የቡሌ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ጽ/ቤት የእስቴሽነሪ፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ እና ፈርኒቸር ግዥ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጌዴኦ ዞን የቡሌ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጌዴኦ ዞን በቡሌ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ጽ/ቤት ለተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የጽሕፈት መሳሪያዎችን ለመግዛት ይፈልጋል። በዚሁ መሰረት በምድብ 1 እስቴሽነሪ በምድብ 2 የጽዳት ዕቃዎች በምድብ 3. ኤሌክትሮኒክስ በምድብ 4 ፈርኒቸር ብቁ ከሆኑ ተጫራቾች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው/ያላት
- የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ ያለው/ያላት
- የግብር ከፋይነት ቲን ቁጥር ያለው/ያላት
- ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ወቅታዊ የግብር ክፍያ ማረጋገጫ፣ ማቅረብ የሚችል/የምትችል
- የቫት የምዝገባ ሰርተፍኬት፣ ያለው/ያላት
- የአቅራቢዎች ስም ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸው የሚገልጽ ማስረጃና ሌሎች ሰነዶችን ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች በጽ/ቤቱ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 400.00 (አራት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ ከጽ/ቤቱ ግዥ ኬዝ ቲም ቢሮ ቁጥር 3 መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 20000.00 (ሃያ ሺህ ብር) ብቻ በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ወይም በሲፒኦ (CPO) በቡሌ ወረዳ ፋ/ፕ/ጽ/ቤት ስም አሰርተው ጨረታ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በታሸገ ፖስታ የዋጋና ቴክኒካል የጨረታ ሰነድ ማስገባት አለባቸው። ነገር ግን ጨረታ በሚከፈትበት ቀን ዘግይቶ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።
- የጨረታ ሰነድ ለ21 ተከታታይ የሥራ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን ማቅረቢያ ጊዜ እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ በ22 ቀን ጨረታው [ከፊል ቃል በፎቶው አይነበብም] የጨረታ አከፋፈቱን ሥነ ስርዓት መከታተል የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ [ወኪሎቻቸው] በተገኙበት በቡሌ ወረዳ ፋ/ፕ/ጽ/ቤት ግዥ ኬዝ ቲም ቢሮ ቁጥር 3 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ላይ ይከፈታል።
- የጨረታው ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ዕለት ጀምሮ ለ60 ቀናት ብቻ ይሆናል።
- ተጫራቾች የቴክኒካልና ፋይናንሻል የመጫረቻ ሰነዶችን ለእያንዳንዳቸው አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ የጨረታ ሰነድ ማቅረብ አለባቸው።
- በተጫራቾች ተሞልተው የሚቀርቡ የመወዳደሪያ ሀሳብ ዶጋፊ ሰነዶች በግልጽና በጥራት መሞላት አለባቸው።
- በተጫራቾች ተሞልተው የሚቀርቡ የመወዳደሪያ ሀሳብ እና ሌሎችም ተጨማሪ ማረጋገጫዎች የሚመለከተው ሀላፊ ፊርማና ማህተም ካልተደረገባቸው የቀረበው የመወዳደሪያ ሀሳብ ሊሰረዝ ይችላል።
- አሸናፊ ተጫራቾች የውሉን አስር ፐርሰንት (10%) ) የአፈጻጸም ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- አሸናፊ ድርጅት ወይም ግለሰብ ያሸነፈበትን ዕቃ ቡሌ ፋይናንስ ጽ/ ቤት ማቅረብ የሚችል/የምትችል።
- አሸናፊ ድርጅት ወይም ግለሰብ ያሸነፈውን ዕቃ ጥራት ለመለየት ናሙና ማቅረብ የሚችል/የምትችል።
- አሸናፊ ድርጅት ዕቃውን አስገብቶ ገንዘቡን ሲቀበሉ ቫት 7.5% ለወረዳ መክፈል የሚችል/የምትችል።
- ጽ/ቤታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታ ላይ ለሚነሱ ማንኛውም ጥያቄዎች ጽ/ቤታችን አድራሻ በኩል ምላሽ ማግኘት ይቻላል።
የጌዴኦ ዞን ቡሌ ወረዳ ፋይናንስ ፕላን ጽ/ቤት ከዲላ 27 ኪሎ ሜትር
ለበለጠ መረጃ ስቁ፡- 0910583598/0916044158
በጌዴኦ ዞን የቡሌ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Bule Woreda Finance and Plan Office (Gedeo Zone, South Ethiopia) seeks suppliers of stationery, cleaning supplies, electronics and furniture in four lots for its sector offices. Open to licensed, VAT-registered suppliers on the supplier list with a current tax clearance.
