የፍርድ አፈጻጸም ሐራጅ፡ በሞጆ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የሚገኝ 10 TPH የቡና ማቀነባበሪያ ፕላንት በ34,719,382.68 ብር መነሻ ዋጋ ህዳር 17 ቀን 2019 ዓ.ም. ይሸጣል።
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት በረከት ማርቆስ እና የፍ/ባለዕዳ ሶፋ መሀመድ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/335203 በህዳር 19 ቀን 2018ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/344458 በ28/05/2018ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በሞጆ ከተማ አስ/ጽ/ቤት በሞጆ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤ ግቢ ውስጥ የሚገኝ የቡና መፈልፈያ ፕላንት( 10 TPH Coffee beans processing plant) የሆነ ንብረት የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 34,719,382.68 ( ሰላሳ አራት ሚሊዮን ሰባት መቶ አስራ ዘጠኝ ሺህ ሶስት መቶ ሰማንያ ሁለት ከ68/100) ሆኖ የትራዝክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ህዳር 17 ቀን 2019ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 8:00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታውቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3:30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጎብኘት የሚችሉ ሲሆን፣እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P .O ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም C.P .O አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል _ ማስረጃ _ ከመጻፍ _ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
