Tender Detail

Tender Details


የዓለም ከተማ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት የጽህፈት መሳሪያ፣ ህትመት፣ ጽዳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ኮምፒዩተር፣ የመኪና መለዋወጫ፣ ደንብ ልብስ እና የተሽከርካሪ ጥገና ግዥ

የሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ


ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሰ/ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ የዓ/ከ/ከ/አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት በስሩ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች የተለያዩ የቋሚና አላቂ እቃዎችን ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያዎች፤ ሎት 2 ህትመት፤ ሎት 3 የጽዳት እቃዎች፤ ሎት 4 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፤ ሎት 5 ኮምፒዩተር እና ተዛማጅ፤ ሎት 6 የመኪና መለዋወጫዎች፤ ሎት 7 ደንብ ልብስ፤ ሎት 8 የተሽከርካሪ ጥገና እና የጎሚስታ አገልግሎት ስራዎች በግልፅ ጨረታ ለ2019 በጀት ዓመት ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል። ስለዚህ በዘርፉ ላሉት በመሆኑም በዘርፉ የስራ ፈቃድ ያላቸውን ነጋደዎች በግልፅ ጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል። ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው።
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin number/ ያላቸው።
  3. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  4. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆኑ የግብር ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ።
  5. የግዥው መጠን ከብር 500,000 /አምስት መቶ ሺህ ብር / እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  6. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-5 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  7. የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፍኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
  8. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ከዓ/ከ/ከ/አስ/ገንዘብ/ጽ/ቤት/ግ/ፋ/ን/አስ// ቡድን ከፍል ቢሮ ቁጥር 13 ማግኘት ይችላሉ።
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ጨረታ በቁርጥ ለፅ/መሳሪያ 40000 (አርባ ሺህ ብር)፤ ለኮምፒዩተር እና ተዛማጅ 30000 (ሰላሳ ሺህ ብር) ለፅዳት ዕቃ 15000 (አስራ አምስት ሺህ ብር)፤ ለመኪና መለዋወጫ እቃዎች ብር 15000/አስራ አምስት ሺህ ብር እና ለሌሎቹ ለእያንዳንዳቸው ሎት ጨረታዎች 5000 (አምስት ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በጽ/ቤቱ ገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው።
  10. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ-28-/02/2019 ዓ.ም እስከ 7/03/2019 ዓ/ም ድረስ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  11. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ሞልተው የጨረታውን አይነት በመግለጽ በፖስታው ላይ በመፃፍና የድርጅቱን ማህተም፣ ስልክ ቁጥርና ፊርማ በመፈረም ማስታወቂያው ከወጣበት ከ-28-/02/2019 ዓም እስከ 8/03/2019 ዓ.ም የካላንደር መቁጠሪያ ቀናት ከጠዋቱ 3:30 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው። በዚሁ እለት ከጠዋቱ 3:30 የጨረታ ሳጥኑ ይታሸጋል።
  12. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ-8/3/2019 ዓ/ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት በግ/ፋ/ን/አስ/ደ/ስ/ሂ ክፍል በሮ ቁጥር 32 ይከፈታል።
  13. መ/ቤቱ ጨረታውን በጥቅል/ ሎት ወይም በነጠላ የማወዳደር መብት አለው።
  14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  15. ጨረታው በመሰረዙ ምክንያት ተጫራቾች ለመወዳደር ላወጡት ወጭ መ/ቤቱ ኃላፊነት የማይወስድ መሆኑን
  16. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 32 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 011 13 20 801 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
  17. ተጫራቾች ያሸነፉትን ሙሉ ስራ የመስራት ግዴታ ይኖርባቸዋል።
  18. የጨረታ መክፈቻ ቀን በስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይቀየራል።
  19. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ሲሞሉ ከቫት በፊት ከነቫቱ እዲሁም ጠቅላላ ዋጋ ስርዝ ድልዝ በሌለው መልኩ መሙላት ይጠበቅባቸዋል። ይህ ካልሆነ ግን ጨረታው ውድቅ ይሆናል።
  20. ተጫራቾች ለሚገዙት ሰነዶች ከሰነዱ ጋር ከቀረበው የግዥ ሰነድ ጋር አግባብነት ያለው ንግድ ፍቃድ ማቀረብ ይኖርባቸዋል።
  21. ለማንኛውም ግዥ ለእቃዎች ከ20,000 ብር /ሃያ ሺህ ብር/በላይ እና ለአገልግሎት ከ10,000 ብር /አስር ሺህ ብር/ በላይ ለሚሆኑ ግዥዎች አቅራቢው ከሚፈፀምለት ክፍያ ላይ 3% የቅድመ ግብር ተቀንሶ የሚቀር መሆኑን ማወቅ አለባቸው።

የስራ ቦታ ዓለም ከተማ
አድራሻ ዓለም ከተማ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ስልክ ቁጥር 0111320801/395

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሰ/ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ

✨ messages.ai_summary
Alem Ketema Town Finance Office (North Shewa Zone, Amhara) seeks suppliers in 8 lots: stationery, printing, cleaning items, electronics, computers, vehicle spare parts, uniforms, and vehicle maintenance and tyre services. Open bid.
Save Tender