የላስታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግንባታ እቃዎች፣ ሲሚንቶ፣ የመኪና ጎማ፣ ጣውላ፣ የጽህፈት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የጽዳት፣ የስፖርትና የፕላስቲክ እቃዎች ግዥ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ወሎ አስተዳደር ዞን የላስታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨ/ መለያ ቁጥር ግ/ን/እ/ስ/:-18/2019
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ወሎ አስተዳደር ዞን የላስታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለላስታ ወረዳ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል:- ሎት01ቆርቆሮ ሚስማር ብረታ ብርትና ሌሎች የግንባታ እቃዎች ፤ ሎት 02 የሲሚንቶ አቅርቦት ፤ ሎት የመኪና ጎማ ፤ ሎት4 ጣውላ ፤ሎት 05 የጽህፍት መሳሪያ፤ ሎት06 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ፤ሎት 07 የጽዳት እቃዎች፤ ሎት 08 የስፖርት ትጥቅ፤ ሎት 09 HDEP/ፕላስቲክ/እቃዎች ግዥ በመደበኛና በተራድኦ በጀት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል::
በመሆኑም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው::
- በአዲሱ የንግድ አዋጅ መሠረት የእያንዳንዱ ሎት የተናጠል በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ፤የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን ነበር/ ሰርተፍኬት ያላቸውና፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑን የሚገልጽ የግብር ክሊራንስ ፤ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወርቀት እና የሚሞሉት ዋጋ ከ500000/አምስት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ሰርተፍኬት ማቅርብ አለባቸው::
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ላስታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁ.3 በመቅረብ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ የኢ.ት.ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል መግዛት ይችላሉ::
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች ለሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ለጨረታ ማስከበሪያ በተጫራቾች መመሪያ በተ.ቁ 8 ላይ የተገለጸውን የገንዘብ መጠን ለእያንዳንዱ ሎት ለየብቻ ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO)፤ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (BID BOND)፡ በባንክ በተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት በማሰራት ማስያዝ ይኖርባቸዋል:: የጨረታ ማስከበሪያው ከፖስታው ውስጥ አብሮ መግባት ይኖርበታል::
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት የመጀመሪያው ቀን አንስቶ የሚቆጠር ለ10 ተከታታይ ቀናት ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆይና በ11ኛው ቀን:- ሎት 01 ቆርቆሮ ሚስማር ብረታ ብርትና ሌሎች የግንባታ እቃዎች፤ሎት 02 የሲሚንቶ አቅርቦት እቃዎች ፤ ሎት4 ጣውላ ፤ሎት09 HDEP/ፕላስቲክ/እቃዎች ጠዋት 3:45 ታሽጎ 4:00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል:: እንዲሁም በዚሁ ቀን :-ሎት 05 የጽህፍት መሳሪያ፤ ሎት 06 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፤ ሎት 07 የጽዳት እቃዎች፤ ሎት 08 የስፖርት ትጥቅ፤ ሎት 03 የመኪና ጎማ ከሰዓት 8:15 ታሽጎ 8:00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል::
- የተጠቀሰው ቀን ቅዳሜ፣ እሁድ ወይም በካላንደር ዝግ ከሆነ ለሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ይተላለፉና ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ላስታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 ይከፈታል::
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሠነዳቸውን ኮፒና ኦርጂናል በተለያየ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ውስጥ ማስገባት አለባቸው::
- አሸናፊው አካል እቃዎችን በራሱ ትራንስፖርት ላስታ ወረዳ ሴ/መ/ቤቶች መጋዘን ድረስ አጓጉዞ ማቅረብ ይኖርበታል::
- የጨረታ መዝጊያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም::
- ተጫራቾች በአንድ ሎት ውስጥ የተዘረዘሩትን የእቃ አይነቶች ከፋፍሎ መሙላት አይቻልም ውድድሩ በየሎት ምድብ ጥቅል ድምር ስለሆነ የሁሉም እቃ ዋጋዎች መሞላት አለበት::
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::
- ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ወይም ማብራሪያ ከፈለጉ በአካል በመቅረብ ወይም ከዚህ በታች በተጠቀሱት ስልክ ቁጥሮች 0333360124፤ ወይም 0984148804 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ::
የላስታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Lasta Woreda Finance Office (North Wollo, Amhara) seeks suppliers in 9 lots: corrugated sheets, nails and steel, cement, tyres, timber, stationery, electronics, cleaning items, sportswear and HDPE plastic items. Bidders need a renewed licence, TIN, tax clearance and VAT where required. Open bid.
