የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት በሸገር ከተማ ኮዬ ፈጬ የሚገኝ ስቱዲዮ ኮንዶሚኒየም ቤት የሐራጅ ሽያጭ
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
በፍ/ባለመብት መዝገቡ ማንደፍሮ እና በፍ/ባለዕዳ እነ ኤፍሬም ማንደፍሮ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/196915 በ06/02/2018 ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ እና በኮ/መ/ቁ/211739 በ29/3/2018 ዓ.ም በኮ/መ/ቁ/211739 በ9/10/2018ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በሸገር ከተማ በኮዬ ፈጬ ክ/ከተማ ውስጥ የሚገኝ የቤት ቁጥር 01 የህንጻ ቁጥር ብሎክ 270 የወለል ቁጥር 0 የቦታው ስፋት 41.96 ካ/ሜ የሆነ እስትዲዮ ኮንደሚኒየም ቤት የመለያ ቁጥር AA000070901718270000I ካርታ ያለው የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 733,639.55 (ሰባት መቶ ሰላሳ ሶስት ሺህ ስድስት መቶ ሰላሳ ዘጠኝ ከ55/100) ሆኖ የትራክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ህዳር 29 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል:: የተጫራቾች ምዝገባ 4:30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል::
የሐራጅ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፤ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3:30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ c.P.O ማስያዝ ይኖርበታል:: ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም::
በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም c.P.O አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት:: በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን:: ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን::
