Tender Detail

Tender Details

  • Company የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address ቡታጅራ ፡ ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 046-145-67-77
  • Website
  • Deadline13 Nov 2026, 5:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 1000.00
  • Bid Securityየቦታ ስፋት × መነሻ ዋጋ 20% (CPO)
  • opening dateበሚቀጥለው የስራ ቀን ከቀኑ 2:30 ሰዓት፣ በቡታጅራ ከተማ ሴራና የመሰብሰቢያ አዳራሽ
  • Categories Land , House, Building And Warehouse

የቡታጅራ ከተማ ማዘጋጃ ቤት በአዋጅ በተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት መሠረት የ2019 1ኛ ዙር የሊዝ ጨረታ በአሬሻ በአረንዛፍ እና ዘቢዳር ቀበሌዎች ለንግድና ኢንቨስትመንት የሚሆን ቦታ በሊዝ ጨረታ አወዳድሮ ለማስተላለፍ ተወዳዳሪዎችን ይጋብዛል::

የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት


የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

የቡታጅራ ከተማ ማዘጋጃ ቤት በአዋጅ በተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት መሠረት የ2019 1ኛ ዙር የሊዝ ጨረታ በአሬሻ በአረንዛፍ እና ዘቢዳር ቀበሌዎች ለንግድና ኢንቨስትመንት የሚሆን ቦታ በሊዝ ጨረታ አወዳድሮ ለማስተላለፍ ተወዳዳሪዎችን ይጋብዛል::

  1. የጨረታው ዓይነት መደበኛ ጨረታ
  2. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በማዘጋጃ ቤቱ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ዘርፍ ቢሮ በመቅረብ ዝርዝር የጨረታ ሰነድ 1000 /አንድ ሺህ/ ብር በመግዛት መወዳደር ይችላሉ::
  3. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ለቦታው የሚያቀርቡትን ዋጋ፣ የሚከፍሉትን የሊዝ ቅድም ክፍያ ወይም ለንግድና ኢንቨስትመንት 20% መከፈል የሚችል በጨረታ መወዳደሪያ ሰነድ ላይ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡
  4. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና መጠን የጠቅላላ የቦታው ስፋት በመነሻ ዋጋ ተባዝቶ ከሚገኘው ውጤት 20 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የገንዘብ ክፍያ ትዕዛዝ /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል::
  5. የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የሚጠናቀቀው ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከተነገረበት ቀን ጀምሮ በአስረኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 10:00 ሰዓት ሆኖ የጨረታ ሣጥን የሚታሸገው በዕለቱ ከቀኑ 11:00 ይሆናል:: ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቡታጅራ ከተማ ሴራና የመሰብሰቢያ አዳራሽ ከቀኑ 2:30 ሰዓት ይከፈታል::
  6. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነድ በሁሉም ገጽ ላይ ሙሉ ስማቸውን ፣ ፊርማቸውን፣ የመኖሪያ አድራሻቸውንና ስልካቸውን ማስፈር አለባቸው::
  7. ጨረታ ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሣብ ላይ ለውጥ /ማሻሻያ/ ማድረግና ከጨረታው ራሣቸውን ማግለል አይችሉም::
  8. ተጫራቾች ለጨረታ የሚያቀርቡትን የጨረታ ዋጋ በአሃዝና በፊደል መግለፅ አለባቸው ሆኖም የአሃዝና የፊደል ልዩነት ካለ በፊደል የተፃፈው ገዢ ይሆናል::
  9. ተጫራቾች የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያቸውን ሞልተው ካስገቡ በኋላ ሰነድ በመሰረዝ በምትኩ ሌላ የጨረታ ሰነድ ማስገባት አይችሉም::
  10. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የቅድመ ክፍያ መጠን ከአጠቃላይ የሊዝ ክፍያ 20% ማነስ የለበትም::
  11. የጨረታው አሸናፊ ተለይቶ በማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በይፋ ከተገለጸ በኋላ በጨረታው የተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ቦንድ /CPO/ ጨረታው ከተፈፀመ በኋላ ካለው የሥራ ቀን ጀምሮ ተመላሽ ይደረጋል፡
  12. አንድ ተጫራች በአንድ የጨረታ ዙር ከአንድ የጨረታ ሰነድ በላይ መግዛት አይችልም::
  13. ተጫራቾች ለጨረታ የቀረቡትን ቦታዎች ጨረታው በጋዜጣ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10/አስር/ ቀናት ጠዋት ከ2:30 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት ቦታዎችን በመዘዋወር መመልከት ይችላሉ::
  14. ሌላ ተጫራች በሚሠጠው ዋጋ ላይ በመንተራስ ዋጋ መስጠት አይቻልም::
  15. በጨረታው ሂደት ላይ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ካልተገኙ የጨረታው ሂደት በሌሉበት የሚከፈት ይሆናል::
  16. ተጫራቾች ጨረታውን ለማሸነፍ ተገቢ ያልሆነ አድራጐት ከፈፀሙ ወይም የጨረታው ሂደት ለማዛባት ከሞከሩ ከጨረታው የሚታገዱ እና ያስያዙት /CPO/ ለመንግሥት ገቢ እደሚደረግና በአመቱ በሚካሄዱ ጨረታዎች የማይሣተፉ ይሆናል::
  17. አሸናፊ ተጫራች አሸናፊ መሆኑ በማዘጋጃ ቤቱ የማስታወቂያ ሰሌዳ ከተገለጸበት ቀን ጀምሩ ባሉ ተከታታይ አስር የስራ ቀናት ውስጥ በመቅረብ ያስገባውን ቅድመ ክፍያ በመከፈል ውል መግባት ይኖርበታል::

