Tender Detail

Tender Details

  • Company MIDROC GOLD Mine P.L.C (ሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኃ.የተ.የግ.ማህበር)
  • Address ሰሚት ፋርማኪዩር ግቢ ውስጥ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0921-10-12-47
  • Website
  • Deadline22 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazinefortune
  • Bid Document Priceብር 1000 (የማይመለስ)
  • Bid Securityከሚያቀርቡት ዋጋ 20% (በባንክ የተረጋገጠ CPO)
  • opening dateበዚያኑ ቀን በ4:30 ሰዓት (ቅዳሜ፣ እሑድ ወይም በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን)
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure , Disposal Sale , Vehicle

ሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኃ.የተ.የግ.ማህበር ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች የጨረታ ሽያጭ

MIDROC GOLD Mine P.L.C (ሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኃ.የተ.የግ.ማህበር)


ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ

  1. በጨረታ የሚሳተፈው ድርጅት ከሆነ የታደሰ ንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር የከፈለ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል እንዲሁም ከዚህ ጨረታ ጋር በተያያዘ ማንኛውም ገቢ የሚደረግ ገንዘብ በተጫራች ድርጅት ስም መሆን አለበት::
  2. ተጫራቾች በተራ ቁጥር 15 ላይ በተገለፀው ቦታ በአካል ቀርበው የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 1000 (አንድ ሺህ ብር) በሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኃ.የተ.የግል ማህበር ስም በዳሽን ባንክ የሂሳብ ቁጥር 0122244971011 ወይም በንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000000933353 በማስገባት ያስገቡበትን የባንክ ስሊፕ በመያዝ ሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ፋይናንስ መምሪያ የገንዘብ ገቢ ደረሰኝ በማስቆረጥ ሠነዱን በተራ ቁጥር አራት ላይ በተገለፀው የሥራ ቀንና ሰዓት መሠረት መውሰድ ይችላሉ::
  3. በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ሠነድ ለመግዛት ሲመጡ የታደሰ መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል::
  4. ተጫራቾች ሰነድ ገዝተው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 3:00 እስከቀኑ 8:00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ተሽከርካሪዎችን በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 ቃሊቲ አደባባይ/ መንገድ ትራንስፖርት ማሰልጠኛ/ ወደ ሐና ማሪያም አቅጣጫ በቀኝ ጠርዝ 50 ሜትር በኩል የድሮ ዩናይትድ አዉቶ ጋራዥ ቢግ ኤም አፓረል እና ጋርመንት (BIG M) ጎን በሚገኘው የድርጅቱ ተርሚናል ግቢ ውስጥ በመሄድ መመልከት ይችላሉ::
  5. ተጫራቾች ለሚሳተፉበት (ለሚገዙት) ለእያንዳንዳቸው ተሽከርካሪዎች ያስገቡትን ዋጋ ሃያ በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኃ.የተ.የግ.ማህበር ስም ማስያዝ ይኖርበታል::
  6. ተጫራቾች ድርጅቱ ባዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ የተሽከርካሪ ዓይነትና የሠሌዳ ቁጥር ትይዩ የሚገዙበትን ዋጋ በመጥቀስ ከጨረታ ማስከበሪያ CPO ጋር በማካተት ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመረጡት ተሽከርካሪ ዋጋ የዋጋ ማቅረቢያ እና CPO በታሸገ ኤንቨሎፕ በማዘጋጀት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በማስገባት መወዳደር ይችላሉ:: የጨረታ የመገምገሚያ መስፈርት ዋጋና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ኦርጅናል CPO እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ይኖርበታል::
  7. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መኪኖቹ በሚገኙበት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 ቃሊቲ አደባባይ/ መንገድ ትራንስፖርት ማሰልጠኛ/ ወደ ሐና ማሪያም አቅጣጫ በቀኝ ጠርዝ 50 ሜትር በኩል የድሮ ዩናይትድ አዉቶ ጋራዥ ቢግ ኤም አፓረል እና ጋርመንት (BIG M) ጎን በሚገኘው የድርጅቱ ተርሚናል ግቢ ውስጥ ይከፈታል:: ሆኖም የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜ እና እሑድ ወይም የበዓላት ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል::
  8. በጨረታው አሸናፊ የሆኑት ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለፀላቸው በ10 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል ሆኖም ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለድርጅቱ ገቢ ይደረጋል::
  9. የጨረታ አሸናፊዎች ለሚገዟቸው ተሽከርካሪዎች የስም ማዛወሪያ እና በመንገድ ትራንስፖርት ግምትና የሽያጭ ውል ልዩነት ካለ ለአገር ውስጥ ገቢዎች ሚኒስቴር የሚከፈል ወጪ በጨረታ አሸናፊዎች ይሸፈናል::
  10. የጨረታ ሰነድ በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከውድድሩ ውድቅ ይደረጋል::
  11. በጨረታው አሸናፊ የሆነ ግለሰብ/ ድርጅት አሸናፊነቱ በተገለፀለት በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ጊዜ ውስጥ አሸናፊ የሆነበትን ተሽከርካሪ ሙሉ ዋጋ ገቢ በማድረግና የሽያጭ ውል በመዋዋል ተሽከርካሪውን ተረክቦ ማንሳት ይኖርበታል:: ሆኖም ተሽከርካሪውን በተጠቀሰው ቀን ማንሳት ካልቻለ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው CPO የማይመለስ ይሆናል::
  12. በጨረታው የተሸነፈ ተጫራች ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ CPO ለተጫራች ሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኃላ.የተ.የግ.ማህበር በሚያወጣው ፕሮግራም መሠረት እንዲመለስ ይደረጋል::
  13. በጨረታ ሰነድ ላይ በሚቀርበው ፖስታ ላይ የተሽከርካሪው ሠሌዳ ቁጥር እና መለያ ኮድ መፃፍ አለበት:
  14. በጨረታ ሰነዱ ላይ የተጠቀሱት ደንብና ሁኔታ አስገዳጅ ናቸው::
  15. የጨረታ ሰነድ መሸጫ ቦታ አዲስ አበባ ሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኃ.የተ.የግ.ማህበር ስሚት ፋርማ ኪዩር ግቢ1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 ነው::
  16. ድርጅቱ በማንኛውም ምክንያት ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
  17. ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0917-83-32-06 እና 0911-19-00-03 ይጠቀሙ::

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ / ሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኃ.የተ.የግ.ማህበር

✨ messages.ai_summary
MIDROC Gold Mine PLC (MIDROC Investment Group) is selling used vehicles by sealed bid. Vehicles can be inspected at its terminal compound in Akaki Kality sub-city, Addis Ababa, after buying the bid document. Open to individuals and companies.
Save Tender