የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ህግን ተላልፈው የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በ04/03/2019 ዓ/ም በግልጽና በሐራጅ ጨረታ በአክሽን ኢትዮጵያ(auction Ethiopia) መተግበሪያ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ጉምሩክ ኮሚሽን አዋሽ ቅ/ፅቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ህግን ተላልፈው የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በ04/03/2019 ዓ/ም በግልጽና በሐራጅ ጨረታ በአክሽን ኢትዮጵያ(auction Ethiopia) መተግበሪያ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች መተግበሪያውን ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር auction Ethiopia ብለው በማውረድ ወይም www. auction.et ላይ በመመዝገብና የጨረታ ሰነዱን በማየት፣ የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች በሟሟላት በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ ሲሆን፣ የእቃዎችን ሳምፕልም ከአክሽን ኢትዮጵያ ድህረ-ገጽ (auction Ethiopia pape) ወይም አዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በአካል በመገኘት ወይም በቴሌግራም እንዲላክሎት በማድረግ ማየት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን::
የጨረታ መስፈርቶች:-
- ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚያስፈልጉ ተጫራች በጨረታ በሚሸጡ ዕቃዎች ጋር በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ:
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርትፍኬት፣ ዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑን ክሊራንስ (Clearance) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴያቸውን ለታክስ ማዕከሉ ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው የምስክር ወረቀት እና የመለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በሲስተም አታች ማድረግ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ቀን በ04/03/2019 ዓ/ም ከአክሽን ኢትዮጵያ ድህረ-ገጽ (action Ethiopia page) ማየት ይችላሉ::
- ለግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (cpo) የሚወዳደሩበት እቃ ኮድ 5 በመቶ እንዲሁም ለሐራጅ ጨረታ ለሚወዳደሩበት እቃ ኮድ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ አሰርተው በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስም በማስያዝ በሲስተም አታች ማድረግ ይኖርባቸዋል::
| ተ.ቁ | አጫራች ቅ/ጽ/ቤት | የጨረታው ዓይነት | ለጨረታ የቀረቡ ዕቃዎች | የዕቃዎች መመልከቻ ቀን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ | የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀን ሰዓት |
| 1 | አዋሽ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት | ግልጽ ጨረታ እና በሐራጅ | ጫማዎች አልባሳት፣ የመኪና መለዋወጫ የሞባይል ቀፎና አክሰሰሪ ኤሌክትሮኒክስ፣ ምግብ ነክ የስፖርት እቃዎች የእጅ ሰዓት ኮስሞቲክስ፣ መነፅር ጌጣጌጥ፣ የሳሙና ፋብሪካ አካል ማሽነሪ ተሽከርካሪ እና ሌሎች ልዩ ልዩ ዕቃዎች | ለግልጽና ለሐራጅ ጨረታ በ04/03/2019 - ከሰዓት 9:45 | ግልጽ ጨረታ መዝጊያ በ04/3/2019 ዓ/ም ከሰዓት 10:00 ሰዓት ሲሆን የሐራጅ ጨረታ የመጀመሪያ ጊዜ በ04/03/2019 ዓ/ም 11:00 ሰዓት ይሆናል። |
- የጨረታው መክፈቻ ሰዓት እና ቀንን ከአክሽን ኢትዮጵያ ድህረ-ገጽ auction Ethiopia page በማየት የጨረታው ሂደት ተጀምሮ ከማለቁ በፊት ዋጋ መስጠት ይችላሉ::
- ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ያስያዙት (CPO) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታ ውጤት ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል::
- አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ3 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን በመረከብ ከመጋዘን ማውጣት ይኖርበታል::
- ከላይ በተ.ቁ.7 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክበው ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታው ማስረከቢያ ያስያዙት ገንዘብ የከፈሉት ዋጋ ለኮሚሽኑ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል::
- ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊል ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- የአክሽን ኢትዮጵያ(auction Ethiopia) መተግበሪያን በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ሠራተኛ ለማግኘት በስልክ ቁጥር 09-05-11-55- 11/011-66-68-828 በመደወል ማግኘት ይችላሉ::
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 09-13-97-49-27 ይደውሉ::
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በጉምሩክ ኮሚሽን የአዋሽ ቅ/ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Awash Customs Branch invites buyers to bid online via Auction Ethiopia for seized goods, including shoes, clothing, vehicle parts, phones, electronics, food, cosmetics, machinery, a vehicle and more. Sector license, VAT and tax clearance required.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
