Tender Detail

Tender Details

  • Company በምዕራብ አርሲ ዞን የዶዶላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
  • Address በምዕራብ አርሲ ዞን : ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0913529429
  • Website
  • Deadline25 Sep 2026, 3:01 PM
  • magazineአዲስ ዘመን ጋዜጣ
  • Bid Document Price1000.00 ብር
  • opening dateጨረታው አየር ላይ ለተከታታይ 15 የስራ ቀናት ቆይቶ በ 16 ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  • Categories Cleaning & Janitorial , Office Supplies And Services , Textile, Garment & Leather , Vehicle tire , Electrical Materials

በምዕራብ አርሲ ዞን በዶዶላ ወረዳ መስተዳደር የዶዶላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 ዓ.ም የበጀት ዓመት ከዚህ በታች የተገለፁትን ዕቃዎችና አገልግሎቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ 01/209

በምዕራብ አርሲ ዞን በዶዶላ ወረዳ መስተዳደር የዶዶላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 ዓ.ም የበጀት ዓመት ከዚህ በታች የተገለፁትን ዕቃዎችና አገልግሎቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

  1. የፅህፈት መሳሪያ ዕቃዎች የፅዳት ዕቃዎች፣ አላቂ ዕቃና የትምህርት ዕቃዎች፣
  2. የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችና ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች
  3. የሠራተኛ ደንብ ልብስ
  4. የተሰያዩ የመኪና ጎማ
  5. የስፌት አገልግሱት

በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት ያስባቸው መስፈርት ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ናቸው።

  1. ተጫራቾች ከሚጫረቱበት ዕቃ ጋር ቀጥታ ግንኙነት ያለዉና ዕቃዎቹን በጥራት ለማቅረብ የሚያስችል ህጋዊ ንግድ ፍቃድ፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ /NAT TIN NO/ እንዲሁም የምዝገባ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችል ብቻ
  2. ተጫራቾች በጨረታ ተካፋይ ለመሆን የምትፈልጉት በምን ዓይነት ዕቃ እንደሆነ በሰነዶቻቸው ላይ በትከከል ለይተው መጻፍ ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የዕቃ ስም Brand Name ና የተመረተበትን ሀገር መግለጽ ይኖርባቸዋል።
  4. ማንኛውም ተጫራች የሚወዳደርበትን የዕቃ ዓይነት ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ ማቅርብ ይኖርበታል፡፡ በነጠላ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ መካከል ልዩነት ቢኖር የነጠላ ዋጋ ይወሰዳል፡፡
  5. ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ በ15 የስራ ቀናት ዉስጥ ቅዳሜ እሁድና የበዓለት ቀን ሳይጨምር በተ.ቁ 1,2,3,4, ና 5 የማይመለስ 1000.00 ብር በዶዶላ ወረዳ አገር ውስጥ ገቢዎች ባለስልጣን በመከፈል የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸው ላይ መ/ቤታችን በሰጣቸው የጨረታ ሰነድ ላይ የአንዱ ዋጋ የሚለው ቦታ ላይ ተጨማሪ እሴት ታከስ ያካተተ ዋጋ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በመሙላትና የድርጅታቸውን ማህተም በየገፁ ፊርማና ሙሉ አድራሻቸውን በመግለፅ በሰም በተሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦርጂናል እና ሁለት ጥር በሥራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 5 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  7. ለጨረታ ከቀረቡ ዕቃዎች ዝርዝር ውስጥ ጽ/ቤቱ እስከ 20% ለመጨመር ወይም ለመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ተመላሽ የሚሆን በተ.ቁ 1,2,3 ና 4 ብር 30,000.00 እንዲሁም በተ.ቁ 5 10.000.00 ብር በባንክ የተመሰከረለት (CPO) ወይም ጥሬ ብር በዶዶላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ማስያዝ አለበት፡፡
  9. የሚያቀርቡት ዕቃዎች ጥራት ያላቸዉና በተሰጠው ስፔስፊኬሽን መሰረት ተሟልተው መቅረብ ይኖርባችዋል። ተጫራቾቸ ውል በሚፈርሙበት ጊዜ አጠቃላይ ካሸነፉት ዕቃ ላይ የውል ማስከበሪያ ተመላሽ የሚሆን 10% በጽ/ቤቱ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  10. አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች በራሱ ትራንስፖርት እስከ ዶዶላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።
  11. በ 1, 2 ና 3 ውስጥ በመ/ቤታችን የተገለፁት ዕቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የሚመለስ ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡
  12. ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ15 የስራ ቀናት ቅዳሜ፤ እሁድና የበዓለት ቀን ሳይጨምር አየር ላይ ከዋላ በኋላ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመ/ቤታችን ቢሮ ቁጥር 5 ውስጥ ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታውን ከመከፈት አያግድም፡፡ ዕለቱ በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
  13. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0910408490/0910769460/ ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡

የምዕራብ አርሲ ዞን የዶዶላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

Save Tender