ማዘጋጃ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ጨረታውን ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

በቡታጅራ ከተማ ማዘጋጃ ቤት በ2019 ዓ.ም. የበጀት ዓመት ለአንደኛ ዙር ለሊዝ ጨረታ ለንግድና ኢንቨስትመንት የቀረቡ ቦታዎች መግለጫ

ተ.ቁ ቦታው የሚገኝበት አካባቢ የቦታው ስፋት በካሬ ሜትር ቀበሌ የቀረበ ፕሎት ብዛት የቦታው ደረጃ ብሎክና ፕሎት የቦታው አገልግሎት የሚገነባው ህንጻ ከፍታ የጨረታ መነሻ ዋጋ የሊዝ ዘመን የጨረታ ዓይነት የክፍያ ማጠናቀቂያ የጨረታ ሰነድ መሸጫ ዋጋ
1 ሀይሌ ወፍጮ ፊት ለፊት 650 አረንዛፍ 1 1ኛ EMB1P1 ንግድና ኢ/ት G+4ና በላይ 1529.30 70 መደበኛ 40 1000.00
2 አድማሱ ቶርኖ በስተምስራቅ 500 አረንዛፍ 1 1ኛ ADHP2 ንግድና ኢ/ት G+4ና በላይ 1529.30 70 መደበኛ 40 1000.00
3 መስቃን ወረዳ ፖሊስ መግቢያ በስተቀኝ (ፊት ለፊት) 600 አረንዛፍ 1 1ኛ MPP1 ንግድና ኢ/ት G+4ና በላይ 1529.30 70 መደበኛ 40 1000.00
4 አሊ አንጩት ቤት ፊት ለፊት ፈረሳት ምግብ ቤት ጎን 290 ዘቢዳር 1 1ኛ DFP1 ንግድና ኢ/ት G+4ና በላይ 1529.30 70 መደበኛ 40 1000.00
5 የቀድሞ ዘማር ሆቴል አካባቢ ዴዝሞ ክለብ ፊት ለፊት 650 አሬሻ 1 1ኛ UNB3P1 ንግድና ኢ/ት G+4ና በላይ 1529.30 70 መደበኛ 40 1000.00
6 አሜግ ሆቴል በስተምስራቅ አሬሻ ቀበሌ ጎን 350 አሬሻ 1 1ኛ AMBP3 ንግድና ኢ/ት G+4ና ላይ 1529.30 70 መደበኛ 40 1000.00
7 መናህሪያ መግቢያ ምንጭ ቁርስ ቤት 390 አረንዛፍ 1 1ኛ BSP1 ንግድና ኢ/ት G+6ና በላይ 1529.30 70 መደበኛ 40 1000.00

በቡታጅራ ከተማ ማዘጋጃ ቤት በ2019 ዓ.ም. የበጀት ዓመት ለአንደኛ ዙር ለሊዝ ጨረታ ለንግድና ኢንቨስትመንት የቀረቡ ቦታዎች መግለጫ

ተ.ቁ ቦታው የሚገኝበት አካባቢ የቦታው ስፋት በካሬ ሜትር ቀበሌ የቀረበ ፕሎት ብዛት የቦታው ደረጃ ብሎክና ፕሎት የቦታው አገልግሎት የሚገነባው ህንጻ ከፍታ የጨረታ መነሻ ዋጋ የሊዝ ዘመን የጨረታ ዓይነት የክፍያ ማጠናቀቂያ የጨረታ ሰነድ መሸጫ ዋጋ
8 ቀና ማዘጋጃ አካባቢ አቡጊዳ ጂም ጀርባ 390 አረንዛፍ 1 1ኛ MBP1 ንግድና ኢ/ት G+4ና በላይ 1529.30 70 መደበኛ 40 1000.00
9 መስቃን ወረዳ አስተዳደር ፊት ለፊት 260 አረንዛፍ 1 1ኛ MWP1 ንግድና ኢ/ት G+6ና በላይ 1529.30 70 መደበኛ 40 1000.00
10 ከሴራና ወደ ንግድ ባንክ መሄጃ በስተግራ 340 አረንዛፍ 1 1ኛ MWP1 ንግድና ኢ/ት G+4ና በላይ 1529.30 70 መደበኛ 40 1000.00
11 ከመስቃን ወረዳ ፖሊስ ወደ ሴራና አዳራሽ መሄጃ በስተግራ 450 ዘቢዳር 1 1ኛ MPP2 ንግድና ኢ/ት G+4ና በላይ 1529.30 70 መደበኛ 40 1000.00
12 ሳውዘርን ሆቴል ጀርባ 352 አሬሻ 1 1ኛ SH2P1 ንግድና ኢ/ት G+4ና በላይ 1529.30 70 መደበኛ 40 1000.00
13 ሳውዘርን ሆቴል ጀርባ 245 አሬሻ 1 1ኛ SH2P1 ንግድና ኢ/ት G+4ና በላይ 1529.30 70 መደበኛ 40 1000.00
14 አሜግ ሆቴል በስተደቡብ ህብረት ግሮሰሪ ፊት ለፊት 600 አሬሻ 1 1ኛ AMB2P1 ንግድና ኢ/ት G+4ና ላይ 1529.30 70 መደበኛ 40 1000.00

የቡታጅራ ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Butajira City Finance Office (Central Ethiopia) offers 14 urban plots of 245 to 650 m² in Arenzaf, Zebidar and Aresha kebeles on 70-year lease by auction for trade and investment use, with G+4 or G+6 and above buildings required. First-round lease auction.
Save Tender