Tender Detail

Tender Details

  • Company በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251112730852
  • Websitehttps://www.fsc.gov.et/
  • Deadline09 Dec 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityየመነሻ ዋጋ 1/4 (C.P.O በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
  • opening dateምዝገባው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ፣ የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ
  • Categories Land , House, Building And Warehouse , Sales, Disposals And Foreclosure

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 15 የሚገኝ G+2 ቤት የሐራጅ ሽያጭ

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት


የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለመብት ሜፋኮን ኮንስትራክሽን ሀ/የተ/የግ/ማ እና የፍ/ባለዕዳ ሚኪያስ ተስፋዬ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 261988 በግንቦት 9 ቀን 2016 ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/325034 በ12/11/2016ዓ.ም በኮ/መ/ቁ/325034 በ22/8/2018ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 15 በሚኪያስ ተስፋዬ ስም የተመዘገበ የይዞታ መለያ ቁጥር AA000080119656 በሴሪያል ቁጥር CL0201323 የቦታ ስፋት 72 ካ/ሜ የቤቱ ስፋት 161.70 ካ/ሜ G+2 ቤት የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 6,137,412 (ስድስት ሚሊዮን አንድ መቶ ሰላሳ ሰባት ሺህ አራት መቶ አስራ ሁለት) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ኅዳር 30 ቀን 2019 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል:: የተጫራቾች ምዝገባ 4:00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል::

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለሙብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3:30 ብቻ በመገኘትና ባለሙብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት ¼ ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል:: ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም:: በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም C.P.O አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን:: ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን::

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
The Federal Courts Judgment Execution Office auctions, by court order, a titled G+2 house (161.70 m² on a 72 m² plot) in Nifas Silk Lafto sub-city, Woreda 15, Addis Ababa. The buyer pays transaction tax; site visits by arrangement through the auction section. Public auction.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender