Tender Detail

Tender Details

  • Company Amhara Bank S.C (አማራ ባንክ አ.ማ)
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-558-2660
  • Website
  • Deadline04 Dec 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityተጫራቾች የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ ወይም ሃያ አምስት በመቶ (25%) በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ (C.P.O) ብቻ በአማራ ባንክ አ.ማ ስም በማሰራት፣ በማስያዝ እና በመመዝገብ በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ::
  • opening dateህዳር 25 ቀን 2019 ዓ.ም ከ 4:00 እስከ 5:00 ሰዓት አማራ ባንክ አ.ማ ባ/ዳር ዲስትሪክት ቢሮ (ባ/ዳር)
  • Categories Land , House, Building And Warehouse , Sales, Disposals And Foreclosure , Disposal Sale

አማራ ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሠረት ከዚህ ቀጥሎ የቀረበውን ንብረት በግልጽ የሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Amhara Bank S.C (አማራ ባንክ አ.ማ)


የሐራጅ ማስታወቂያ

ቁጥር አማራ ባንክ/57/2019

አማራ ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሠረት ከዚህ ቀጥሎ የቀረበውን ንብረት በግልጽ የሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ

ተ.ቁየተበዳሪው ስምየንብረት አስያዥ ስምአበዳሪው ቅርንጫፍየንብረቱ አድራሻየቦታው ስፋትየባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ ቁጥርየንብረቱ ዓይነት/ የይዞታው አገልግሎትየጨረታ መነሻ ዋጋ /ብር/ጨረታው የሚከናወንበት
ከተማክ/ከተማወረዳቀበሌቀንሰዓትቦታ
1አቶ ሀብታሙ ሙጬ ተገኘአቶ ሙጬ ተገኘ የኋላባህር ዳርባህር ዳርጣና-16249 ካ.ሜ302/2004ለመኖሪያ6,481,568.33ህዳር 25 ቀን 2019 ዓ.ምከ 4:00 እስከ 5:00 ሰዓትአማራ ባንክ አ.ማ ባ/ዳር ዲስትሪክት ቢሮ (ባ/ዳር)

ማሳሰቢያ

  1. ተጫራቾች የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ ወይም ሃያ አምስት በመቶ (25%) በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ (C.P.O) ብቻ በአማራ ባንክ አ.ማ ስም በማሰራት፣ በማስያዝ እና በመመዝገብ በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ::
  2. ከፍተኛ ዋጋ የሰጠው ተጫራች የጨረታው አሸናፊ ነው የሚባለው ከባንኩ አሸናፊነቱን የሚገልጽ ደብዳቤ በጽሁፍ ሲደርሰው ብቻ ነው::
  3. የጨረታ አሸናፊው አሸናፊ መሆኑ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት/ ቀናት ውስጥ ቀሪውን ገንዘብ አጠናቆ መክፈል ይኖርበታል:: ባይከፍል ግን የሐራጁ ውጤት ተሰርዞ ያስያዘው ሲፒኦ አይመለስለትም፤ ለባንኩ ገቢ ይሆናል:: በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሃራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል:: ላላሸነፉት ተጫራቾች ግን ያስያዙት ሲፒኦ በእለቱ ይመለስላቸዋል::
  4. የሐራጁ አሸናፊ /ገዥ/ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን የሊዝን ክፍያን ጨምሮ፣ ግብር፣ በዋጋው ላይ ሚታሰብ ተጨማሪ እሴት ታክስ (15%) ካለ ከስም ማዘዋወሪያ ጋር የተገናኙ እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በህግ የተወሰኑ ታክስ እና ግብሮች ገዥው/አሸናፊው/ ይከፍላል::
  5. ተጫራቾች በሃራጅ ለመሳተፍ ሲመጡ መታወቂያ (የቀበሌ፣ የመንጃ ፍቃድ፣ ፓስፖርት ወይም ብሄራዊ መታወቂያ) መያዝ ይገባቸዋል:: ተጫራቾች የህግ ሰውነት የተሰጣቸው አካላት ከሆኑ ደግሞ ህጋዊ ሰውነት ያገኙበትን የዋና ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ሃራጁን ለመሳተፍ የቀረበው ግለሰብ ስልጣኑን የሚያሳይ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት የጸደቀ መመስረቻ ጽሁፍ(የመተዳደሪያ ደንብ)፣ ቃለጉባኤ ወይም የውክልና ሰነድ ይዞ መቅረብ አለበት::
  6. ንብረቱ በገዢው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል::
  7. ለሐራጅ የቀረበውን ንብረት ለመጎብኘት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የጉብኝት ፕሮግራም ከወርካውትና ሪከቨሪ ክፍል ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በማስያዝ ጨረታው ከመካሄዱ ከ5 ቀን በፊት መጎብኘት ይችላል::
  8. ጨረታው በሰንጠረዡ ላይ በተጠቀሰው ቀን፣ ሰዓትና ቦታ ተጫራቾች፣ ተበዳሪ እና ንብረት አስያዥ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት ይካሄዳል:: ነገር ግን ተበዳሪውም ሆነ መያዣ ሰጪው ባይገኙ ጨረታው በሌሉበት ይካሄዳል::
  9. ንብረቱን/ቶቹን በጨረታ አሸንፎ የገዛ ግለሰብ/ድርጅት የሽያጭ ገንዘቡን ከፍሎ ባጠናቀቀ በ15 ቀናት ጊዜ ውስጥ ንብረቱን መረከብ ያለበት ሲሆን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ንብረቱን ካልተረከበ በንብረቱ ላይ ለሚደርስ ጉዳት ባንኩ ኃላፊነት አይወስድም:: ገዥው በተጠቀሰው ጊዜ ንብረቶቹን ካልተረከበ ከንብረቶቹ ጋር በተያያዘ ለሚኖር ወጪ ኃላፊነቱን ይወስዳል::
  10. በባንኩ የብድር ፖሊሲ፣ መመሪያ እና ቅድመ ሁኔታ መሰረት የሚፈለገውን ማስረጃ አሟልቶ ለቀረበ የጨረታ አሸናፊ ባንኩ ፤ እስከ 100% ድረስ ብድር ሊያመቻች ይችላል::
    በንብረቱ ላይ የምርት ተግባር ለሚያከናውኑ ገዥዎች ባንኩ ተጨማሪ ብድር ሊያመቻች ይችላል::
    በተጨማሪም ለባንኩ የተሻለ ጥቅም የሚያስገኝ ከሆነ ባንኩ ለመደራደር ዝግጁ ነው::
  11. የተጫራቾች ምዝገባ ከሃራጁ መዝጊያ ሰአት 30 ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል::
  12. ለበለጠ ማብራሪያ አማራ ባንክ አ.ማ 0115 58 27 64 ወይም 0115-58 41 89 በስራ ሰአት ደውለው መጠየቅ ይችላሉ::
  13. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው:
  14. በወንድ አንቀጽ የተጠቀሰው ለሴት እና ህጋዊ ሰውነት ላላቸው ድርጅትም ያገለግላል::

አማራ ባንክ አ.ማህበር

✨ messages.ai_summary
Amhara Bank re-advertises the auction of a foreclosed residential property on a 249 sq m plot in Tana sub-city, Kebele 16, Bahir Dar, sold as is. The bank may finance up to 100% for qualifying winners.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender