Tender Detail

Tender Details

  • Company የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት ደ/ብርሃን
  • Address ሰሜን ሸዋ ዞን ደ/ብርሃን ከተማ ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: ----------
  • Website
  • Deadline13 Dec 2026, 10:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityያሸነፉበት ዋጋ 1/4 (ሲፒኦ)
  • opening dateታህሳስ 04 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት፣ ንብረቱ በሚገኝበት በኮቱ ከተማ 01 ቀበሌ
  • Categories Land , House, Building And Warehouse , Sales, Disposals And Foreclosure

የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በኮቱ ከተማ የሚገኝ ቤት የሐራጅ ሽያጭ

የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት ደ/ብርሃን


ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ጨረታ ማስታወቂያ

በአፈ/ከሣሽ ፀደይ ባንክ እና በአፈ/ተከሳሽ እነ አሰግደዉ ደስታ /5ሰዎች/ መካከል ስለአለው የአፈጻጸም ክስ ክርክር ጉዳይ በአፈ/ተከሳሽ አሰግደዉ ደስታ ስም የተመዘገበና በኮቱ ከተማ የሚገኝ በምስራቅ ሽመልስ ዉጣባቸዉ ፤በምዕራብ አመዘነች ታደሰ፤ በሰሜን መንገድ፤በደቡብ አበባየሁ ደምሴ የሚያዋስነዉ በ182 ካ/ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ ቤት በመነሻ ዋጋ ብር 917,845.76 /ዘጠኝ መቶ አስራ ሰባት ሺህ ስምንት መቶ አረባ አምስት ብር ከሰባ ስድስት ሳንቲም/ ታህሳስ 04 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት ንብረቱ በሚገኝበት በኮቱ ከተማ 01 ቀበሌ በጨረታ እንዲሸጥ ፍ/ቤቱ አዟል::

በመሆኑም:-

  1. ተጫራቾች ያሸነፉበትን 1/4 ገንዘብ በሲፒኦ ወዲያውኑ የማስያዝ ግዴታ አለባቸው::
  2. ተጫራቾች ማንነታቸውን ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የማቅረብ ግዴታ አለባቸው::
  3. ንብረቱን ለመሸጥ ምክንያት የሆነው እንደፍርዱ ለማስፈፀም ነው::
  4. ገዥው በጨረታ ለገዛው ንብረት ዋጋውን ሳይከፍል የቀረ እንደሆነ ወይም በህግ በተወሰነው በዚሁ የሽያጭ ማስታወቂያ ላይ በተገለፀው መሠረት ዋጋውን ያላስቀመጠ እንደሆነ ሽያጩ ይሠረዛል በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ/429/2/ መሠረት ለሃራጅ ማስታወቂያው የተደረገውን ወጪ እንዲከፍል ይገደዳል::
  5. የሐራጅ ማስታወቂያውን ለማቋረጥ የሚቻልበት የተሻለ መንገድ ካለ የጨረታ ማስታወቂያው በማንኛውም ጊዜ ሊቋረጥ ይችላል::

የሰ/ሸዋ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት
ደ/ብርሃን

✨ messages.ai_summary
The North Shewa Zone High Court (Debre Birhan) is auctioning, by court order, a house on a 182 m² plot in Kotu town, kebele 01, in a judgment execution case brought by Tsedey Bank. The auction is held at the property site. First-round public auction.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender