የአዲስ አበባ የመሬት ይዞታና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ የኮምፒውተር፣ የጽህፈት መሳሪያ፣ የመኪና ኪራይ፣ የደንብ ልብስ፣ የህትመት እና ሌሎች እቃዎችና አገልግሎቶች ግዥ
Addis Ababa City Admin. Landholding Registration and Information Agency (በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ)
ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዥው መለያ ቁጥር LHR/A/NCD/001/2019 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ይዞታና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ የ2019 በጀት ዓመት የቢሮ አላቂ እና ቋሚ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::
የሚገዛው ዕቃ ተዛማጅ አገልግሎት
- ሎት 01:- ኮምፒውተር፣ ኤሌክትሮኒክስ እና ተዛማጅ እቃዎች ግዥ
- ሎት 02:- የተለያዩ አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች ግዥ
- ሎት 03:- የመኪና ኪራይ
- ሎት 04:- የቢሮ ማስዋቢያ እቃዎች ምንጣፍ እና መጋረጃን ጨምሮ
- ሎት 05:- የመስተንግዶ አገልግሎት ግዥ
- ሎት 06:- የደንብ ልብስ ግዥ
- ሎት 07:- ሌሎች የቢሮ መገልገያ እና የጀኔሬተር መለዋወጫ እቃዎች ግዥ
- ሎት 08 :-የህትመት ግዥ
- ሎት 09:- የመኪና ጎማና ጌጣጌጥ እቃዎች
- ሎት 10:-የቅየሳ መሳሪያ ኪራይ
በመሆኑም በጨረታው የሚሳተፉ ተጫራቾች:-
- በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድና የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ እና በተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሎት 1: 30,000 ብር/ ሰላሳ ሺህ ብር/ ለሎት 2:- 10,000 ሺህ ብር /አስር ሺህ ብር/ ለሎት 3:- 80,000 ሺህ ብር /ሰማንያ ሺህ ብር/ ለሎት 4:- 15,000 ብር /አስራ አምስት ሺህ ብር/ ለሎት 5:- 15,000 ብር /አስራ አምስት ሺህ ብር/ ለሎት 6:- 150,000 ብር /አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር/ ለሎት 7:- 15,000 ብር /አስራ አምስት ሺህ ብር/ ለሎት 8:- 15,000 ብር /አስራ አምስት ሺህ ብር/ ለሎት 9:- 20,000 ብር /ሃያ ሺህ ብር/ ለሎት 10:- 50,000 ብር /ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ /CPO/ የመሬት ይዞታና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች በጨረታው ያሸነፉበትን እቃ በራሳቸው ትራንስፖርት እስከ ኤጀንሲው እቃ ግምጃ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል::
- ተጫራቾች የጨረታውን ፋይናንስ ሰነድ ዋናውን እና ኮፒውን እንዲሁም ቴክኒክ ሰነድ ዋናውን እና ኮፒውን ትክክለኛውን ቅጂ ለየብቻው በፖስታ አሽገው ማቅረብ አለባቸው::
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ናሙና እንዲቀርብ ለተጠየቁት እቃዎች ከጨረታው መከፈቻ ቀደም አድርገው ናሙና ማቅረብ አለባቸው:: ከተጠቀሰው ቀን ዘግይቶ የሚቀርብ ናሙና ተቀባይነት አይኖረውም::
- የጨረታው ፋይናንስ ሰነድ የሚከፈተው እና ግምገማ የሚካሄደው ከላይ ከተራ ቁጥር 1-7 የተመለከቱት ቴክኒካል መረጃዎች እና የእቃው ናሙናዎች በትክክል ተሟልቶ መቅረባቸው ሲረጋገጥ ነው::
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር ከጠዋቱ 2:30 እስከ ቀኑ 6.30 እና ከቀኑ 7:30 እስከ 11:30 ሰዓት ድረስ ከጎላጎል ወደ መገናኛ በሚወስደው መንገድ ለም ሆቴል አካባቢ በሚገኘው የመሬት ይዞታና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ ዋናው መስሪያ ቤት 13ኛ ፎቅ ላይ የግዥ ንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት በመምጣት የማይመለስ 300 ብር/ ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ::
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ በ11ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4:-00 ሰዓት የጨረታው ሳጥን ተዘግቶ በዚያው እለት ከጠዋቱ 4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል:: የጨረታው መዝጊያ እና መክፈቻ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል::
- ኤጀንሲው አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተገለፀው መጠን 20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል::
- በሌሎች ዋጋ ላይ ተንተርሶ መጫረት አይቻልም::
- ኤጀንሲው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ
ከጎላጎል ወደ መገናኛ በሚወስደው መንገድ ለም ሆቴል አካባቢ በሚገኘው የመሬት ይዞታና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ ዋናው መስሪያ ቤት ህንፃ 13ኛ ፎቅ ወይም በስልክ ቁጥር 0118125085 ደውለው ያነጋግሩ::
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ይዞታና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ
✨ messages.ai_summary
Addis Ababa Landholding Registration and Information Agency seeks suppliers in 10 lots, including computers and electronics, stationery, vehicle rental, office décor, catering, uniforms, printing, generator parts, tires and survey equipment rental. Open bid.
