በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 የሚገኘው የቁስቋም ጣይቱ ብጡል ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት እና በወተመህ በጀት ግዥ ለመፈፀም የወጣ ጨረታ
አንደኛ ዙር ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር ቁ/ጣ/ብ/የመጀመሪያና የመካከለኛ ደ/ት/ቤት001/2019
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 የሚገኘው የቁስቋም ጣይቱ ብጡል ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት እና በወተመህ በጀት ግዥ ለመፈፀም የወጣ ጨረታ
- 6211 ለደንብ ልብስ ለጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ 38,800.00 ብር
- 6211 ለደንብ ልብስ ስፌት ለጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ 1,200.00 ብር
- 6212 አላቂ ፅህፈት መሳሪያዎችና የቢሮ እቃዎች ለጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ 23.000.00 ብር
- 6213 ለህትመት ጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ 2,200.00 ብር
- 6214 ለቀይ መስቀል ለመጀመሪያ እርዳታ እቃዎች ለጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ 400.00 ብር
- 6215 አላቂ የትምህርት እቃዎች ለጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ 4,000.00 ብር
- 6215 አላቂ የትምህርት እቃዎች በወተመህ በጀት ለጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ብር 5,000.00
- 6218 አላቂ የፅዳት እቃዎች ለጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ 30,000.00 ብር
- 6219 ለልዩ ልዩ መሳሪያዎች ለጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ 1,000.00 ብር
- 6233 ለሰራተኞች ካፍቴሪያ መስተንግዶ ለጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ 28,000.00 ብር
- 6243 ለፕላንት ለማሽነሪ እና ለመሳሪያ እድሳትና ጥገና ሲፒኦ ብር 2,000.00
- 6244 ሰህንጻ መሳሪያ እቃዎች እና ለቁሳቁስ ለጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ 3,400.00 ብር
- 6313 ለቋሚ እቃ የሚውል ለጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ 16,216.00 ብር
- ብር6313 ለቋሚ እቃ የሚውል (በወተመህ) በጀት ለጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ 20,000.00
- 6244 ለህንጻ ለቁሳቁስ እና ለተገጣጣሚዎች እድሳትና ጥገና (በወተመህ) በጀት ለጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ብር 4900.00
- 6255 ለእቃ ጭነት አገልግሎት የሚውል ትራንስፖርት ለጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ 4,000.00
በዚህ መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ አቅራቢዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ይፈልጋል፡፡
- አግባብነት ያለው ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
- የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና የተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- ከፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር በአቅራቢነት ሊስት የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ለጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ በቁስቋም ጣይቱ ብጡል ቅድመ አንደኛ፣ እንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በሚል ተሞልቶ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ስለ ጨረታው የሚገልፀው የተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 የስራ ቀናት የማይመለስ በሎት ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱን ከፋይናንስ ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በ10ኛው ቀን 11፡30 ተዘግቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም ባይገኙም በጨረታ ኮሚቴው አማካኝነት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ መግለጫ በታሸገ ኤንቬሎፕ ኦርጅናል እና ኮፒ በማድረግ ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች መጫረት የሚችሉት በንግድ ፍቃድ ዘርፍ ብቻ መሆን አለበት::
- ተጫራቾች በእያንዳንዱ ሳምፕል ለሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና (ሳምፕል) ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ቅድሚያ ናሙና ያላቀረቡ ተጫራቾች ከውድድሩ ውጪ ይሆናሉ፡፡
- አሸናፊዉ በሚያቀርባቸው እቃዎች ላይ 10% የዉል ማስከበሪያ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርበታል። አሸናፊዉ ድርጅት ያሸነፈባቸዉ እቃዎች በራሱ ትራንሰፖርት መስሪያ ቤቱ ንብረት ከፍል ድረስ የማምጣት ግዴታ አለበት፡፡
- በማስታወቂያው ያልተገጹ ነገሮች ቢኖሩም በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
- ት/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ማንኛውም ተጫራቶች በሚያቀርቡበት የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ቫትን አካቶ መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- በዚህ ጨረታ ላይ ከተጠቀሰው ስራ (እቃ) ከውል በፊት እንደአስፈላጊነቱ 20% መጨመር ወይም የመቀነስ ት/ቤቱ መብት ይኖረዋል፡፡
- የጥቃቅንና አነስተኛ ተጫራች በሚወዳደርበት እቃ ካደራጃቸው የመንግስት ተቋም ለግዥ ፈፃሚ መ/ቤት የተፃፈ ደብደቤ መያዝና መወዳደር የሚችሉት በሚያመርቱት ምርት ላይብቻ ልዩ አስተያየት ይደረጋል፣ ይህ ካልሆነ እንደማንኛውም ተወዳዳሪ እኩል ይወዳደራል።
አድራሻ፡- ሽሮሜዳ ከፍ ብሎ እንጦጦ ፓርክ መውጫ ቁስቋም ጣይቱ ብጡል የመጀ/ደ/ት/ቤት
ስልክ: -0111236202
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 የሚገኘው የቁስቋም ጣይቱ ብጡል ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
