በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ/ዞን/ የእንሳሮ ወረዳ ፍ/ቤት ለ2019 በጀት አመት ከመደበኛ በጀት ላይ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎችን ለመግዛትና ለማሰራት ስለሚፈልግ በዚህ መሰረት የሚከተሉትን መመዘኛዎችን የሚያሟሉና በዘርፍ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ ዘዴ ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል::
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ/ዞን/ የእንሳሮ ወረዳ ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡ
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር/ 51/2019ዓ.ም
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ/ዞን/ የእንሳሮ ወረዳ ፍ/ቤት ለ2019 በጀት አመት ከመደበኛ በጀት ላይ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎችን ለመግዛትና ለማሰራት ስለሚፈልግ በዚህ መሰረት የሚከተሉትን መመዘኛዎችን የሚያሟሉና በዘርፍ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ ዘዴ ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል:: በመሆኑም
ሎት1 የጽህፈት መሳሪያ እቃዎች/የኮምፒውተር ቀለሞች/እና የአላቂነት ባህሪ ያላቸው እቃዎች
ሎት2 ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
ሎት3 ቋሚ እቃዎች/ፈርኒቸር/
ሎት4 የጽዳት እቃዎች
ሎት5 የህትመት ስራዎች
ሎት6 የተዘጋጁ ልብሶች/ብትንጨርቅ/ጫማዎች
ሎት7 ቋሚ እቃዎች ጥገና
ሎት8 ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ጥገናዎች
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋያ መለያ ቁጥር/tin/ያላቸው::
- የተጨማሪ እሴት ታክስ/VAT/ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ::
- ተጫራቾች ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ1-2 የተጠቀሱትንና ሌሎች የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
- በማንኛውም ግዥ ለእቃዎች ከብር 20000/ሀያ ሽህ/ በላይ እና ለአገልግሎት ከብር 10000/አስር ሽህ/ በላይ ለሚሆኑ ግዥዎች አቅራቢው ከሚፈጸምለት ክፍያ ላይ 3% የቅድመ ግብር/with hold/ ተቀንሶ የሚቀር ይሆናል::
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200/ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመከፈል ጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከሚዘጋበት ቀን ድረስ ከግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን/የስ/ሂደት ቢ.ቁ 03 በመቅረብ ዘውትር በስራ ሰአት መውሰድ ይችላሉ::
- ተጫራቾች የሚቀርቡት ዋጋ ማንኛውንም አይነት ግብር የሸፈነ መሆን አለበት በጨረታው ለመሳተፍ ወይም ለመወዳደር የሚወጡ ወጭዎች ቢኖሩ መስሪያ ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም::
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውንና ደጋፊ ማስረጃዎችን የሚዘገጁበት ቋንቋ አማርኛ መሆን አለበት::
- መ/ቤቱ የእቃዎችን ናሙና የሚፈልጉ ከሆነ ተጫራቾች የጠየቁትን ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው:: ጨረታው የሚለየው በጥቅል ዋጋ ነው::
- በተጫራቾች መመሪያ ይዘት ላይ ምንም ማሻሻያ ማድረግ አይቻልም::
- ተጫራቾ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ የእቃ ዋጋ 1% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በኢትዮጵያ ንግድ ባንክና በአቢሲኒያ ባንክ ብቻ በሲፒኦ/በጥሬ ገንዘብ/ በጽ/ቤቱ ህጋዊ ደረሰኝ ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማስያዝ አለባቸው::
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን አንድ ወጥ በሆነ ዋና ኦርጅናል በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ስም፣ ፊርማና ሙሉ አድራሻ በመፃፍ እ/ወ/ፍ/ቤት ቢሮ ቁጥር 4 በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰአት ማስገባት አለባቸው:: ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ11ኛው ቀን 4:30 ሰአት ተዘግቶ በዚያው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ5:00 ሰአት በገልጽ ይከፈታል::
- በማንኛውም ሁኔታ ተጫራች በሌላ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ወይም ተመስርቶ መጫረት አይችልም::
- ግዝ ፈፃሚው አካል ውል ከመግባቱ በፊት ከአሸናፊው ተጫራች የቀረበውን ዋጋ ሳይቀይር እስከ 20% ለመቀነስ ወይም መጨመር እንደሚችል ማወቅ አለባቸው::
- የጨረታው መዝጊያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታ እራሳቸውን ማግለል አይችሉም:: አሸናፊ የሆነ ድርጅት በግዥ ፈጻሚ መስሪያ ቤት አቅራቢያ በሚገኝ ዐ/ህግ ጽ/ቤት በመቅረብ 10% ውል በመግባት ለግዥ ፈጻሚ መስሪያ ቤት ንብረት ክፍል ማስረከብ አለባቸው::
- ጨረታ ለማዛባት የሚሞከሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጭ ይሆናሉ፤ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ውርስ ይሆናል::
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም ብሄራዊ በአላት ቀን ከሆን በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል::
- የመስሪያ ቤቱ መገኛ ከዞኑ ደ/ብርሀን ከተማ 86 ኪ.ሜትር ከአዲስ አበባ ደግሞ 130 ኪ.ሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች::
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0912841935 መጠየቅ ይችላሉ::
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ/ዞን/ የእንሳሮ ወረዳ ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡ
✨ messages.ai_summary
The Insaro Woreda Court in Amhara Region seeks to procure office and home furniture, stationery, electronics, cleaning supplies, printing services, and ready-made clothing/shoes, plus furniture and electronics repair. Bidders must have a renewed business license, TIN, and VAT registration.
