የሸኖ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ለሸኖ ፖሊ. ቴክኒክ ኮሌጅ እና ለተለያዩ መ/ቤቶች Construction, ICT & Electronics, Automotive, Metal and welding, Electrical material እና የህትመት ዉጤቶች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በኦሮሚያ ክልል የሸኖ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- ግ/ጨ/ቁ 02/2019
የሸኖ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በኦሮሚያ የስራ ዕድል ፈጠራ እና ሙያ ቢሮ ለሸኖ ፖሊ. ቴክኒክ ኮሌጅ እና ለተለያዩ መ/ቤቶች የተለያዩ፡-
- Construction material
- ICT & Electronics Material
- Automotive material
- Metal and welding material
- Electrical electronics
- Material for BEI
- የተለያዩ የህትመት ዉጤቶች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡
ስለዚህ በየስራ ዘርፉ የዘመኑን ግብር የከፈላችሁ፤ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላችሁ፤የተጨማሪ እሴት ታክስ VAT 15% ተመዝጋቢ የሆናችሁ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN ያላችሁ እና በአቅራቢዎች ዝርዝር ዉስጥ የተመዘገቡ ለመሆናቸዉ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ዉስጥ በሸኖ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በግንባር በመቅረብ ዝርዝር መጠይቆችን የያዘውን ሰነድ በማይመለስ በብር 800 በካሽ መግዛት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ በዝርዝር የተመለከተውን የጨረታ ማስከበርያ ዋስትና በካሽ ወይም ሲፒኦ "CPO ማስያዝ አለባቸው፡፡
ተጫራቾች በተዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒ በማያዝ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ በ16ኛው ቀን እስከ 8:00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በዚሁ እለት በ8:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮች በተገኙበት ይከፈታል።
ማሳሰቢያ፡-
ጨረታውን ያሸነፈ ድርጅት ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ ውሉን ፈጽሞ እቃዎችን የማስገባት ግዴታ አለበት።
መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ (አማራጭ) ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ በሚወስደው መንገድ 78 ኪሎ ሜትር ሸኖ ከተማ ነው፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0910 093362 በመደወል ጠይቆ መረዳት ይቻላል፡፡
