የደሴ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት የጽህፈት መሳሪያ፣ ፅዳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸር፣ ህትመት፣ መስተንግዶ እና ደንብ ልብስና ጫማ ግዥ
በደቡብ ወሎ ዞን የደሴ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የደሴ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት በ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት ለመ/ቤቱ የጽህፈት መሳሪያ፣ የፅዳት እቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ቋሚ አላቂ እቃዎች፣ የፈርኒቸር እቃ፣ ህትመት እቃዎችን፣ የመስተንግዶ፣ ደንብ ልብስ ብትን ጨረቅ እና ጫማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም፤
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin/ ያላቸው፣
- የግዥ መጠኑ 500,000.00 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሠነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ኦሪጅናል ዕቃ መሙላት እና ያሸነፉባቸውን ዕቃ በባለሙያ ማስፈተሽ አለባቸው።
- የሚገዙ ዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሠነዱ ማግኘት ይቻላል።
- ማንኛውም ተጫራች በሰነዱ ላይ ሲሞሉ ከእያንዳንዱ የዕቃ ዋጋ ላይ ቫትን ጨምሮ መሙላት አለባቸው፣
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 6 ማግኘት ይቻላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ብር የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /C.P.O/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች በጥሬ ገንዘብ ሲያሲዙ በፍ/ቤቱ የገቢ ደረሰኝ ቆርጦ ኮፒውን ከኦሪጅናል ሰነዱ ጋር መታሸግ አለበት።
- አሸናፊው አካል የአሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ የሚያስዝ ይሆናል።
- ውድድሩ የሚካሄደው በጠቅላላ በሎት ድምር ነው።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በደሴ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት በግዥ ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 6 ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጥቅምት/02/2019 ዓ.ም እስከ ህዳር 02/2019 ዓ.ም ለ10 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነዱን መግዛትና በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
- ጨረታው ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ በተገኙበት በግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 6 በ11ኛው ቀን ማለትም ህዳር 03/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ይታሸጋል። በዚሁ ቀን በፍ/ቤቱ 4፡00 ይከፈታል። የመክፈቻው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ 4፡00 ይከፈታል።
- በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 6 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0914050100/ 0914050954/ በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
- በመ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ
አሸናፊው ድርጅት /ተጫራች/ኦርጅናል ዕቃ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው እንዲሁም በፍ/ቤቱ ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ ይኖርበታል።
የደሴ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Dessie City Woreda Court seeks suppliers of stationery, cleaning supplies, electronics, consumables, furniture, printing, catering, and uniform fabric and shoes, evaluated as a total lot. Open to suppliers with a renewed trade licence and TIN.
