Tender Detail

Tender Details


ድርጅታችን የእናቶችና ሕፃናት ዘርፈ-ብዙ የልማት ድርጅት (ሜስሚዶ) ለተለያዩ ፕሮጀክት ትግበራዎች ይጠቀምባቸው የነበሩ የተለያዩ ቋሚ እቃዎች (ላብቶፕ፣ ኮምፒውተሮች፣ ፕሪንተሮች፣ የፎቶኮፒ ማሽኖች፣ ቴሌቪዥኖች፣ ስካነሮች፣ ሞተር ሳይክሎች ካሜራዎች፣ ብስክሌቶች፣ ስልኮች፣ ወንበሮች እና የመሳሰሉት) በአገልግሎት ጊዜ ብዛት እና በተለያዩ ምክኒያቶች በመበላሸታቸው እቃዎቹን አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

የእናቶችና ሕፃናት ዘርፈ-ብዙ የልማት ድርጅት (ሜስሚዶ)


 

በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

ጨ/ቁ ESP 52/2025

 

ከላይ በእርሱ እንደተጠቀሰው ድርጅታችን የእናቶችና ሕፃናት ዘርፈ-ብዙ የልማት ድርጅት (ሜስሚዶ) እ.ኤ.አ በ1989 ዓ.ም. የተመሰረተ ሲሆን በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር 1113/2011 በድጋሚ የተመዘገበና በሰርተፊኬት ቁጥር 0022 መሠረት በሁሉም የሀገሪቱ ክልሎችና ከተማ መስተዳድሮች የልማትና የሰብአዊ ምላሽ ስራዎችን እየሠራ የሚገኝ ድርጅት ሲሆን፡፡

ድርጅታችን ለተለያዩ ፕሮጀክት ትግበራዎች ይጠቀምባቸው የነበሩ የተለያዩ ቋሚ እቃዎች (ላብቶፕ፣ ኮምፒውተሮች፣ ፕሪንተሮች፣ የፎቶኮፒ ማሽኖች፣ ቴሌቪዥኖች፣ ስካነሮች፣ ሞተር ሳይክሎች ካሜራዎች፣ ብስክሌቶች፣ ስልኮች፣ ወንበሮች እና የመሳሰሉት) በአገልግሎት ጊዜ ብዛት እና በተለያዩ ምክኒያቶች በመበላሸታቸው እቃዎቹን አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም ድርጅታችን ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡

በመሆኑም ድርጅታችን ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።

  1. ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
  2. የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች በየክልሎች በሚገኙ የድርጅታችን ቅርንጫፍ መ/ቤቶች ወይም እንግሊዝ ኢምባሲ ፊት ለፊት የካ ግሎባል ት/ቤት ጎን በሚገኘው ዋናው መስሪያ ቤታችን የጨረታውን ሰነድ መጥተው በመውሰድ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመውሰድ ሲመጡ የማይመለስ 500 (አምስት መቶ ብር) የጨረታ ቁጥሩን በመግለጽ እናቶች እና ህጻናት ዘርፈ ብዙ የልማት ድርጅት የንግድ ባንክ አካውንት 1000004544618 በማስገባት የባንክ ስሊፕ ይዞ በመምጣት ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቾች ሰነዱን ሲያስገቡ ያስገቡትን ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ በድርጅቱ ስም ተሰርቶ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  5. ጨረታው ከወጣበት ህዳር 28, 2018 ዓ/ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 5 የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆያል።
  6. ተጫራቾች የሚወዳደሩትን ዋጋ ጨረታ ሰነዱን ሲወስዱ በሚሰጣቸው የዋጋ መሙያ ሰነድ ላይ ሞልተው እና ማህተም አድርገው በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ እና ፖስታው ላይ ማህተም በመምታት እስከ ታህሳስ 03 ‚2018 ዓ/ም ከቀኑ 10፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው ታህሳስ 07 ‚2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  7. ድርጅቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

ለተጨማሪ መረጃ እና ሰነድ ለመውሰድ በስልክ ቁጥሮች

አዲስ አበባ +25111261169፣ ሰመራ 0921698993፣ መቀሌ 0911093403፣ ባህር ዳር 0918002700፣ ጋምቤላ 0956509561፣ አሶሳ 0923386660፣ ዳሰነች 0917229685 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

Save Tender