Tender Detail

Tender Details

  • Company የሰንዳፋ በኬ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
  • Address ሰንዳፋ በኬ ከተማ አስተዳደር ዳሽን ባንከ ፊት ለፊት ፡ ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0116860068
  • Website
  • Deadline17 Nov 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 1,000.00 (የማይመለስ)
  • Bid Security2% (CPO በሲንቄ ወይም ኦሮሚያ ባንክ)
  • opening dateበዚሁ ዕለት 8:30
  • Categories Textile, Garment & Leather , Water Pipes And Fittings , Stationery Materials

የሰንዳፋ በኬ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት የጽህፈት መሳሪያ፣ HDPE እና GS ፊቲንግ እና የደንብ ልብስ ግዥ

የሰንዳፋ በኬ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት


የጨረታ ማስታወቂያ

የሰንዳፋ በኬ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በዚሁ መሰረት

  • Lot.1. አላቂ ዕቃ (Stationary)
  • Lot.2. HDPE fitting & GS fitting
  • Lot.3. (የደንብ ልብስ uniform) ናቸው።

ስለዚህ

  1. በተጠቀሱት የንግድ ዘርፎች ህጋዊና የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ያለውና 2018 ዓ.ም ግብር የከፈለ።
  2. የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችልና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው።
  3. የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነና በግብር አስገቢው ባለሥልጣን የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን በሰንዳፋ በኬ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ቢሮ 4 ቁጥር በመምጣት የማይመለስ ብር 1000.00 (አንድ ሺህ ብር ብቻ) ከፍለው መውሰድ ይችላሉ።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ CPO (bid bond) 2% በሲንቄ እና ኦሮሚያ ባንክ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  6. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ሠነዱን በመግዛት ዋጋ ሞልተው በታሸገ ኤንቨሎፕ በሰንዳፋ በኬ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ቢሮ ቁጥር 3 ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን በ11ኛ ቀን ከሰዓት 8፡00 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 8፡30 ይከፈታል።
  7. የጨረታው መዝጊያና መከፈቻ ቀናት ቅዳሜና ዕሁድ በዓላት ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ይሆናል።
  8. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው።

ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ከፈለገ በስልክ ቁጥር 0116860068 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

የሰንዳፋ በኬ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት

✨ messages.ai_summary
Sendafa Beke Town Water Supply and Sewerage Service Enterprise seeks suppliers of stationery (Lot 1), HDPE and GS pipe fittings (Lot 2) and staff uniforms (Lot 3). Open to licensed, VAT-registered suppliers with a supplier certificate and TIN.
Save Tender