Tender Detail

Tender Details

  • Company የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ቦሌ ቅ/ጽ/ቤት
  • Address , Phone: ..........
  • Website
  • Deadline13 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 500 (የማይመለስ)
  • Bid Securityሎት 1: ብር 5,000.00፣ ሎት 2: ብር 5,000.00፣ ሎት 3: ብር 2,000.00 (CPO ወይም የባንክ ዋስትና)
  • opening dateበዚሁ እለት በ4:30 ሰዓት
  • Categories Cleaning And Janitorial Equipment , Stationery Materials , Cloth And Shoes

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ቦሌ ቅ/ጽ/ቤት የደንብ ልብስ፣ የጽህፈት መሳሪያና የፕሪንተር ቀለሞች እና የጽዳት ዕቃዎች ግዥ

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ቦሌ ቅ/ጽ/ቤት


ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር አ/አ/ት/ቢ/ቦሌ/ቅ/ጽ/ቤት ግጨ/01/2019

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ቦሌ ቅ/ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በግልጽ ጨረታ ቁጥር አ/አ/ት/ቢ/ቦሌ/ቅ/ጽ/ቤት/ግጨ/01/2019 በሎት 1 (አንድ) ደንብ ልብስ፣ በሎት 2 (ሁለት) የጽህፈት መሳሪያ የፕሪንተር ቀለሞች እና ሎት 3 (ሶስት) የጽዳት ዕቃዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::

በዚህ መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታው መወዳደር የምትችሉ ሲሆን፡-

  • የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት ሰርተፍኬት (ቲን ነምበር)፣ የአቅራቢነት ሰርተፍኬት፣ ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን በጨረታ መሳተፍ ስለመቻላችሁ የሚገልጽ ማስረጃ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባችሁ፤
  • ማስታወቂያው አየር ላይ የሚቆየው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ሆኖ በ11ኛው ቀን ከረፋዱ በ4:00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ እለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ4:30 ሰዓት ይከፈታል፤
  • ተጫራቾች የቴክኒክና የዋጋ ፖስታቸውን ለይተው ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ሲሆን የቴክኒክ ፖስታው ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶችና የጨረታ ማስከበሪያ መያዝ ያለበት ሆኖ በጨረታ መክፈቻ ወቅት የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን::
  • የጨረታ ሰነዱን ከአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ቦሌ ቅ/ጽ/ቤት ከፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 602 ማስታወቂያው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን እስከ 10:00 ሰዓት በማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ) በመግዛት መውሰድ ትችላላችሁ::
  • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 1 (አንድ) ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር)፣ ለሎት 2 (ሁለት) ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር) እና ሎት 3 (ሶስት) ብር 2,000.00 (ሁለት ሺህ ብር) CPO ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል::
  • ተጫራቾች በሚሞሉት ሰነድ ላይ የድርጅታቸውን ማህተም እና ህጋዊ ውክልና ባለው አካል በእያንዳንዱ ገጽ ላይ መፈረም አለባቸው::

ማሳሰቢያ:- መ/ቤቱ ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

አድራሻ:- 22 ማዞሪያ መከሊት ህንጻ ጎን ፕሪሚየም ኮሌጅ ያለበት ህንጻ ላይ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 602 ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 -10-50-28-12 መጠየቅ ይቻላል::

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ቦሌ ቅ/ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
The Addis Ababa Transport Bureau Bole Branch seeks suppliers in 3 lots: uniforms, stationery and printer toner, and cleaning supplies. Bidders need a renewed trade licence, TIN, supplier registration, VAT certificate and revenue authority clearance. Open bid.
Save Tender