በደቡባዊ ሲዳማ ዞን ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ የቢሮ መገልገያ ዕቃ ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡባዊ ሲዳማ ዞን ፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ
የቢሮ መገልገያ ዕቃ ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡባዊ ሲዳማ ዞን ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት የቢሮ መገልገያ ዕቃ ማለትም ሎት 1 የጽሕፈት መሳሪያዎችን ሎት 2 የኤሌክትሮኒክስ ሎት 3 ፈርኒቸር እና ሎት 4 የለል ምንጣፍ ግዥ በጨረታ ዋጋ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ተጫራቾች -
- አግባብነት ያለው ህጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያለው/ያላት ኦርጅናል ፎቶ ኮፒ አያይዞ ማቅረብ የሚችል
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው እና የዘመኑን ወይም 2019 ዓ.ም ግብር የከፈሉበት ማረጋገጫ ያለው/ያላት ኦሪጅናል ፎቶ ኮፒ አያይዞ ማቅረብ የሚችል፡፡
- የ2018 ዓ.ም የግብር ክሊራንስ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል የምትችል፡፡
- የቫት ተመዝጋቢ የሆነ እና በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ያለው/ያላት ኦሪጅናል ፎቶ ኮፒ አያይዞ ማቅረብ የሚችል፡፡
- ጊዜው ያላለፈበት በአቅራቢነት በጨረታ ላይ እንዲሳተፉ ከመንግስት መ/ቤት የተሠጠ ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ያለው/ያላት ኦሪጅናል ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችል
- የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ ብር 30,000 ከታወቀ ባንክ /CPO/ማስያዝ የሚችል፡፡
- የውል አፈፃፀም ዋስትና ማስከበሪያ ከሚያቀርበው ጠቅላላ ዋጋ 10% በጥሬ ወይም ከታወቀ ባንክ የተሰጠ CPO/ማስያዝ የሚችል፡፡
- ማንኛውንም ወጪዎች ማለትም የጉምሩክ የትራንስፖርት የባንክ እና የሌሎች አገልግሎት ወጪዎችን በራስ ሸፍኖ ዕቃውን ማስረከብ የሚችል
- ተጫራቾች የሚጫረቱባቸውን ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የዕቃውን ዝርዝር ወይም ስፔስፍኬሽን በተዘጋጀው የጨረታ ሠነድ ላይ መመልከት ይችላሉ፡፡
- በጨረታው ተሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች ያቀረቡት ናሙና ወዲያው ተመላሽ ይደረጋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 400/አራት መቶ ብር/ በደቡባዊ ሲዳማ ዞን ፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ በመክፈል እና ሰነዱን በደቡባዊ ሲዳማ ዞን ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ግዥ ሥራ ሂደት ቢሮ በመውሰድ በተዘጋጀው የጨረታ ሠነዱ ላይ የአንዱን ዋጋ ብቻ ቫትን አካቶ በመሙላት ቴክኒካል ዶክመንትን እና ፋይናንሻል ኦርጅናል እንዲሁም ሁለት ሁለት ፎቶ ኮፒውን ለየብቻ በማድረግ በአንድ ፖስታ አሽጎ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በደቡባዊ ሲዳማ ዞን ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ግቢ ውስጥ ባለው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየገለጸን የጨረታ ሳጥን በ11ኛው ቀን ከቀኑ 8:30 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚው ቀን ከቀኑ 9:00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
ማሳሰቢያ፡-
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ለመግዛት ሲመጡ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ኮፒና ማመልከቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- መምሪያው በጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አንድ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ሌላው ተጫራች ተንተርሶ መጫረት አይችልም፡፡
- የወቅቱን የገበያ ዋጋ ያላገናዘበ የጨረታ ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- ጨረታው መከፈቻ በሥራ ቀን ካልዋለ በቀጣይ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ይሆናል፡፡
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡባዊ ሲዳማ ዞን ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ
✨ messages.ai_summary
Procurement of office supplies in four lots: stationery, electronics, furniture, and carpet. Bidders must hold a valid renewed business license, TIN, VAT registration, tax clearance, and a supplier certificate, submit item samples, and cover all delivery costs.
