በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 10 የሚገኝ መኖሪያ ቤት የሐራጅ ሽያጭ (በድጋሚ የወጣ)
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
ድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለሙብት ፍሬህይወት አንዳርጋቸው እና የፍ/ባለዕዳ እነ ከተማ ትሳሱ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/209765 በ15/03/2018 ዓ.ም እና . በኮ/መ/ቁ/212955 በ07/05/2018ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በን/ስ/ላ/ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ውስጥ የሚገኝ የቤት ቁጥር አዲስ በመስከ ልኬት የተገኘ የቦታ ስፋቱ 99.04 ካ/ሜ የሆነ ሰነድ አልባ ማህደር ያለው ይዞታው ቤቱ መብት ያልተፈጠረለት እና ካርታ ያልወጣለን ሰነድ አልባ ስለሆነ ከፍ/ባለዕዳ ወደ ገዥው ይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ሳይኖረው የስም ዝውውር አገልግሎት ለመስጠት የማይቻል ሲሆን ነገር ግን በአዲስ አበባ ከተማ መ/ል/አስ/ቢሮ በመብት ፈጠራ ቡድን በኩል መመሪያ እና አሰራር የሚፈቅደውን አሟልተው ከተገኙ ለገዥ መብት በመፍጠር በስሙ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ተዘጋጅቶ የሚሰጠው ሲሆን አዋሳኞቹ በሰሜን የመሰረት ማሞ ቤት በደቡብ የእግር መንገድ በምስራቅ የጸዳለ አለሙ ቤት በምዕራብ የእግር መንገድ የሚያዋስኑት የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 3,055,335.20 (ሶስት ሚሊዮን ሃምሳ አምስት ሺህ ሶስት መቶ ሰላሳ አምስት ከ20/100) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ጥቅምት 3 ቀን 2019 ዓ.ም በሐራጅ ለመሸጥ ቀጠሮ የተያዘ ቢሆንም በዕለቱ ተጫራች ባለመቅረቡ ምክንያት ጨረታው ሳይከናወን ቀርቷል:: ስለሆነም በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.212955 በቀን 11/02/2019 ዓ.ም በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት በድጋሚ ሐራጅ ጨረታ ሆኖ 1/4ኛ ብር 763,833.80 ( ሰባት መቶ ስልሳ ሶስት ሺህ ስምንት መቶ ሰላሳ ሶስት ከ80/100) በማስያዝ መሳተፍ የሚቻል ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ህዳር 28 ቀን 219 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል::የተጫራቾች ምዝገባ 4:00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል::
የሐራጅ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለሙብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3:30 ብቻ በመገኘትና ባለሙብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል:: ከ1/4ው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም:: በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም C.P.O አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን::
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን::
