የብርብር ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት ዩኒት የጽህፈት መሣሪያና አላቂ የቢሮ ዕቃ ግዥ
በጋሞ ዞን የብርብር ከተማ አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የብርብር ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት ዩኒት በ2019 በጀት ዓመት ለሴክተር መ/ቤቶች -
1. የጽህፈት መሣሪያና አላቂ የቢሮ ዕቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::
በዚሁ መሠረት ተጫራቾች:-
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለውና የዘመኑን ግብር የከፈለ፤
- የግብር ከፋይነት ቲን ነምበር ያለው፤
- በተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገበ፤
- የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው፤
- የመኪና ኪራይ የጫኝ እና አውራጅ በአሸናፊ ድርጅት የሚሸፈን ይሆናል::
- ንብረቶችን እስከ ብርብር ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት ዩኒት ገቢ ደረስ ለማድረስ ፍቃደኛ የሆን
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለጽህፈት መሣሪያና ለአላቂ የቢሮ ዕቃ ግዥ ብር 10 አስር ሺህ ብር ብቻ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል::
- ተጫራቾች ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት15 ተከታታይ የሥራ ቀናት በብርብር ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ዩኒት በመቅረብ የማይመለስ 300 (ሦስት መቶ ብር ብቻ ለጨረታ ሰነድ በመክፈል እና ደረሰኝ በመያዝ የጨረታ ዝርዝር የያዘውን ሰነድ ከብርብር ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ስማት ዩኒት 1ኛ ፎቅ ከቢሮ ቁጥር 01 መግዛት ይቻላል::
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦሪጅናሉንና ኮፒውን ለየብቻ በማሸግ ሙሉ አድራሻውን በመግለጽ በአንድ እናት ፖስታ በመክተት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን እንዲጨምሩ እያሳሰብን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ በወጣ በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4:00 ይታሸጋል:: የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን በተጠቀሰው በሥራ ሰዓት ይታሸጋል::
- ጨረታው በ16ኛው የሥራ ቀን ልክ ከቀኑ 8:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል::የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል::
- የጨረታ አሸናፊው ድርጅት የአሸናፊነት ደብዳቤ በተጠቀሰው በ7ኛው ቀን የውል ማስከበሪያ 10% በመያዝ ውል ይፈራረማል::
- የጨረታ ሣጥን በብርብር ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት ዩኒት 1ኛ ፎቅ በቢሮ ቁጥር 01 ላይ ይገኛል::
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው::
የብርብር ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት ዩኒት
✨ messages.ai_summary
Birbir City Administration Finance and Plan Development Unit seeks suppliers of stationery and office consumables for its sector offices. Bidders need a renewed licence, TIN, VAT and supplier registration and must deliver to the unit. Open bid.
