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎችና ቅባቶች
በመሆኑም በዚህ ጨረታ መሳተፍ የሚፈልግና በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ።

  1. ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የ2019 በጀት ዓመት ተፈጻሚ የሆነ የግብር ከፋይ ማጣሪያ ሰርተፍኬት (Tax Clearance)፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ወይም ሌላ ተፈጻሚ የታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማስረጃ ኮፒዎችን ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችሉ፣
  2. የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ገንዘብ የማይመለስ ለሎት 01 [የዋጋው ክፍል በፎቶው በግልጽ አይነበብም] መቶ ሃምሳ ብር/፣ ለሎት 04 500/አምስት መቶ ብር/፣ ለሎት 02 እና ለሎት 03 ብር 350/ሦስት መቶ ሃምሳ ብር/ እና ሎት 06 ብር 250/ሁለት መቶ ሃምሳ ብር/፣ ለሎት 05 እና ሎት 07 ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ ብቻ እያንዳንዱ ሰነድ በመክፈል ከገዋታ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ከግዥና ን/አስ/ር/የስራ ሂደት በሥራ ሰዓት በተዘጋጀው ቅፅ ስምና የድርጅተን ስም እያስመዘገቡ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእንዳንዱ ሰነድ ለሎት 01፣ 03 እና 04 ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር)፣ ለሎት 2 ብር 40,000/አርባ ሺህ ብር/፣ ለሎት 05፣ 06 እና 07 ብር 35,000/ ሰላሳ አምስት ሺህ ብር በባንክ ክፍያ ትዕዛዝ /CPO/ ብቻ ለእያንዳንዱ ሎት በጨረታ ማስታወቂያ መሰረት ማስያዝ የሚችሉ ጥሬ ገንዘብ የጨረታ ማስከበሪያ ማቅረብ አይፈቀድም። ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያውን በተገለጸው መጠንና መንገድ ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን፣የማስከበሪያው ትክክለኛነትና የሚቆይበት ጊዜ በጨረታ ሰነዱና በተፈጻሚው የግዥ መመሪያ መሰረት ይወሰናል፡፡
  4. ተጫራቾች በአንድ ወይም ከአንድ በላይ ሎቶች መወዳደር የሚችሉ ሲሆን፤ ከሥራ ፍቃዳቸዉና ከተማጅ ፍቃድ ውጭ መወዳደር የተከለከለና በሕጉ መሠረት ከመንግሥት ግዥ ተሳትፎ ያልታገዱ መሆን አለባቸው፡፡ ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያ ላይ በተጠየቀው የዕቃ አይነትና ዝርዝር መሰረት ጥራቱን በጠበቀ ሁኔታና በጥንቃቄ ከነቫት ተሞልቶ በእያንዳንዱ ገጽ ላይ ህጋዊ የድርጅቱን ማህተም፣ ፊርማና ስልክ ቁጥር ተደርጎ አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ ተለይቶ በአግባቡ በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ የጨረታውን አይነት በግልፅ በኤንቨሎፕ ላይ በመፃፍ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ጨረታውን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 21 በሥራ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት በ22ኛ የሥራ ቀን ላይ ከሰዓት በኋላ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች/ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን በ22ኛ ቀን በዓል /ሰንበት/ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከሰዓት በኋላ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በ8፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎች በጨረታው መከፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ ባይገኙም በህጉና በጨረታ ሰነዱ መሰረት ያለመገኘት የጨረታ መክፈቻ ሂደቱ አያስተጓጉልም፡፡
  6. የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸፈበትን ዕቃ በራሱ ወጪ ትራንስፖርትና መጓጓዣ ችለዉ ዕቃውን እስከ ገዋታ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ማቅረብ የሚችሉ፡፡ አሸናፊው ተጫራች የውል ማስከበሪያ ከውሉ ጠቅላላ ዋጋ 10% (አሥር በመቶ) CPO በሚሆን መጠን፣ በተፈጻሚው የግዥ መመሪያና በጨረታ ሰነዱ በተፈቀደው መልኩ ማቅረብ አለበት።
  7. መ/ቤቱ ሕጋዊ ምክንያትና የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ - ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 09111053990/0917686362

በደ/ምዕ/ኢት/ህ/ክልላዊ መንግስት በከፋ ዞን የገዋታ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Gewata Woreda Finance Office seeks bidders for various goods and services in 7 lots: stationery and cleaning supplies, electronics, veterinary drugs and medical equipment, construction tools, water construction materials and pipe fittings, furniture and office supplies, and vehicle maintenance, spare parts and lubricants. Bidders need a valid business license, tax clearance, TIN and VAT registration.
Save Tender