Tender Detail

Tender Details


በጋምቤላ ሕ/ብ/ክ/መ/ብዙኃን መገናኛ አገልግሎት ለሚዲያ ሥራ አገልግሎት የሚውል ኤሌክትሮኒክ መሣሪያዎች

የጋምቤላ ሕ/ብ/ክ/መ/ብዙኃን መገናኛ አገልግሎት


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 01/2018

 

በጋምቤላ ሕ/ብ/ክ/መ/ብዙኃን መገናኛ አገልግሎት ለሚዲያ ሥራ አገልግሎት የሚውል ኤሌክትሮኒክ መሣሪያዎች፡-

  1. ዴስክቶፕ ኮምፒዩተር /Desktop Computer/                               6. ፕሪንተር /Printer/
  2. ላፕቶፕ ኮምፒዩተር /Laptop Computer/                                     7. ስማርት ቴሌቪዥን /Smart TV/
  3. ድሮን ካሜራ /Drone Camera/                                                    8. ሳምሰንግ ጋላክሲ S24 Ultra
  4. ቪዲዮ ካሜራ /Video Camera/                                                    9. ፕሮጀክተር /Generator/
  5. ቪዲዮ ኤዲቲንግ ዎርክስቴሽን /Video Editing Workstation/         10. USB Flash Drive

     

በዚዙ መሰረት ከላይ የተጠቀሱትን እቃዎች ለማቅረብ መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-

  1. ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው
  2. የዘመኑን ግብር የከፈለ
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN ሰርተፊኬት ያለው
  4. የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ
  5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ወይም ለመወዳደር ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ከማይመለስ ፎቶ ኮፒ እንዲሁም ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ
  6. የሚገዙ እቃዎች ዝርዝር ዓይነት መግለጫ /Specification/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  7. ተጫራቶች ስፔስፍኬሽን /Specification/ የቀረበላቸው ዕቃዎች በሙሉ ናሙና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል በክልሉ ብዙኃን መገናኛ አገልግሎት ግዥ ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 6 በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  9. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ በሰም የታሸገ ኢንቨሎፕ ሆኖ በሚመለከተው ኃላፊ ተፈርሞና የድርጅቱን ማህተም ያረፈበት መሆን ይኖርበታል፡፡
  10. ተጫራቾች በቅድሚያ ብር 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/ በጥሬ ወይም በባንክ በተመሰከረለት ሲ.ፒ.ኦ /CPO/ የሚጫረቱበትን በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ ያላስያዘ በጨረታው ሰነድ የመጀመሪያ ምርመራ ውድቅ ይደረጋል፡፡
  11. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የሚቆዩ ሲሆን በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከቀኑ 5፡30 ሰዓት ላይ በተጫራቾች ወይም በሕጋዊ ወኪሎቻቸው ፊት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን የመንግሥት ሥራ የማይኖርበት ቀናት ከሆነ በሚቀጥለው ተመሳሳይ የሥራ ቀናት ጨረታው እንደሚከፈት በማስታወቂያ ይገለጽላቸዋል፡፡
  12. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0475511472 ደውለው ይጠይቁ።

 

የጋምቤላ ሕ/ብ/ክ/መ/ብዙኃን መገናኛ አገልግሎት

 

Save Tender