Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Electric Utility (የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት)
  • Address ፒያሳ አካባቢ በሚገኛው አዲሱ የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ህንፃ 15ኛ ፎቅ የሰፕላይ ቼይን እና ንብረት ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-5-57-38-98
  • Websitehttp://www.ethiopianelectricutility.gov.et/
  • Deadline26 Nov 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceበነፃ (ከauction.et ይወርዳል)
  • Bid Securityብር 506,800 (CPO ወይም የባንክ ዋስትና)
  • opening dateህዳር 17 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 (online, auction.et)
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure , Disposal Sale , Electrical Materials

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያገለገሉ ስፑል ኢንሱሌተሮች (Spool Insulators) ሽያጭ

Ethiopian Electric Utility (የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት)


የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር ኢኤአ/ንአ/ግጨ-07/2019

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::

ተ.ቁየሚወገደው ንብረት ዓይነትየሚገኝበት ቦታመለኪያብዛትየጨረታ ማስከበሪያ (CPO)የጨረታ መዝጊያየጨረታ መክፈቻ
1Spool insulator 30/50 mmጎፋ ማዕከላዊ ዕቃ ግምጃ ቤትበቁጥር1,055,000506,800ህዳር 17 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:00ህዳር 17 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:30
2Spool insulator 70/50 mm183,347

ስለሆነም በጨረታው መካፈል የሚፈልግ ድርጅት ወይም ግለሰብ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ::

ማሳሰቢያ:- ውድድሩ የሚከናወነው ሙሉ በሙሉ በአክሽን ኢትዮጵያ አክሲዮን ማህበር በፈጠሩት የማወዳደሪያ ሲስተም መተግበሪያ auction.et መሰረት መሆኑን እየገለጽን፤ መስፈርቶቹ ከዚህ እንደሚከተለው ቀርበዋል:-

  1. በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ሆኖ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ወይም የታደሠ መታወቂያ ሊኖራቸው ይገባል::
  2. ስለጨረታው አካሄድ እና ንብረቶች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን ሰነድ የአክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ ከንብረቶቹ መግለጫ ስር ተያይዞ የሚገኝ ስለሆነ በነጻ አውርደው መመልከት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አክሽን ኢትዮጵያ አክሲዮን ማህበር ጋር ቀጠሮ በማስያዝ ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 3:00 እስከ 10:00 ሰዓት ንብረቶቹ በሚገኙበት ቦታ በመገኘት መመልከት ይቻላል::
  4. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት ዋጋ 15% ቫትን ጨምሮ ማቅረብ አለባቸው::
  5. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና(Bid Security) በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ስም ሲ.ፒ.ኦ. በማሰራት የአክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገባት ይችላሉ።
  6. ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች የጨረታውን ሂደት በቀጥታ (online) መከታተል ይችላሉ።
  7. ተጫራቾች የአክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር(Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም (auction.et) ላይ መመዝገብ እና መጫረት ይችላሉ።
  8. በጨረታው አሸናፊ ለምትሆኑ ተጫራቾች ለወደፊት አሸናፊነታችሁ ከሚገለፅበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር አምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የአሸነፋችሁበትን ዋጋ ሙሉውን ክፍያ ለወደፊት በምናሳውቃችሁ በተቋማችን ሂሳብ ቁጥር ገቢ በማድረግ የሽያጭ ውል ስምምነት የመፈጸም ግዴታ ይኖርባችኋል፤ ሆኖም ግዴታቸውን የማይወጡ ተጫራቾች ለውድድር ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ. ለተቋማችን ገቢ ይደረጋል::
  9. ከላይ የተጠቀሰውን እና በጨረታ ሠነዱ ላይ የተቀመጡ መመሪያዎችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ/ሊደረግ ይችላል::
  10. ተቋሙ ጨረታውን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል የሚችል ሲሆን በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
  11. የአክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በአጭር የስልክ መስመር 09-05-11-55-11 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
  12. ንብረቶቹን በተመለከተ በስልክ ቁጥር 011-1-11-98-97 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ::

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት

✨ messages.ai_summary
Ethiopian Electric Utility is selling, as-is via Auction Ethiopia (auction.et), spool insulators (30/50 mm and 70/50 mm sizes) held at its Gofa central store in Addis Ababa. Open to Ethiopian nationals with valid ID or trade licence; items can be viewed by appointment. Online auction.
Save Tender