የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ል/መምሪያ የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጀር፣ ATS እና የሊፍት ዕቃዎች ግዥ
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ል/መምሪያ
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና /ኢኮ/ልማት መምሪያ
የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ ለሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በታቀደው መሠረት የተለያዩ እቃዎችን ለመግዛት በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ማስታወቂያ አወዳድሮ በዘርፉ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች መካከል በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::
በዚህ መሠረት:-
- የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረግያ፣ ሎት/ምድብ 01(አንድ)
- ATS፤ ሎት/ምድብ- 02(ሁለት)
- የሊፍት ዕቃዎች ሎት/ምድብ- 03(ሶስት)
በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድረጅቶች መወዳደር ይችላሉ:-
- በዘርፉ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው አቅራቢዎች፤-
- በሥራ መስኩ ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መከፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፣
- የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፣
- በጨረታው እንዲሳተፍ የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ አለበት፤
- የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተ ዳደር ፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ ቢሮ አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 54 (ሃምሳ አራት) በመቅረብ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 /አስር/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቀርባችሁ ሰነድ በብር፣ 500 (አምስት መቶ ብር) በመግዛት ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ ይችላሉ።
- ተጫራቾች በየሎት 01 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) እንዲሁም ለሎት 02 ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር)እና ሎት 03 ብር፣ 100000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ የተመሰከረለት ሲፒኦ (cpo) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለበት
- ጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቬሎፕ አንድ ኦሪጂናል እና ሁለት ኮፒ ፋይናንሻል እና ቴክኒካል አንድ ኦሪጂናል እና ሁለት ኮፒ ሰነዶችን አሟልቶ በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10(አስር) ተከታታይ ቀናት በፋይ/ኢኮ/ልማት/ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 54 (ግዢ ኬዝ ቲም) ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
- አስፈላጊ የሆኑ ቴክኒካል ጉዳዮች በሚሸጥ ሰነድ ውስጥ በተቀመጠው መስፈርት መሠረት የሚገመገም ስለሆነ በጥንቃቄ መዘጋጀት ይጠበቅበታል፤
- የሚገዙት ዕቃዎች እስቶክ ውስጥ መኖራቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ጨረታው በሚከፈትበት ቀን መቅረብ አለበት (እስቶክ ውስጥ መኖሩ ግዴታ ነው)::
- ጨረታው በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4:00 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ከረፋዱ 4:30 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 54 ይከፈታል::ይህ ቀን በበዓላት ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት የሚታሽግና የሚከፈትበት ቀን ይሆናል:: የበዓል ቀን ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል::
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ስልክ ቁጥር 046-212-13-34
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና /ኢኮ/ል/መምሪያ
ሀዋሳ
✨ messages.ai_summary
Hawassa City Administration Finance and Economic Development Department seeks suppliers for the Mayor's Office in 3 lots: electric vehicle chargers, ATS (automatic transfer switch) and lift parts, which must be in stock. Bidders need a renewed licence, supplier registration and tax clearance.
