Tender Detail

Tender Details

  • Company Tsedey Bank S.C. (ፀደይ ባንክ አ.ማ)
  • Address ሰንጋተራ አካባቢ በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት ህንጻ 16ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 09 ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0115584896
  • Websitehttps://tsedeybank-sc.com/
  • Deadline11 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineሪፖርተር
  • Bid Document Price500(አምስት መቶ ብር)
  • Bid Securityየአጠቃላይ ዋጋውን 2% ወይም የአጠቃላይ ዋጋው 2% ከብር 500,000.00 የሚበልጥ ከሆነ ብር 500,000.00 በሲፒኦ /CPO/ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ የ90 ቀን
  • opening dateጨረታው በተዘጋበት ዕለት በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ 4:30
  • Categories Audio Visual, Photography And Filming Service And Equipment , Building Construction , Camera

ፀደይ ባንክ አ.ማ ከስር የተዘረዘሩትን ዕቃዎች/ስራዎች/አገልግሎቶች ፈቃድ ያላቸውን ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት/ማሰራት ይፈልጋል::

Tsedey Bank S.C. (ፀደይ ባንክ አ.ማ)


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ብ/ግ/ጨ/008/2019

ፀደይ ባንክ አ.ማ ከስር የተዘረዘሩትን ዕቃዎች/ስራዎች/አገልግሎቶች ፈቃድ ያላቸውን ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት/ማሰራት ይፈልጋል::

ሎት-1 የህንፃ ግንባታ ፍኖተ ሰላም ቅርንጫፍ BC / GC -5 and above

Construction Work of G+4 Main Office Building ,Generator House ,Guard House, Fence Work and Site Work of Project

ሎት-2 ለቪዲዮ ቀረፃ የሚያገለግሉ ዕቃዎች

ተ.ቁየእቃው አይነትብዛት
1.Video Light2
2.Gimbal Stabilizer2
3.Camera Backpack Professional DSLR Bag Rain Cover2
4.Compact Memory Card for Camera (128GB)4
5.Zebra Lens with cage and bag1
6.Spotlight for photo camera1
7.Bag for camera stand (Tripod)2
8.Bag for LED Video Light Stand2
9.CF Card 128 GB2
10.Wireless Mic2
11.Tripod2

ስለሆነም ከዚህ በታች የቀረበውን መስፈርት የሚያሟላ ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ ድርጅት/ኀ.ጋ.ዶ/ መወዳደር የሚችል መሆኑን እንገልጻለን::

  1. የ2018 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፈቃድ # የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት በጨረታ ለመካፈል/ለመሳተፍ የሚሰጥ የምስክር ወረቀት/ክሊራንስ ጊዜው ያላለፈበት:: ቴክኒካል ዶክመንትና የሚያቀርቡበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ መሰረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል ::
  2. ለጨረታ ማስከበሪያ የአጠቃላይ ዋጋውን 2% ወይም የአጠቃላይ ዋጋው 2% ከብር 500,000.00 የሚበልጥ ከሆነ ብር 500,000.00 በሲፒኦ /CPO/ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ የ90 ቀን በፀደይ ባንክ አ.ማ ስም ማሰራት ይኖርባቸዋል:: ከየትኛውም የፀደይ ባንክ አ.ማ ቅርንጫፍ የተሰጠ ሲፒኦም ሆነ ባንክ ጋራንቲ ተቀባይነት የለውም ::
  3. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከጥቅምት 19 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት የስራ ቀናት ማለትም ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት እና ከሰዓት በኋላ ከ7:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 11:00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ አምስት መቶ ብር /500.00/ ፀደይ ባንክ ለገሃር ቅርንጫፍ ወይም በማንኛውም የፀደይ ባንክ ቅርንጫፍ የሂሳብ ቁጥር 1201390000037 በመክፈል ሰንጋተራ አካባቢ በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት 16ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 09 ከግዥ ክፍል ሰነዱን መዉሰድ ይችላሉ::
  4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ በሰም በታሸገ ፖስታ ጨረታው እስከሚዘጋበት ህዳር 02 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ድረስ አዲስ አበባ ሰንጋተራ አካባቢ ጤና ሚኒስቴር ዝቅ ብሎ በሚገኘው ፀደይ ባንክ ዋና መ/ቤት 16ተኛ ፎቅ ግዥና ዉል አስተዳደር ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል:: ጨረታው በተዘጋበት ዕለት በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ 4:30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመስሪያ ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል::
  5. የጨረታዉ መዝጊያ ሰዓት ካለፈ በኋላ የሚመጣ ማንኛዉም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረዉም::
  6. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

አድራሻ:- አዲስ አበባ ሰንጋተራ አካባቢ ጤና ሚኒስቴር ዝቅ ብሎ በሚገኘው የፀደይ ባንክ ዋና መ/ቤት ስልክ ቁጥር 0115581658

ፀደይ ባንክ አ.ማ

✨ messages.ai_summary
Tsedey Bank invites licensed bidders for two lots: Lot 1, construction of a G+4 main office building, generator house, guard house, fence and site works (BC/GC-5 and above); Lot 2, video production equipment. Bidders need a renewed business license, VAT certificate and valid clearance.
Save Tender