አማራ ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሠረት ከዚህ ቀጥሎ የቀረበውን ንብረት በግልጽ የሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
Amhara Bank S.C (አማራ ባንክ አ.ማ)
የሐራጅ ማስታወቂያ
ቁጥር አማራ ባንክ 56/2019
አማራ ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሠረት ከዚህ ቀጥሎ የቀረበውን ንብረት በግልጽ የሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ
| ተ.ቁ | የተበዳሪው ስም | የንብረት አስያዥ ስም | አበዳሪው ቅርንጫፍ | ክ/ከተማ | ከተማ | ወረዳ | ቀበሌ | የቦታው ስፋት | የባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ ቁጥር | የንብረቱ ዓይነት/ የይዞታው አገልግሎት | የጨረታ መነሻ ዋጋ /ብር/ | ቀን | ሰዓት | ቦታ |
| 1 | አስናቀ አጅት አንተነህ [ስሙ በፎቶው በግልጽ አይነበብም] | ወ/ሪት ቤዛዊት አጅት አንተነህ [ስሙ በፎቶው በግልጽ አይነበብም] | ሳር ቤት | ኮ/ቀራንዮ | አዲስ አበባ | 4 | - | 150 ካ.ሜ | K05/02-3-130-183-8260/01 | ለመኖሪያ | 8,128,007.98 | ኅዳር 18 ቀን 2019 ዓ.ም | ከ 4:00 እስከ 5:00 ሰዓት | አማራ ባንክ አ.ማ ዋናው መስሪያ ቤት |
ማሳሰቢያ
- ተጫራቾች የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ ወይም ሃያ አምስት በመቶ (25%) በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ (C.P.O) ብቻ በአማራ ባንክ አ.ማ ስም በማሰራት በማስያዝ እና በመመዝገብ በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- ከፍተኛ ዋጋ የሰጠው ተጫራች የጨረታው አሸናፊ ነው የሚባለው ከባንኩ አሸናፊነቱን የሚገልጽ ደብዳቤ በጽሁፍ ሲደርሰው ብቻ ነው፡፡
- የጨረታ አሸናፊው አሸናፊ መሆኑ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት/ ቀናት ውስጥ ቀሪውን ገንዘብ አጠናቆ መክፈል ይኖርበታል፡፡ ባይከፍል ግን የሐራጅ ውጤቱ ተሰርዞ ያስያዘው ሲፒኦ አይመለስለትም፣ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡ በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሃራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል፡፡ ላላሸነፉት ተጫራቾች ግን ያስያዙት ሲፒኦ በእለቱ ይመለስላቸዋል፡፡
- የሐራጅ አሸናፊ /ገዥ/ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን የሊዝን ክፍያን ጨምሮ፣ ግብር፣ በዋጋው ላይ ሚታሰብ ተጨማሪ እሴት ታክስ (15%) ካለ ከስም ማዛዋወሪያ ጋር የተገናኙ እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በህግ የተወሰኑ ታክስ እና ግብሮች ገዥው/አሸናፊው/ ይከፍላል፡፡
- ተጫራቾች በሃራጅ ለመሳተፍ ሲመጡ መታወቂያ (የቀበሌ፣የመንጃ ፍቃድ፣ፓስፖርት ወይም ብሄራዊ መታወቂያ) መያዝ ይገባቸዋል፡፡ ተጫራቾች የህግ ሰውነት የተሰጣቸው አካላት ከሆኑ ደግሞ ህጋዊ ሰውነት ያገኙበትን የዋና ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ሃራጁን ለመሳተፍ የቀረበው ግለሰብ ስልጣኑን የሚያሳይ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት የጸደቀ መመስረቻ ጽሁፍ (የመተዳደሪያ ደንብ)፣ ቃለጉባኤ ወይም የውክልና ሰነድ ይዞ መቅረብ አለበት፡፡
- ንብረቱ በገዢው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል፡፡
- ለሐራጅ የቀረበውን ንብረት ለመጎብኘት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የጉብኝት ፕሮግራም ከወርክዉትና ሪከቨሪ ክፍል ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በማስያዝ ጨረታው ከመካሄዱ ከ5 ቀን በፊት መጎብኘት ይችላል፡፡
- ጨረታው በሰንጠረዡ ላይ በተጠቀሰው ቀን፣ ሰዓትና ቦታ ተጫራቾች፣ ተበዳሪ እና ንብረት አስያዥ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት ይከናወናል፡፡ ነገር ግን ተበዳሪውም ሆነ መያዣ ሰጪው ባይገኙ ጨረታው በሌሉበት ይከናወናል፡፡
- ንብረቱን/ቶቹን በጨረታ አሸንፎ የገዛ ግለሰብ/ድርጅት የቀሪው ገንዘብ ክፍያ ከጠናቀቀ በ15 ቀናት ጊዜ ውስጥ ንብረቱን መረከብ ያለበት ሲሆን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ንብረቱን ካልተረከበ በንብረቱ ላይ ለሚደርስ ጉዳት ባንኩ ኃላፊነት አይወስድም፡፡ ገዥው በተጠቀሰው ጊዜ ንብረቶቹን ካልተረከበ ከንብረቶቹ ጋር በተያያዘ ለሚደርስ ወጪ ኃላፊነቱን ይወስዳል፡፡
- በባንኩ የብድር ፖሊሲና መመሪያ እና ቅድመ ሁኔታ መሰረት የሚፈለገውን ማስረጃ አሟልቶ ለቀረበ የጨረታ አሸናፊ ባንኩ ለተጫራቹ እስከ 100% ብድር ሊያመቻች ይችላል፡፡
- የተጫራቾች ምዝገባ ከሃራጅ ማካሄጃ ሰአት 30 ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል፡፡
- በወንድ አንቀጽ የተጠቀሰው ለሴት እና ህጋዊ ሰውነት ላላቸው ድርጅትም ያገለግላል፡፡
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ ማብራሪያ አማራ ባንክ አ.ማ 0115 58 27 64 ወይም 011 5 58 41 89 በስራ ሰአት ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
አማራ ባንክ አ.ማ.
✨ messages.ai_summary
Amhara Bank is selling a residential property (150 sq.m) in Addis Ababa, Kolfe Keranio, via public auction. Bidders must present valid ID or legal entity documents and a 25% CPO. The highest bidder wins upon written confirmation and must pay the balance within 15 days.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
