ኩባንያችን የተለያየ መጠን ያላቸውን የፅህፈት መሣሪያዎች እና የፅዳትና የሪፍሬሽመንት ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::
AFRICA INSURANCE COMPANY S.C (አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ.)
አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ /አ.ማ/
የፅህፈት መሣሪያዎች ፣ የፅዳትና የሪፍሬሽመንት ዕቃዎች ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር AIC:- 0018/2026
ኩባንያችን የተለያየ መጠን ያላቸውን የፅህፈት መሣሪያዎች እና የፅዳትና የሪፍሬሽመንት ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::
ሀ. ሎት -1 የፅህፈት መሣሪያዎች
ለ. ሎት-2 የፅዳትና የሪፍሬሽመንት ዕቃዎች
ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መስረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ::
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ እንዲሁም ከሚመለከተው የመንግስት ተቋም የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል:: የጨረታው አሸናፊ ባቀረበው ሰነድ መሰረት እቃዎቹን ሳያቀርብ ቢቀር ያስያዘው በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ለኩባንያው ገቢ ይደረጋል ወይም ተመላሽ አይሆንም::
- ከላይ በተራ ቁጥር 2 ላይ የተገለጸው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን ሲፒኦ (CPO) ሙሉ ለሙሉ ተመላሽ የሚሆነው አሸናፊው ድረጅት ያሸነፋቸውን እቃዎች ለኩባንያው ገቢ ካደረገ በኋላ ኩባንያው የገቡትን እቃዎች በሳምፕላቸው መሰረት መሆኑን ካረጋገጠ በኋላ ነው::
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት በኩባንያው ዋና መ/ቤት በመገኘት የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ) በመክፈል የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ::
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ጋር መሆን ወይም አለመሆኑን መግለፅ ይኖርባቸዋል::
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ጥቅምት 11 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 17 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 ድረስ ቦሌ በሚገኘው የአፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ ዋና መ/ቤት ህንፃ 11ኛ ፎቅ በስራ ሰዓት በመቅረብ ለዚሁ ጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው::
- ጨረታው ጥቅምት 17 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኩባንያው ዋና መ/ቤት ህንፃ 11ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የስብሰባ/ስልጠና አዳራሽ ይከፈታል::
- ተጫራቾች የሚያስገቡት የጨረታ ሰነድ የእቃው ዝርዝር መግለጫ (Specification) የያዘ ሊሆን ይገባል እንዲሁም በሚያቀርቡት ናሙና (Sample) ላይ የድርጅታቸው ማህተም ሊኖር ይገባል::
- አንዱ ተጫራች በሌላው ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ መጫረት ከጨረታው የሚያሳግድ መሆኑን እንገልፃለን::
- አሸናፊው ተጫራች የጨረታው አሸናፊ መሆኑ ከተገለፀለት ወይም የጨረታ ውጤት ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ የፅህፈት መሣሪያዎች፣ የፅዳትና የሪፍሬሽመንት ዕቃዎች ከ7 ቀን ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ወይም በውሉ መሰረት ማቅረብ ይኖርበታል::
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የፅህፈት መሣሪያዎች፣ የፅዳትና የሪፍሬሽመንት ዕቃዎች ሲወዳደሩ ባስገቡት (ባቀረቡት) ሳምፕል / ናሙና መሰረት መሆን አለበት::
- ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃዎች የኩባንያው ዋና መ/ቤት ድረስ በማምጣት ማስረከብ ይኖርባቸዋል::
- ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ በማንኛውም ጊዜ በከፊል ወይም በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ :- በስልክ ቁጥር 0116 611877 / 0116 637485/ 0116 637716 በመደወል መጠየቅ ይቻላል::
አድራሻ:- አዲስ አበባ ቦሌ ሩዋንዳ ደርድይ አካባቢ አፍሪካ ኢንሹራንስ ህንፃ 1
✨ messages.ai_summary
Africa Insurance Company seeks to buy stationery (Lot 1) and cleaning and refreshment supplies (Lot 2) via open tender. Bidders must hold a valid business license, tax payment and VAT registration proof, and a competency certificate from the relevant government body, and must submit samples bearing their company stamp.
