Tender Detail

Tender Details


የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት በሰንጠረዥ የተገለፁትን ያገለገሉ ንብረቶች ለ2ኛ ጊዜ በድጋሚ በወጣ የሃገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ADDIS ABEBA CITY BUS SERVICE ENTERPRICE (የአዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት)


 

በድጋሚ የወጣ የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ያገ/ን/ሽ/ግጨ/003/2017

 

የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት በሰንጠረዥ የተገለፁትን ያገለገሉ ንብረቶች ለ2ኛ ጊዜ በድጋሚ በወጣ የሃገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

 

ተ.ቁ

የሚገዛው ዕቃ (አገልግሎት) አይነት

የጨረታ ማስከበሪያ መጠን

የጨረታ መዝጊያ ቀን

የጨረታ መክፈቻ ቀን

1

ሎት 1 የአውቶቡስ እና የተለያየ መጠን ያገለገሉ የተሸከርካሪ ጎማዎች

ለውድድር የቀረበውን ጠቅላላ የመነሻ ዋጋ 10%

መስከረም 05 ቀን 2018 ዓ.ም ሰዓት 8፡00

መስከረም 05 ቀን 2018 ዓ.ም ሰዓት 8፡30

2

ሎት 2፡- የአውቶቡስ እና የተለያየ መጠን ያላቸው ያገለገሉ የተሽከርካሪ ባትሪዎች

ለውድድር የቀረበውን ጠቅላላ የመነሻ ዋጋ 10%

መስከረም 05 ቀን 2018 ዓ.ም ሰዓት 8፡00

መስከረም 05 ቀን 2018 ዓ.ም ሰዓት 8፡30

3

ሎት 3፡- ያገለገለ ቁርጥራጭ ብረታ ብረት

ለውድድር የቀረበውን ጠቅላላ የመነሻ ዋጋ 10%

መስከረም 05 ቀን 2018 ዓ.ም ሰዓት 8፡00

መስከረም 05 ቀን 2018 ዓ.ም ሰዓት 8፡30

4

ሎት 4፡- ያገለገለ የአየር ማጣሪያ (Air Cleaner)

ለውድድር የቀረበውን ጠቅላላ የመነሻ ዋጋ 10%

መስከረም 05 ቀን 2018 ዓ.ም ሰዓት 8፡00

መስከረም 05 ቀን 2018 ዓ.ም ሰዓት 8፡30

5

ሎት 5፡- ያገለገለ ኤርባግ

ለውድድር የቀረበውን ጠቅላላ የመነሻ ዋጋ 10%

መስከረም 05 ቀን 2018 ዓ.ም ሰዓት 8፡00

መስከረም 05 ቀን 2018 ዓ.ም ሰዓት 8፡30

6

ሎት 6:- ጋዜጣ

ለውድድር የቀረበውን ጠቅላላ የመነሻ ዋጋ 10%

መስከረም 05 ቀን 2018 ዓ.ም ሰዓት 8፡00

መስከረም 05 ቀን 2018 ዓ.ም ሰዓት 8፡30

 

ስለሆነም በጨረታ መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች፡-

  1. ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ማቅረብ አለበት፡፡
  2. ተጫራቾች 22 በሚገኘው ኢየሩስ ህንፃ የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 01 በመምጣት ለሽያጭ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 700.00 (ሰባት መቶ ብር) በመክፈል ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 05 ቀን 2017 ዓ.ም ጨረታ ከመዘጋቱ በፊት ባለው ጊዜ ቅዳሜን ጨምሮ ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት እና ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 6፡00 ድረስ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከገዙ በኋላ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ንብረቶቹን በሚገኙበት ቃሊቲ ቅ/ፅ/ቤት የካ ቅ/ጽ/ቤት ሰሚት ቅ/ፅ/ቤት ሸጎሌ ቅ/ፅ/ቤት እና መካኒሳ ቅ/ጽ/ቤት በአካል በመሄድ መመልከት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች ለሁሉም ሎቶች የጨረታ መነሻ ዋጋ 10% (አስር በመቶ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንከ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ከጨረታው መዝጊያ ሰዓት በፊት ማስገባት አለባቸው፡፡የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡
  5. የጨረታ ሳጥኑ መስከረም 05 ቀን 2017 ዓ.ም ከሰዓት: 8:00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት ሃያ ሁለት ኢየሩስ ህንፃ 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 01 ይከፈታል፡፡ ነገር ግን የመክፈቻ ቀኑ የስራ ቀን ላይ ካልሆነ (እሁድ ላይ ከዋለ) ወይም በዓል ቀን ላይ ከዋለ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ላይ ይከፈታል፡፡
  6. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡ አድራሻ፡- የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት 22 ኢየሩስ ህንፃ 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 01

ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0116-66-33-67 በመደወል መዐ ይቻላል፡፡

 

የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት

 

Save Tender