Tender Detail

Tender Details


በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የምስራቅ ባሌ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት በዞኑ ስር ለሚገኙ የመንግስት መስሪያ ቤቶች በ2017 በጀት የመጀመሪያ ዙር ግዥ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።


 

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የምስራቅ ባሌ ዞን ገንዘብ /ቤት በዞኑ ስር ለሚገኙ የመንግስት መስሪያ ቤቶች 2017 በጀት የመጀመሪያ ዙር ግዥ፤

1 የደንብ ልብስ፣

2. የጽህፈት መሳሪያ፣

3. የትምህርት መርጃ መሳሪያ፣

4. የፅዳት እቃ፣

5. አላቂ የቢሮ እቃ፣

6. የመኪና ጎማ እና ባትሪ፣

7. ቋሚ እቃ (ፈረኒቸርና ኤሌክትሮኒክስ)

8. የሞተር ሳይክሎች 150

9. የቢሮ ውስጥ ምንጣፎችና ማስዋቢያ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

የመወዳደሪያ መስፈርት:-

  • የንግድ ፍቃድ ያለው እና ባለው የስራ ፍቃድ ልክ አቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል ፡፡
  • 2016 ግብርን ከፍሎ ያጠናቀቀ :: የንግድ ፍቃዱን 2017 የስራ ዘመን ያሳደሰ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችል ፡፡
  • የምዝገባ ቁጥር (TIN) ያለው፤ የቫት ተመዝጋቢ የሆነ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
  • የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO 30,000 ( ሰላሳ ሺህ ) ብር በምስራቅ ባሌ ዞን ገንዘብ /ቤት ስም አሰርተው በእጃቸው ይዘው ማቅረብ ሲኖርባቸው 2 (አመት) ወዲህ ለተደራጁ // ካደራጃቸው አካል የጨረታ ማስከበሪያ የዋስትና የተጠየቀውን የገንዘብ መጠን የሚጠቅስ ደብዳቤ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  • የተደራጁ መሃበራት ካደራጃቸው አካል ህጋዊ ማህበር መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ፡፡
  • ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በህትመት (ሃርድ ኮፒ) ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) የስራ ቀናት ከምስራቅ ባሌ ዞን ገቢወች መስሪያ ቤት የማይመለስ 300 ( ሶስት መቶ) ብር በመክፈል መግዛት ይችላል፡፡
  • ተጫራች የሚፈርመው ውል ለግማሽ አመት እንደሚቆይ ማወቅ ሲኖርበት ይህንን አውቆ ውል ለመግባት ፍቃደኛ የሆነ፡፡
  • ጨረታውን ተወዳድሮ ያሸነፈው ተጫራች የውል ማስከበሪያ ከተሰጠው ትእዛዝ ውስጥ 10% CPO ለማስያዝ ፍቃደኛ የሆነ፡፡
  • የተለያዩ ተቀናናሽ ክፍያዎችን ማለትም የቲኦቲ እና ከቫት 15 % ግማሹን (7.5) ለመክፈል ፍቃደኛ የሆነ።
  • ተጫራች ጨረታውን ማሸነፉ ከተገለፀ እና ትእዛዝ ከተቀበለ በኋላ ባሉት በተከታታይ 15 /አስራ አምስት/ ቀናት ውስጥ ምስራቅ ባሌ ዞን ገንዝብ /ቤት ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  • ተወዳዳሪዎች ለውድድር ሲቀርቡ ቴክኒካል ማስረጃቸውን እና .. በእጃቸው ይዘው ማቅረብ ሲኖርባቸው ቴክኒካል ኮፒውን በሰም አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  • ተጫራች ፋይናንሺያል ማስረጃ ዋናውንና ኮፒውን ለየብቻ በሰም በማሸግ ሙሉ ሰነዱን የመወዳደሪያ ዋጋቸውን በጥንቃቄ በግልፅ በማስቀመጥ ማህተም ስምና ፊርማ፤ የስልክ ቁጥራቸውን የድርጅታቸውን አድራሻ በመሙዋላት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  • የጨረታ ሰነዱ ማቅረቢያ ጊዜ የሚያበቃው ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት 16 (አስራ ስድስተኛው የስራ) ቀን ከጠዋቱ 330 ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው በዚያው ቀን ከጠዋቱ 400 ተወዳዳሪዎች / ህጋዊ ወኪሎች የግዥ ኮሚቴዎች ባለበጀት መስሪያ ቤቶች ባሉበት በምስራቅ ባሌዞን //ቤት በግዢ ክፍል ውስጥ በግልጽ ይሆናል:: ነገር ግን ተጫራች በሌለበት ይከፈት ብሎ ካመለከተ ሰነዱ የሚከፈት ይሆናል፡፡
  • የጨረታ ሰነዱ የሚከፈትበት ቀን ባጋጣሚ የስራ ቀን ባይሆን በቀጣዩ የስራ ቀን የሚከፈ ይሆናል።
  • የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ ዘግይቶ የሚቀርብ ማንኛውም የመወዳደሪያ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፤ የዋጋ ማሻሻያ ማድረግም አይቻልም፡፡
  • ተጫራቾች መጫረት የሚችሉት ባላቸው የንግድ ፍቃድ ዘርፍ ብቻ መሆኑን ማወቅ ይኖርባቸዋል። ከንግድ ፍቃዳቸው ዘርፍ ውጭ መወዳደር አይችሉም፡፡
  • ገዥው መስሪያ ቤት ግዥውን 20 ፐርሰንት ቀንሶ ወይም ጨምሮ ሊገዛ ይችላል፡፡
  • ገዥው መስሪያ ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::
  • ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የእቃ ሞዴል የመሙላት ግዴታ አለባቸው የሚያቀርቡትን እቃ ሞዴል ካልሞሉ ዋጋቸው ተቀባይነት የለውም።
  • ተጫራች ከዚህ በፊት ከገዢ መስሪያ ቤት ጋር ውል ፈርሞ ግድታውን ያልተወጣ ከሆነ በጨረታው መሳተፍ አይችልም፡፡

ማሳሰቢያ፡-

  • ተጫራች ሌሎች ዝርዝር ሁኔታወችን ከጨረታ ሰነድ ውስጥ ማግኘት ይችላሉ
  • ለአቅራቢው ከፍያ የሚፈጸመው በውድድሩ መሰረት ጥራት ያለውን እቃ በተፈለገው ጊዜ፤ መጠን ፤ ቦታ አይነት ሲያቀርብ በግዥ ኮሚቴወች እንዲሁም በሚመለከታቸው አካላት ታይቶ ርክክብ ከተደረገና ህጋዊ ደረሰኝ ለየመስሪያ ቤቱ ከተቆረጠ በኋላ ይሆናል፡፡
  • ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0910373081/ 0912198114 ደውለው ማጣራት ይችላሉ።

 

የምስራቅ ባሌ ዞን ገንዘብ /ቤት

Save Tender