በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 03 የሚገኝ ህንጻ፣ ማሽኖችና ንብረቶች የሐራጅ ሽያጭ
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
በፍ/ባለሙብት እነ ትርሲት ታደሰ እና በፍ/ባለዕዳ እነ ካሳሁን ግዛው መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ በፌ/ከ/ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/183866 በቀን 22/10/2013ዓ/ም በመ/ቁጥር/01209 በቀን 13/08/2017ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 03 የኤች.ኢ.ኤፍ.ኬ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ስም ተመዝግቦ የሚገኝ ህንጻ እና ፡ ማሽኖች፡ እና የተለያዩ ንብረቶች የይዞታው የመለያ ቁጥር AA000060306103 የይዞታ ስፋት 452ካ/ሜ ይዞታው ለድርጅት አገልግሎት እየሰጠ ያለ ሆኖ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 140,591,777.58 ( አንድ መቶ አርባ ሚሊዮን አምስት መቶ ዘጠና አንድ ሺህ ሰባት መቶ ሰባ ሰባት ከ58/100) ሆኖ ካፒታል ጌን ታክስ ሻጭ የሚከፍል ሲሆን የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ለህዳር 30 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል:: የተጫራቾች ምዝገባ 4:30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል::
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለሙብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3:30 ብቻ በመገኘትና ባለሙብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት ¼ ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል:: ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም:: በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም C.P.O አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን:: ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን::
