በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሸገር ሪጅን በስሩ ለሚገኙ የሥራ ክፍሎች እና ለ30 (ሰላሳ) ደንበኞቹ አገልግሎት ማዕከላት የጽህፈት መሳሪያዎች ፣ የጽዳት ዕቃዎች እና የኤሌክትሪክ ዕቃዎች ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች ላይ ለመግዛት ይፈልጋል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሸገር ሪጅን ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር ኢ/ኤ/አገ/ሸ/ሪ/ግ/ጨ/004/2019
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሸገር ሪጅን በስሩ ለሚገኙ የሥራ ክፍሎች እና ለ30 (ሰላሳ) ደንበኞቹ አገልግሎት ማዕከላት የጽህፈት መሳሪያዎች ፣ የጽዳት ዕቃዎች እና የኤሌክትሪክ ዕቃዎች ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች ላይ ለመግዛት ይፈልጋል።
| የዕቃው አይነት | የመዝጊያ ቀን እና ሰዓት | የመክፈቻ ቀን እና ሰዓት | የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ |
| የጽህፈት መሳሪያዎች እና የጽዳት ዕቃዎች (ሎት 1) | ህዳር 3 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት | ህዳር 3 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት | ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ) |
| የኤሌክትሪክ ዕቃዎች እና ቶነሮች (ሎት- 2) | ህዳር 3 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት | ህዳር 3 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት | ብር 250,000.00 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ) |
- ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨ.እ.ታ ሰርተፍኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና ከገቢዎች ባለስልጣን ጽ/ቤት ጨረታ ላይ እንዲሳተፉ የሚል ማስረጃ ያለው በጨረታው መሳተፍ ይችላል።
- ተጫራቾች የመንግስት ድርጅቶች በሚያወጡት ጨረታ ላይ ለመሳተፍ እንዲችሉ በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ https://epg.ppa.gov.et ድህረ ገጽ ላይ የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።
- በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች በማያያዝ መወዳደር የሚችሉ ሲሆን ዝርዝር ሁኔታው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ ይገኛል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ) ለእያንዳንዱ ሎት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000482105592 EEU- ፊንፊኔ ዙርያ ዲስትሪክት በሚለው በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
- አድራሻ፡- 22 ድንበሯ ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሸገር ሪጅን ሰፕላይ ቼይን ንብረት እና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ።
- ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን ከላይ በሠንጠረዡ ውስጥ በፀገለጠው መሠረት ሆኖ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ሲፒኦ /CPO/ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Bid Bond) መሆን ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል በአንድ ላይ በማድረግ ኦሪጅናል እና ኮፒ በማለት በተለያዩ ፖስታ በማሸግ እና ሁለቱን በአንድ ትልቅ ፖስታ በማድረግ ጨረታ ቁጥር ኢ/ኤ/አ/ሸ/ ሪጅ/ግ/ጨ/004/2019 የሚል በማድረግ እስከ ህዳር 03/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ከላይ በተራ ቁጥር 5 ላይ በተጠቀሰው አድራሻ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚኖርባቸው ሲሆን፤ ጨረታው ህዳር 03/2019 ዓ.ም 4፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል።
- ጨረታው ከላይ በተገለፀው መሠረት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር +251-011-522-65-04 መደወል ይችላሉ።
- ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሸገር ሪጅን
አዲስ አበባ
✨ messages.ai_summary
Ethiopian Electric Utility Sheger Region seeks suppliers for stationery, cleaning supplies (Lot 1) and electrical materials and toners (Lot 2) for its departments and 30 customer service centers. Bidders must hold a renewed business license, VAT certificate, TIN and tax clearance, and be registered on the government supplier list.
