የተተውና የተወረሱ ዕቃዎች የኦንላይን ሀራጅ ሽያጭ (ሐ-20/2019, Auction Ethiopia) - የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
Modjo Customs Branch Office (የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት)
በጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
የተተውና የተወረሱ ዕቃዎች የሀራጅ ጨረታ ቁጥር ሐ-20/2019 ጨረታ
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተሻሻለው የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 1160/2011 አንቀፅ 13 መሠረት እና በተለያዩ ምክንያቶች የተወረሱ ንብረቶችን ስለማስወገድ በወጣው መመሪያ ቁጥር 167/2012 አንቀፅ 10 መሠረት የተተው ንብረቶችን ማለትም፦ AC ADAPTOB HD TV CABLE TV WALL MOUNT LED HIGHBAY LIGHT SKMEI IRON ADULT HAND WATCH! WOODEN DOOR FRAME & WATER PURIFIER OUT DOOR SOLAR STRIGHT LIGHT & STRIGHT LIGHT STAND! LED STRING LIGHTS! RUBBER NAIL FILTER, S/S MANICURE, METAL DECORATIVE & EYE LASH PHOTO COPY MACHINE AND PRINTER ADULT FABRIC CAP, SHOPPING BAG & OTHERS! RECHARGEBLE CAMPING PORTABLE PORTABLE SHOWER! SHOWER WALL TRANSFORMER CHEMICAL MIXING TANK, CHANNEL STEEL, GALVANISED STEEL PIPE: HEALD FRAME FABRIC MICRO FIBER CLEANING TOWEL SINGLE,DOUBLE PORT FACE PLATE & OTHER S/S ARTIFICIAL EARRING & BEARING, SCHOOL BAG, FABRIC ADULT CAP & SUPERMARKET SHELF! CHILDRED SPORT SHOES BRAND & LADYSPORT SHOES BRAND LADY SKIRT, LADY TIGHT & OTHER: VIBRATION ANALYSIS OF CENTERFUGAL BLOWER FAN! ELECTRIC CRANE SCALE HAIR CLIPER, PERFUME & TROUSERI DAF TRACK VAN CAR WITH CONTAINER WITHOUT REIFROGIRETOR! TWO SIDE COATED ART PAPER፤ የኮንስትራክሽን ማሽኖች እቃዎችና የተሽከርካሪ መለዋወጫ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በሀራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በዚህም መሠረት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመወዳደር የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
- ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር፣ ዓይነት እና ብዛት የያዘውን ሰነድ ከአክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በመግዛት ከንብረቶቹ መግለጫ ስር ተያይዞ የሚገኝ ስለሆነ አውርደው መመልከት ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች አክሽን ኢትዮጵያ ላይ ተመዝግበው የጨረታ ሠነዱን ካገኙ በኋላ ንብረቶቹን በአካል ለመመልከት ዘወትር ከሰኞ እስከ ቅዳሜ በስራ ሰዓት ማየት ይቻላል።
- ተጫራቾች በጨረታው ከሚሸጠው ዕቃ ጋር በዘርፉ የፀና ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ በአክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ማያያዝ አለባቸው። ሆኖም ግምታዊ ዋጋቸው ከብር 500,000.00 በታች የሆኑ ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሠርተፍኬት ማቅረብ ሳያስፈልግ መወዳደር ይችላሉ። N.B: ተሽከርካሪ ላይ ለመጫረት የተሽከርካሪው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰብ ከሆነ ሰው በስተቀር ማንኛውም እድሜዉ ከ18 አመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ የታደሰ መታወቂያ በማቅረብ ቅድመ-ሁኔታዎቹን ማሟላት ሳያስፈልገዉ በጨረታው መሳተፍ ይችላል።
- ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስን ሳይጨምር መሆኑን እናሳውቃለን።
- ማንኛውም ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን የሚጫረቱበትን ለሁሉም ዕቃዎች 300,000.00 (ሶስት መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ CPO ጨረታ ከመከፈቱ በፊት በቅድሚያ በአካል የአክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ ማስያዝ ይኖርበታል። CPO በቅርንጫፍ ጽ/ቤታችን ስም ETHIOPIAN CUSTOMS COMMISSION MODJO BRANCH OFFICE በሚል ሲሆን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ አበባ እና አዳማ ዋና ቅርንጫፎች መዘጋጀት አለበት።
- የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ8ኛው የሥራ ቀን እስከ ጥዋቱ 4:00 ሰዓት ድረስ በሚካሄደው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች የጨረታውን ሂደት በቀጥታ (online) መወዳደር ይችላሉ።
- ተጫራቾች የአክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም (auction.et) ላይ መመዝገብ እና መጫረት ይችላሉ።
- ማንኛውም የጨረታ ሽያጭ ዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤት እና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም፤ ጨረታውን ካሸነፈ በኋላ አራሱን ከጨረታው ውድድር ማግለል አይቻልም፤ የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ ለጨረታው ማግኘት ተጠናቀ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የጨረታውን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል።
- የሐራጅ ጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ስለማሸነፋቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ አለበት። በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ ገንዘቡ ካልተገለ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል።
- በተራ ቁጥር 07 በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ያሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ አድርጎ ዕቃውን ያልተረከበ እንደሆነ ለሚቆዩበት ለተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ ይከፍላል። ሆኖም ዕቃው በ2 (ሁለት) ወራት ውስጥ ካልወጣ እንደተተወ ተቆጥሮ በጨረታ ሽያጭ ይወገዳል።
- አሸናፊው ተጫራች ዕቃዎቹን ለመረከብና ለማጓጓዝ የሚያስፈልጉትን ወጪዎችን ሁሉ ራሱ ይሸፍናል።
- ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ዕቃዎቹን ለመሸጥ የተሻለ አማራጭ ወይም ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የአክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በአጭር የስልክ መስመር 9164 ወይም 09-05-11- 5511/ 011-666 8828 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በሥልክ ቁጥር 022-236-90-94 ወይም 022-236-01-90 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
