የልደታ ክ/ከ የዕውቀት ለህብረት 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የደንብ ልብስ፣ የቢሮና የትምህርት ዕቃዎች፣ የህትመትና ልዩ ልዩ ዕቃዎች ግዥ
የልደታ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የአውቀት ለህብረት 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
1ኛ ዙር የጨረታ ማስታወቂያ
በልደታ ክ/ከ/ ስር የሚገኘው የዕውቀት ለህብረት 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በጨረታ ቁጥር 001/2019 መሰረት
- ሎት 1 የደንብ ልብስ
- ሎት 2 አላቂ የቢሮ እቃዎች
- ሎት 3 የህትመት ስራዎች
- ሎት 4 የትምህርት መሳሪያዎች
- ሎት 5 የፅዳት አላቂ ዕቃዎች
- ሎት 6 ልዩ ልዩ እቃዎች
- ሎት 7 የጥገና እቃዎች
- ሎት 8 ቋሚ የቢሮ እቃዎች
- ሎት 9 ቋሚ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
በዚህም መሠረት መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ሕጋዊ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል::
- ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው የሀገር ውስጥ የዘመኑን ግብር አጠናቆ የከፈሉ:: የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው::
- በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡ በሚያቀርቡት የእቃ ዋጋ ከነቫቱ መጠቀስ አለበት::
- የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከጠዋቱ 3:00-10:00 ሠዓት በፋ/ግ/ን/ አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 14 የጨረታ ሰነድ መግዛት ይቻላል::
- የጨረታ ማስከበሪያ ከሚወዳደሩበት በእያንዳንዱ ሎት 2% (ሁለት ፐርሰንት) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ አለባቸው::
- ተወዳዳሪው አሸናፊ የሆነ ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ የገዘውን ግምታዊ ዋጋ 10% በቅድሚያ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል::
- ተጫራቾች ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ናሙናው ጨረታው ከመከፈቱ ከሁለት ቀናት በፊት ማቅረብ ግዴታ ይኖርባቸዋል፤ ካላቀረቡ ግን ከጨረታው ይሰረዛሉ::
- ጨረታው በ11ኛው ቀን ከቀኑ ከጠዋቱ 3:00 ሰአት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት በፋይናንስ ክፍል ይከፈታል::
- በጨረታው የሚቀርቡት ዕቃዎች የጥራት ደረጃውን የጠበቁ መሆን አለባቸው::
- ማንኛውም ተጫራች በግዥ ጨረታው ላይ ከተጠየቀው ውጪ ናሙና ማቅረብም ሆነ ናሙናው ላይ ምልክት ማድረግ ከውድድር ውጭ ያደርጋል::
ማሳሰቢያ:- መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ:- በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 ከኢትዮጵያ መድሃኒት ፋብሪካ ጀርባ ገባ ብሎ
ለበለጠ መረጃ:- 09 11-79-47- 46 ወይም 09 11 47 75-46
በልደታ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Ewket Lehibret Secondary School (Lideta Sub-city, Addis Ababa) seeks suppliers in 9 lots: uniforms, office consumables, printing, educational materials, cleaning supplies, miscellaneous and maintenance items, office furniture and electronics. VAT-registered suppliers with renewed licence. Open bid.
