Tender Detail

Tender Details


የደቡብ ወሎ ዞን ቦረና ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸር፣ የእንስሳት መድሀኒት፣ የኮንስትራክሽን ማቴሪያል፣ ደንብ ልብስ፣ የጽህፈት መሳሪያ እና ሌሎች እቃዎች ግዥ

የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የደቡብ ወሎ ዞን የቦረና ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሄራዊ በክልላዊ መንግስት የደቡብ ወሎ ዞን የቦረና ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት አመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሎቶች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::

  1. ሎት 1 ኤሌክትሮኒክስ
  2. ሎት 2 የቢሮ ቋሚ እቃ/ፈርኒቸር/
  3. ሎት 3 የአስፖርት ትጥቅ
  4. ሎት 4 የእንስሳት መድሀኒት
  5. ሎት 5 የኮንስትራክሽን ማቴሪያል
  6. ሎት 6 የኪና ጎማ
  7. ሎት 7 ቋሚ እና አላቂ የቢሮ እቃዎች
  8. ሎት 8 የጽህፈት መሳሪያ
  9. ሎት 9 የጽዳት እቃ
  10. ሎት 10 የመኪና እቃ
  11. ሎት 11 የደንብ ልብስ ጫማ
  12. ሎት 12 ሱፍ መሰል ጣቃና ቲትረን 6000
  13. ሎት 13 የተዘጋጁ ልብሶች
  14. ሎት 14 ህትመት

በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለለመግዛት ይፈልጋል፤ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል

ስለዚህ

  1. የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር ያላቸው!
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት /ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
  4. ግዥ ከ500.000 በላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበት
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-4 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው:
  6. የሚገዙ እቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል:
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 400 / አራት መቶ ብር/ ለእያንዳንዱ ሎት በመክፈል ቢሮ ቁጥር 9 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ:
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢል ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ የዕቃ ዋጋ 1% እና ከዚያ በላይ ከባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ / ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው::
  9. ማንኛውም ተጫራች ግዢ በጥቅል /በሎት/ የሚፈጸም መሆኑን አውቆ የእያንዳንዱን ዝርዝር እቃዎች መሙላት ይኖርባቸዋል ሆኖም የተዘረዘሩትን እቃዎች በመሙላት ጠቅላላ ዋጋውን ያለመሙላት ስርዝ ድልዝ ማህተም ፊርማ ያለማድረግ ጭምር ከጨረታ ውጭ ያደርጋል::
  10. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆነ በሁለት ቅጅ በማድረግ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በቦረና ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት ቢሮ ቁጥር 9 ግዥ ክፍል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል::
  11. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 ቀናት የሚቆይ ሲሆን 16ኛው ቀን 3:30 ታሽጎ ከጧቱ 4:00 የሚከፈት ሲሆን የበዓል ቀን ወይም ቅዳሜ ና እሁድ ከሆነ በተመሳሳይ ቀን ከጧቱ 3 30 ታሽጎ 4:00 የሚከፈት መሆኑ ይታወቅ ::
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤
  13. የንብረት ርክብክብ የሚፈጸመው ቦረና ወረዳ ገንዘብ/ጽ/ቤት እና ሴክተር መ/ቤቶች ነው::
  14. በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ከፈለጉ ከግዥ ጨረታ መመሪያው ወይም ቢሮ ቁጥር 9 በቦረና ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ በመገኘት ወይም ስልክ 033 2405441 ወይም 0938429553 መደወል ይችላሉ::

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግ ስት ደ/ወሎ መስተዳደር ዞን የቦረና ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Borena Woreda Finance Office (South Wollo, Amhara) seeks suppliers in 14 lots, including electronics, office furniture, sports kits, veterinary medicines, construction materials, tyres, stationery, cleaning items, vehicle parts, uniforms, fabric and printing. Open bid.
Save Tender