የWindows of Hope 2026 ፕሮጀክት ያሰባሰባቸው አስር አጋር ድርጅቶች ለቆዳ እና የልብስ ስፌት ስራ ማሽኖች አቅርቦት ብቁ የሆኑ አቅራቢዎችን በድጋሚ በጨረታ አወዳድረው መግዛት ይፈልጋሉ፡፡
Duka Youth Led Organization (ዱካ ዩዝ ሌድ ኦርጋናይዜሽን)
በድጋሚ የወጣ የልብስ እና የቆዳ ስፌት ማሽን ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የWindows of Hope 2026 ፕሮጀክት ያሰባሰባቸው አስር አጋር ድርጅቶች ለቆዳ እና የልብስ ስፌት ስራ ማሽኖች አቅርቦት ብቁ የሆኑ አቅራቢዎችን በድጋሚ በጨረታ አወዳድረው መግዛት ይፈልጋሉ፡፡
ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት በአጋር ድርጅቶቹ በሚመሩት የቴሌግራም ቦት @WoH_bid_portalbot በኩል ወይም በጥምረቱ በተመረጡ ሁለት መስሪያ ቤቶች ማለትም በሃንድ ኢን ሃንድ ዋና መስሪያ ቤት (አድራሻ:- ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02፣ ከጀሞ ሚካኤል ወደ አየርጤና በሚወስደው መንገድ ላይ በሚገኘው የሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን 4ኛ ፎቅ) ወይም በዱካ ዩዝ ሌድ ኦርጋናይዜሽን (አድራሻ:- አራት ኪሎ ከቤተ መንግሥት ወደ ሴቶች አደባባይ በሚወስደው መንገድ ከተፍት ቤት ዝቅ ብሎ፣ ጃምባ ፕላዛ 3ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 302) በአካል በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 1,000.00 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
ተወዳዳሪዎች ለጨረታ የሚያቀርቡትን ዋጋ ከጨረታው ሰነድ ጋር በተያያዘው የዋጋ ማቅረቢያ ላይ ከሞሉ በኋላ፣ የጨረታ ማስከበሪያ በሃንድ ኢን ሃንድ ሁለቲ ቻልድረን ሰርቪስ (HinH) ስም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም በባንክ ዋስትና (Bank Guarantee) ወይም የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሰነድ (Bid Security/Bond) ብቻ ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር አያይዘው በፖስታ በማሸግ ከጥቅምት 19 እስከ ህዳር 03 ቀን 2019 ዓ.ም 4:30 ድረስ በህብረት መሪ ድርጅት (ሃንድ ኢን ሃንድ) ዋና ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
ተጫራቾች በአንዱ የማሽን አይነት ወይም በሁለቱም መወዳደር የሚችሉ ሲሆን፣ ለእያንዳንዱ የማሽን አይነት የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
የጨረታው ሣጥን ህዳር 03 ቀን 209 ዓ.ም ከረፋዱ 4:30 ተዘግቶ 5:00 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
ጨረታውን አሸንፈው በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ ውስጥ የማያስረክቡ ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ የሰጡት ዋስትና በሙሉ ለጥምረቱ አባላት ገቢ ይሆናል፡፡ ጨረታውን ለማሸነፍ ያልቻሉ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ሰነድ የጨረታ ግምገማ ውጤት ከተገለፀ በኋላ በ5 ቀናት ውስጥ ይመለስላቸዋል፡፡
ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን ከሞሉ በኋላ በጥምረቱ መሪ ድርጅት ዋና መሥሪያ ቤት ሃንድ ኢን ሃንድ ሁለቲ ቻልድረን ሰርቪስ (HinH) ቢሮ (አድራሻ:- ጀሞ ሚካኤል ወደ አየርጤና መንገድ 500 ሜትር አንደተጓዙ በሚገኘው ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን 4ኛ ፎቅ) በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
ጥምረቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የጥምረቱ አባል ድርጅቶች:-
- ሃንድ ኢን ሃንድ ሁለቲ ቻልድረን ሰርቪስ (HinH) - የጥምረቱ መሪ ድርጅት
- ናሽናል ያንግ ውሜን ቻሪቲ ኦርጋናይዜሽን (NYWCO)
- አዲስ አበባ ሲቲ ዴቨሎፕመንት ቻሪቲ ኦርጋናይዜሽን (AACDCO)
- ራዲያም ዘ ጀነሬሽን (RTG)
- ፌይዝ ኢን አክሽን (FIA)
- ዱካ ዩዝ ሌድ ኦርጋናይዜሽን (DYLO)
- አይ ኬር ፎር ዘ ኔሽን (ICN)
- ቤተ ሳይዳ ቻሪቲ ኦርጋናይዜሽን (BCO)
- ኢንዱራንስ ዩዝ አሶሴሽን (EYA)
- ኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዴቨሎፕመንት (ECD)
