Tender Detail

Tender Details

  • Company የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግስት ፋይናንስ ቢሮ
  • Address ቦንጋ ፡ ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0473312555
  • Website
  • Deadline12 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceለእያንዳንዱ ሎት ብር 500.00 (የማይመለስ)
  • Bid Securityሎት 1 ብር 100,000፤ ሎት 2፣3 እና 4 ለእያንዳንዳቸው ብር 50,000 (CPO)
  • opening dateበዕለቱ 4:30 ሠዓት
  • Categories Cleaning & Janitorial , 3- Wheel Vehicle, Motorcycles And Bicycles , Stationery Materials , Electronics Materials

የኤሌክትሮኒክስ፣ ጽሕፈት መሳሪያ፣ ጽዳት ዕቃዎች እና ሞተር ሳይክሎች ግዥ (4 ሎት፣ 001/2019) - የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግስት ፋይናንስ ቢሮ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግስት ፋይናንስ ቢሮ


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ደ/ም/ኢ/ሕ/ክ/መንግስት ፋይናንስ ቢሮ 001/2019

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ፋይናንስ ቢሮ በ2019 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ቋሚና አላቂ ዕቃዎችን ማለትም፡
ሎት 1 ኤሌክትሮኒክስ እና ተዛመጅ ዕቃዎች
ሎት 2 የጽሕፈት መሳሪያዎች
ሎት 3 የጽዳት ዕቃዎች
ሎት 4 ሞተር ሳይክሎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
በዚሁ መሠረት በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ማናቸውም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች አሟልተው መገኘት አለባቸው።

  1. በመስኩ ሆኖ የዘመኑን ንግድ ፈቃድ ያሳደሱ፣የግብር ከፋይነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነትና የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  2. ተጫራቾች በሚወዳደሩባቸው መስኮች ከ2017 ዓ.ም ወዲህ ቢያንስ አንድ ዙር በመንግስት ግዥ ላይ በመሳተፍ በገቡት ውል መሠረት ስለማቅረባቸው የመልካም ሥራ አፈጻጸም ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ሆኖም አዲስ የንግድ ፈቃድ ያለቸው አይገደዱም።
  3. የጽሕፈት መሳሪያዎችን አላቂ ዕቃዎችንና የተለያዩ ቀለሞችን የሚያቀርቡ ተጫራቾች የዕቃዎችን ናሙና ጨረታው በሚታሸግበት ዕለት ከጠዋቱ 3፡00 ሠዓት ላይ ስለትክክለኛነቱ አረጋግጦ ለመ/ቤቱ ማስረከብ ይኖርባቸዋል።
  4. ተጨራቾች ዋጋ የተሞላበትን ኦሪጅናልና ኮፒ በመለየት ፊርማና የድርጅቱን ማህተም በእያንዳንዱ ገጽ ላይ በማሳረፍና በፖስታ በማሸግ ጨረታው ይፋ ከተደረገበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታ ማሸጊያ ሰዓት ድረስ በክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 7 ለዚሁ ዓላማ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ የማይመለስ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ የባንክ ሒሳብ ቁጥር 1000454348471 ላይ ገቢ በማድረግና ደረሰኙን በማቅረብ የጨረታውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።
  6. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ይፋ ከተደረገበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሠዓት ላይ ታሽጎ በዕለቱ በ4፡30 ሠዓት ላይ ተጨራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል። 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የመንግስት ሥራ ቀን ይከፈታል፡
  7. የጨረታ አሸናፊ የሆነ ተጫራች በራሱ ወጪ አጓጉዞ በቦንጋ ማዕከል በሚገው ፋይናንስ ቢሮ ዕቃዎችን አስመርምሮ ስለትክክለኛነቱ በማረጋገጥ ማስረከብ አለበት።
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማሰከበሪያ ለሎት 1 ብር 100,000.00/አንድ መቶ ሺህ ብር ለሎት 2 ለሎት3 እና ለሎት 4 ለእያንዳንዳቸው ብር 50,000.00 ሃምሳ ሺህ ብር በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ CPO ማቅረብ አለባቸው፡፡
  9. ጨረታውን ያሸነፈ አሸናፊ የውል ማስከበሪያ የውሉን 10% አስር ፐርሰንት ማስያዝ አለበት
  10. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ማሳሰቢያ፡ ማንኛውም በጨረታው ላይ የሚነሱ ጥያቄዎች ሲያጋጥሙ በስልክ ቁጥር 0473311188 መጠየቅ ይችላሉ።

የደ/ም/ኢ/ሕ/ክ/መንግስት ፋይናንስ ቢሮ

✨ messages.ai_summary
South West Ethiopia Peoples' Region Finance Bureau seeks suppliers for office goods in four lots: electronics, stationery, cleaning supplies, and motorcycles. Bidders need a valid trade license, tax registration, VAT registration, and supplier certificate; new licensees are exempt from the prior government contract performance requirement. Stationery/consumables bidders must submit samples.
Save Tender