Tender Detail

Tender Details

  • Company Buusaa Gonolaa Microfinance S.C (ቡሳ ጎኖፋ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ)
  • Address Kolle Keranio Sub-cilly, Woreda 03 Debrezey Road Betesaldo Building, 5 floor : Oromia Region, Ethiopia, Phone: 251 114162621
  • Websitehttp://www.bgmfi.com
  • Deadline20 Nov 2026, 4:00 PM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceብር 200.00 (የማይመለስ)
  • Bid Securityከተጫረቱበት ዋጋ 10% (ሲ.ፒ.ኦ)
  • opening dateህዳር 11 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 10:30 ሰዓት
  • Categories Printing And Publishing

ቡሳ ጎኖፋ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ የጥራዞች፣ ቅጾች፣ ደብተሮች እና ሰርተፊኬቶች የህትመት አገልግሎት ግዥ

Buusaa Gonolaa Microfinance S.C (ቡሳ ጎኖፋ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ)


የህትመት አገልግሎት ጨረታ ማስታወቂያ

ቡሳ ጎኖፋ ማይክሮፋይናንስ አ.ማ ለሚሰጠው የብድርና ቁጠባ አገልግሎት የሚጠቀምባቸውን የተለያዩ ጥራዞች ፣ ቅጾች ፣ ፎርሞችና ሾውቸሮች የህትመት አገልግሎት ፍላጎት ካላቸው የሀገር ውስጥ ማተሚያ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አገልግሎት ማግኘት ይፈልጋል:: የስራው ዝርዝር እንደሚከተለው ይሆናል::

ተ.ቁየሚታተሙት ሰነዶች ዝርዝርመለኪያብዛትመግለጫ
1የተለያዩ ጥራዞች ህትመትጥራዝ7000የተለያየ መጠን ያላቸው
2የተለያዩ ቅጾች/ ፎርሞች ህትመትቁጥር135000የተለያየ መጠን ያላቸው
3የተለያዩ የቁጠባ እና የብድር ደብተሮችቁጥር50000መጠናቸው ይለያያል
4ሰርተፊኬትበቁጥር5000

በመሆኑም በጨረታ መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች የሚከተሉትን ህጋዊ ሰነዶች ማሟላት ይኖርበታል::

  • የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፤ ቫት ምዝገባ ማረጋገጫ ፤ የታክስ ክሊራንስ፤ የታክስ ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፊኬት፤ የቫት ደረሰኝ እና ሌሎች አስፈለጊ መረጃዎች ፤ የስራ ልምድን ጨምሮ ማቅረብ ይኖርበታል::
  • ጨረታው ጸንቶ የሚቆየው ለ10 (አስር) የስራ ቀናት ነው:: ማለትም ከጥቅምት 30 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ ህዳር 11 ቀን 2019 ዓ.ም ሆኖ የጨረታ ማስረከቢያ ቀን ህዳር 11 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ሰ ዓ ት ድረስ ነው።
  • ሰነድ ለመግዛት የምትፈልጉ ሰነዱ በሚገኝበት በቡሳ ጎኖፋ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ ዋናው መስሪያ ቤት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ በመቅረብ የማይመለስ ብር 200.00 ( ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ትችላላችሁ::
  • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያቀርቡት በተጫረቱበት ዋጋ ብር 10 ፐርሰንት ( አስር በመቶ) በሲ.ፒ.ኦ በማቅረብ ይሆናል::

ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ (ኦርጅናል እና ኮፒ ለየብቻ) ከላይ በተጠቀሰው የጨረታ ማስገቢያ ጊዜ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል:: ጨረታው የሚከፈተው ህዳር 11 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 10:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቡሳ ጎኖፋ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ ዋናው መ/ቤት ስብሰባ አዳራሽ ይሆናል። ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

በጨረታው ያሸነፈ/ፉ ተጫራች/ቾች የጨረታው ውጤት በታወቀ 5 የስራ ቀናት ውስጥ ውል መፈረም አለባቸው::

አድራሻ፦ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠመንጃ ያዥ ቅርንጫፍ ፊት ለፊት ፤ ቤተ ሳ ይ ዳ ህንጻ 4ኛ ፎቅ አስተዳደር መምሪያ ቢሮ (አ.አ)::
ስልክ ቁጥር:-0114 162536/ 0936784833

ቡሳ ጎኖፋ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ

✨ messages.ai_summary
Buusaa Gonofaa Microfinance S.C. seeks local printing companies to print registers, forms, savings and loan passbooks, and certificates for its credit and savings services. Work experience is required. Open bid.
Save Tender