Tender Detail

Tender Details


የኢትዮጵያ ስኩል ሬዲነስ ኢኒሼቲቭ (ኢ.ስ.ሬ.ኢ) ለ2019 በጀት ዓመት በ8 ክልሎች ለሚገኙ በፕሮጀክት ለታቀፉ የመንግሥት አፀደ ሕፃናት እና መምህራን ኮሌጆች ለት/ት አሰጣጥ ጥራት ድጋፍ የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ቁሳቁሶች ብቁ እና ሕጋዊ የሆኑ አቅራቢዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ስኩል ሬዲነስ ኢኒሼቲቭ (ኢ.ስ.ሬ.ኢ) ለ2019 በጀት ዓመት በ8 ክልሎች ለሚገኙ በፕሮጀክት ለታቀፉ የመንግሥት አፀደ ሕፃናት እና መምህራን ኮሌጆች ለት/ት አሰጣጥ ጥራት ድጋፍ የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ቁሳቁሶች ብቁ እና ሕጋዊ የሆኑ አቅራቢዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

  1. ICT, MULTIMEDIA & NETWORKING EQUIPMENT
  2. FURNITURE & CLASSROOM SUPPORT EQUIPMENT (open shelf, production table, wall-mounted pegboard, etc.)
  3. STATIONERY & OFFICE SUPPLIES
  4. CREATIVE & ART MATERIALS (Die-Cut Machine for Shapes and Letters, Hot Glue Gun, etc )
  5. OUTDOOR PLAY & PLAYGROUND EQUIPMENT (sea saw, slide, swings, merry-go- round & sand box

በዚሁም መሠረት ተጫራቾች በአዲስ አበባ ከተማ ለቡ በሚገኘው የኢስሬኢ ቢሮ በመቅረብ የጨረታ ሠነዱን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3:00 እስከ 10:00 ሠዓት በመምጣት የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) እየከፈሉ መውሰድ ይችላሉ፡፡ በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች፡-ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ ሠርተፍኬት እና የወቅቱን ግብር የከፈሉበትን ኮፒ አብረው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት የአቅራቢነት /Supplier/ መመዝገባቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣ የቫት ምዝገባ የምስክር ወረቀትና የባለፈው ወር የቫት ዲክላሬሽን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣ የሚወዳደሩበት የመነሻ ጠቅላላ ዋጋ 2% በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የጨረታ ዋስትና ከታወቀ ተቋም ወይም ከባንክ የተሰጠ የተረጋገጠ ቼክ (CPO) ማቅረብ የሚችል፣ ድርጅታቸው በተመሳሳይ ዘርፍ የተሰማሩበትን አጠቃላይ የሥራ ልምድ ከሶስት የተለያዩ ድርጅቶች የሥራ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው ይህ ሣይሆን ቢቀር ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከውድድር ይሠረዛሉ፡፡ ተጫራቾች በገዙት ኦርጅናል የጨረታ ሠነድ ላይ በግልጽ መሙላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

  1. ተወዳዳሪዎች የምታቀርቡትን ሰነድ በአንድ ፖስታ በማሸግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3:00 እስከ 10:00 ሠዓት ድረስ በኢትዮጵያ ስኩል ሬዲነስ ኢኒሼቲቭ ዋና ቢሮ በመገኘት ማስገባት ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች ትክክለኛ አድራሻቸውንና ስማቸውን በታሸገው ኤንቬሎፕና በመጫረቻ ሰነዳቸው ላይ በመፈረም ማስቀመጥ አለባቸው፡፡
  3. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በተዘጋ ባለው የሚቀጥለው የሥራ ቀን በ3:00 ሰዓት በኢትዮጵያ ስኩል ሬዲነስ ኢኒሼቲቭ ቢሮ ይከፈታል፡፡ ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- ለቡ መብራት ኃይል ጋራ ማርት ፊት ለፊት አሳክ ህንጻ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 304/4
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0912037450/0913594852 መደወል ይቻላል፡፡

የኢትዮጵያ ስኩል ሬዲነስ ኢኒሼቲቭ

✨ messages.ai_summary
Ethiopia School Readiness Initiative seeks bids for ICT/multimedia/networking equipment, furniture and classroom support equipment, stationery, creative/art materials, and outdoor play equipment for government kindergartens and teachers' colleges in 8 regions. Bidders must submit renewed business license, tax payment proof, supplier registration, VAT certificate and declaration, and experience letters from three organizations.
Save Tender