Tender Detail

Tender Details

  • Company Belayab Cable Manufacturing PLC (በላይአብ ኬብል አምራች ኃ/የተ/ግ/ማ)
  • Address ዋና መስሪያ ቤት ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ላፍቶ ጋርመንት ኢንዱስትሪ መንደር : አዲስ አበባ እና አዳማ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0114711014
  • Websitehttps://belayabcableplc.com/
  • Deadline20 Nov 2026, 2:00 PM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ ብር 500.00 (የማይመለስ)
  • Bid Securityየሚያስገቡት ዋጋ 2% (CPO)
  • opening dateበዚሁ ዕለት ከቀኑ 8:30
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure , Vehicle

በላይአብ ኬብል አምራች ኃ/የተ/ግ/ማ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች (ኢቸር ደረቅ ጭነትና ዶንፌንግ ቫን) ሽያጭ

Belayab Cable Manufacturing PLC (በላይአብ ኬብል አምራች ኃ/የተ/ግ/ማ)


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

ድርጅታችን በላይአብ ኬብል አምራች ኃ/የተ/የግ/ማ የተለያዩ አይነት ያገለገሉ የተሽከርካሪዎች ከታች በዝርዝር የቀረቡትን ባሉበት ቦታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል::

ተ.ቁየመኪናው ዓይነትመኪናው የተሰራበት ዘመን እ.ኤ.አመኪናው የተሰራበት ሀገርየጭነት መጠንየሞተር ችሎታ (ሲሲ)ተሽከርካሪው የሚገኝበት ቦታ
1ኢቸር ካርጎ ደረቅ ጭነት 10.8 ሞዴል2013ህንድ2 ሰው እና 50.2 ኩንታል3298ዋና መ/ቤት አዲስ አበባ
2ዶንፌንግ የጭነት ቫን2015ቻይና1 ሰው እና 6 ኩንታል1053ዋና መ/ቤት አዲስ አበባ
  1. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 የስራ ቀናቶች በድርጅቱ ዋና መ/ቤት አዲስ አበባ በመቅረብ ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይኖርባቸዋል::
  2. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ተሽከርካሪ የሚያስገቡትን ዋጋ መጠን 2% የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ተሞልቶ ከጨረታ ሰነድ ጋር በማያያዝ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለጨረታው በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
  3. ተጫራቾች መኪኖቹን ባሉበት ቦታ ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ግማሽ ቀን በድርጅቱ የስራ ሰዓት በመገኘት መመልከት ይችላሉ::
  4. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው የስራ ቀን እና የጨረታ ሳጥኑ እስከሚታሸግበት 16ኛው ቀን እስከ 8:00 ሰዓት ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን በድርጅቱ ዋና መ/ቤት አዲስ አበባ ን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ለቡ ኢንዱስትሪ መንደር በአካል በመቅረብ ማስገባት ይኖርባቸዋል::ጨረታው በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8:30 ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል::
  5. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ የጨረታ አሸናፊ መሆናቸው በደብዳቤ ከተገለፀበት ቀን አንስቶ በ30 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን አጠቃላይ ዋጋ ከፍሎ ተሽከርካሪውን የማንሳት ግዴታ አለባቸው ይህ ካልሆነ የጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ የሚወረስ ይሆናል::
  6. ለተሽከርካሪ የስም ማዛወሪያና ተያያዥ ሌሎች ወጪዎች እና ከቦታ ለመንሳት የሚያስፈልጉ ማንኛውንም ወጪዎች ሙሉ በሙሉ በገዥ የሚሸፈን ይሆናል::
  7. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
  8. ስለ ጨረታው ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0939554606/ 0912503275 በመደወል ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ::

በላይአብ ኬብል አምራች ኃ/የተ/ግ/ማ

✨ messages.ai_summary
Belayab Cable Manufacturing PLC is selling two used vehicles as-is at its Addis Ababa head office: a 2013 Eicher 10.8 dry-cargo truck (India) and a 2015 Dongfeng cargo van (China). Vehicles can be inspected before bidding; the buyer covers transfer costs. Open bid sale.
Save Tender