Tender Detail

Tender Details

  • Company የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ
  • Address , Phone:
  • Website
  • Deadline05 Nov 2026, 2:00 PM
  • magazine
  • Bid Document Price300(ሶስት መቶ ብር)
  • Bid Securityከጠቅላላ የጨረታ ዋጋ 2% በባንክ የተረገገጠ ሲፒኦ/ Letter of credit
  • opening dateበዕለቱ 8:30 ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት
  • Categories Education And Training , Stationery Materials , Electronics Materials

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ በሎት 1 ጽ/መሳሪያ ግዥ፣ በሎት 2 ኤሌክትሮኒክስ ግዥ እና በሎት 3 አድቫስድ የኢኮቴ ባለሙያዎች ሥልጠና ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ


የጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ በሎት 1 ጽ/መሳሪያ ግዥ፣ በሎት 2 ኤሌክትሮኒክስ ግዥ እና በሎት 3 አድቫስድ የኢኮቴ ባለሙያዎች ሥልጠና ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::

በዚህ መሰረት በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች

  1. የተጨማሪ እሴት ታክስ VAT / ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉና አግባብ ያለው የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው
  3. በፋይናንስ መስሪያ ቤቶች በዕቃ አቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡና በህግ ያልተገደቡ ፤
  4. በሎት 1 ጽ/መሳሪያ ግዥ፣ በሎት 2 ኤሌክትሮኒክስ ግዥ እና በሎት 3 አድቫስድ የኢኮቴ ባለሙያዎች ሥልጠና ግዥ ለመፈፀም በቢሮ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት በቢሮ የግዥ ፋይ/ ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት በመቅረብ 300 ብር በመክፈል መውሰድ ይችላሉ
  5. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በስም በታሸገ ኢንቬሎፕ የቴክኒካል የጨረታ ሰነድና የፋይናንስ የጨረታ ሰነድን ለብቻ ለብቻ ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ለተዘጋጀ የቴክኒክና የፋይናስ ሰነድ ተጨማሪ ተመሳሳይ አንድ አንድ ኮፒዎች አዘጋጅተው በየኢንቬሎፑ የውጭ ገጽ ዋና /ኦርጂናል/ ወይም / ኮፒ/ ብሎ በመፃፍ አሽገው ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
  6. በማንኛውም ኤንቬሎፕ ውስጥ የጨረታ ማስከበሪያ ማስገባት የለባቸውም ስለ ተጫራቾች የንግድ ፈቃድ የቫት ሰነድ መልካም አፈጻጸም ወዘተ መካተት ያለባቸው በቴክኒክ የጨረታ ሰነድ በሆነት በዋናው/ኦሪጅናል እና ኮፒ ተብሎ በተገለጹት በሁለቱም ኤንቬሎፕ ሲሆን በፋይናንስ የጨረታ ሰነድ በዋናው/ኦሪጅናል / ሆነ ኮፒ ኤንቬሎፕና ውስጥ ከፋይናንስ የጨረታ ሰነድ ውጭ ምንም ተጨማሪ መረጃ ማስገባት አይፈቀድም፤
  7. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን የሚያስገቡበት የመጨረሻ ቀን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት እስከ 8:00 ሰዓት ድረስ ብቻ ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው በዕለቱ 8:30 ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል:: የሚከፈትብት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው የሚዘጋውና የሚከፈተው በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ ይሆናል::
  8. ማንኛውም ተጫራች ህጋዊ ወኪል በፍርድ ቤት የተረጋገጠና በኢ.ፌ.ዴ.ሪ/ በክልሉ መንግስት ህጐች ተቀባይነት ያለው ኦሪጅናል የውክልና ሰነድ ይዞ መቅረብ አለበት ፎቶ ኮፒ ተደርጐ ብቻ የሚመጣ ሰነድ ተቀባይነት የለውም::
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚያቀርቡት ከጠቅላላ የጨረታ ዋጋ 2% በባንክ የተረገገጠ ሲፒኦ/ Letter of credit ለብቻው በታሸገ ፖስታ መሆን አለበት::
  10. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ/ጉ/አቅራቢ/ዎች/ተጨማሪ መረጃ የሚፈልጉ ከሆነ በስልክ ቁጥር 0467710711 ዘወትር በስራ ሰዓት መጠየቅ ይችላሉ::
  11. ቢሮው ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::
  12. በሎት 1 ጽ/መሳሪያ ግዥ፣ በሎት 2 ኤሌክትሮኒክስ ግዥ እና በሎት 3 አድቫስድ የኢኮቴ ባለሙያዎች ሥልጠና ግዥ ዝርዝር መረጃውን ከጨረታ ሰነዱ ውስጥ የተያያዘና የተገለጸ በመሆኑ ዝርዝሩን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ::

የቢሮ አድራሻ፡- በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወረቤ ቅርንጫፍ ህንፃ ላይ ነው::

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት
ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ

✨ messages.ai_summary
The Central Ethiopia Regional Government Innovation and Technology Bureau seeks suppliers for Lot 1 stationery, Lot 2 electronics, and Lot 3 advanced training for EcoTech professionals via open tender. Bidders must be VAT-registered, tax-compliant with valid business licenses, and registered as suppliers.
Save Tender