አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ በደብረ ብርሃን እና በአንኮበር የሚገኙ የመኖሪያ ቤቶች የሐራጅ ሽያጭ
Akufada Micro Finance Institution S.C. (አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ)
የሐራጅ ማስታወቂያ
ቁጥር:- AMFI/04 /2019
አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 97/1990 (እንደተሻሻለው) በተሰጠው ስልጣን መሠረት ቀጥሎ የቀረቡትን ንብረቶች በግልጽ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::
| ተ.ቁ | የተበዳሪው ስም | የንብረት አስያዥ ስም | አበዳሪ ቅርንጫፍ | ለሐራጅ የቀረበው ንብረት | አድራሻ | የካርታ ቁጥር | የቦታ ስፋት | የሐራጅ መነሻ ዋጋ በብር | ቀን | ሰዓት |
| 1 | እነ ወ/ሮ ሰላም ጌታቸው (2) ሰዎች | ወ/ሮ ሰላም ጌታቸው | ዶ/ር ከበደ ሚካኤል | የመኖሪያ ቤት | አማራ ክልል፣ ደ/ብርሃን ከተማ፣ ጫጫ ከተማ 01 ቀበሌ | 3039/14 | 200 ካ/ሜ | 2,700,000 | ህዳር 28 ቀን 2019 ዓ.ም | 3:30-4:00 |
| 2 | እነ በፍርዱ አይደፍሩህም(2) ሰዎች | ወ/ሮ እልፍነሽ የሺ | ዶ/ር ከበደ ሚካኤል | የመኖሪያ ቤት | አማራ ክልል፣ ደ/ብርሃን ከተማ፣ ጫጫ ክ/ከተማ፣ን/ሀ/መለኮት ቀበሌ | 3578/15 | 200 ካ/ሜ | 2,000,000 | ህዳር 28 ቀን 2019 ዓ.ም | 4:00-4:30 |
| 3 | ፀደቀ ወንዳፈረው | ላቀው ምኒሉ | ንጉስ ሳህለ ስላሴ | የመኖሪያ ቤት | አማራ ክልል፣ ሰ/ሸዋ ዞን፣ አንኮበር ወረዳ፣ ጎረቤላ ከተማ፣ 01 ቀበሌ | 0273/97 | 200 ካ/ሜ | 497,000 | ህዳር 28 ቀን 2019 ዓ.ም | 4:40-5:00 |
የሐራጅ ደንቦች:-
- ተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ (1/4ኛ) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ.) ብቻ በአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ::
- አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ አሸናፊ መሆኑ በደብዳቤ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ባሉት በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃልሎ መክፈል አለበት:: ካልተከፈለ የተያዘው ገንዘብ ለማይክሮ ፋይናንሱ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል:: በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል:: በጨረታው ተሸናፊ ለሆኑት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ በዕለቱ ይመለስላቸዋል::
- በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ ተበዳሪ እና ንብረት አስያዥ ወይም ሕጋዊ ተወካዮቻቸው ብቻ ናቸው:: ተበዳሪ እና ንብረት አስያዥ ወይም ወኪሎቻቸው ባይገኙም ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል::
- የመኖሪያ ቤቱ ጨረታ አሸናፊ ለሆነው ተጫራች በማይክሮ ፋይናንሱ የብድር ፖሊሲ፣ መመሪያ እና ቅደመ ሁኔታ መሠረት ብድር ሊመቻችለት ይችላል::
- ከላይ በሰንጠረዡ ውስጥ የተገለፁት የመኖሪያ ቤቶች ሁሉም ጨረታዎች የሚከናወኑት በደ/ብርሃን ከተማ፣ [...] ክ/ከተማ፣ ንግስት እሌኒ ቀበሌ አፄ ዘርዓያዕቆብ ህንጻ ላይ በሚገኘው የማይክሮ ፋይናንሱ ዋና መ/ቤት 4ኛ ፎቅ አዳራሽ ውስጥ ይሆናል::
- የተጫራቾች ምዝገባ ከእያንዳንዱ የንብረት ሐራጅ መዝጊያ ሰዓት ከሰላሳ ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል:: በሐራጁ የመጨረሻ ሰላሳ ደቂቃዎች የተጫራች ምዝገባ አይካሄድም::
- የሐራጁ አሸናፊ/ገዢ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን፣ ከስም ማዛወሪያ ክፍያ ጋር የተገናኙ እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ የግብር ግዴታዎችን ገዥው/አሸናፊው ይከፍላል::
- ተጫራቾች የጨረታው ቀን ከመድረሱ 5 (አምስት) ቀን በፊት ከማይክሮ ፋይናንሱ ጋር በመነጋገር በስራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዘ በቦታው በመገኘት ለጨረታ የቀረቡትን ንብረቶች መጎብኘት (መመልከት) ይችላሉ::
- ተጫራቹ የጨረታው አሸናፊ ነው የሚባለው አሸናፊነቱን የሚገልፅ ደብዳቤ በፅሑፍ ሲደርሰው ነው::
- ማይክሮ ፋይናንሱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0116376246 (ሕግ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት) ደውለው መጠየቅ ይችላሉ::
አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ
✨ messages.ai_summary
Akufada Microfinance Institution is auctioning three foreclosed residential houses on 200 square metre plots in Debre Birhan and Ankober woreda, North Shewa, Amhara. Bidders deposit a quarter of the starting price by CPO; loans may be arranged. Public auction.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
