የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ትምህርት ቢሮ በ2019 በጀት ዓመት በዩኒሴፍ ፕሮግራም ለሴት ተማሪዎች የንጽሕና መጠበቂያ ቁሳቁስ (መልሶ ጥቅም ላይ የሚውል ሞዲስ፣ የውስጥ ሱሪ/ፓንት/ እና ሳሙና) እንዲሁም ለቅድመ-አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አመራሮች ልዩ የሥራ ላይ ሥልጠና ማሰልጠኛ ሞጁል ህትመት በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
Central Ethiopia Region Bureau of Education (የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ትምህርት ቢሮ)
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 002
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ትምህርት ቢሮ በ2019 በጀት ዓመት በዩኒሴፍ ፕሮግራም ለሴት ተማሪዎች የንጽሕና መጠበቂያ ቁሳቁስ (መልሶ ጥቅም ላይ የሚውል ሞዲስ፣ የውስጥ ሱሪ/ፓንት/ እና ሳሙና) እንዲሁም ለቅድመ-አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አመራሮች ልዩ የሥራ ላይ ሥልጠና ማሰልጠኛ ሞጁል ህትመት በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ሎት 01: ለሴት ተማሪዎች የንጽሕና መጠበቂያ ቁሳቁስ (መልሶ ጥቅም ላይ የሚውል ሞዲስ፣ የውስጥ ሱሪ /ፓንት/ እና ሳሙና) ግዥ
ሎት 02: ለቅድመ-አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አመራሮች ልዩ የሥራ ላይ ሥልጠና ማሰልጠኛ ሞጁል ህትመት።
የጨረታ መመሪያዎች:-
- በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድና የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ያሳደሱ፣ በግብር ከፋይነት ተመዝግበው የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸውና ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የተመዘገቡበትን የምዝገባ ወረቀት፣ እንዲሁም የአቅራቢዎች ዝርዝር የዘመኑን የግብር ግዴታ የተወጡበትን መረጃ አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ትምህርት ቢሮ ቁጥር 01 በመቅረብ ለሥራው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ብር 200 (ሁለት መቶ) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ፋይናንሻልና ቴክኒካል በአንድ ኦርጅናል እና ኮፒ ለየብቻው አሽገው ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሎት 01 ብር 140,000.00 (አንድ መቶ አርባ ሺህ ብር ብቻ)፣ ለሎት 02 ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር ብቻ) በባንክ የተረጋገጠ C.P.O ወይም የባንክ ጋራንቲ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች ወራቤ ከተማ በሚገኘው የክልሉ ትምህርት ቢሮ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ማቅረብ አለባቸው።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ11ኛው ቀን 8:00 ሰዓት ላይ ይታሸጋል፤ በ8:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- የውል ማስከበሪያ:- የጨረታው አሸናፊ መሆኑ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ከ7 ቀናት በኋላ ውሉን መፈረምና ተቀባይነት ባላቸው የዋስትና ዓይነቶች የውሉን ጠቅላላ ዋጋ 10% በውል ማስከበሪያነት ማስያዝ አለበት።
- ቢሮው ከአሸናፊው ተጫራች ጋር ውል ከመፈረሙ በፊት በጨረታው ሰነድ ከተገለጸው የአቅርቦት መጠን ላይ መጨመር ወይም መቀነስ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ፣ በጨረታው ውድድር አሸናፊው የሰጠውን ዋጋ ሳይቀይር እስከ 20% መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል።
- የጨረታ ሰነዱ ፀንቶ የሚቆየው ለ45 ቀናት ብቻ ነው።
- ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0467710688 መጠየቅ ይችላሉ።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ትምህርት ቢሮ
✨ messages.ai_summary
Central Ethiopia Region Education Bureau buys, under a UNICEF programme, menstrual hygiene kits for female students (reusable pads, underwear and soap) and printing of training modules for school leaders, by open tender. Bidders need a renewed sector licence, TIN, VAT and paid tax.
