በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ቃሊቲ 2ኛ ደ/ት/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በግልጽ ጨረታ አወዳድረው መግዛት ይፈልጋል፡፡
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የቃሊቲ 2ኛ ደረጀ ት/ቤት
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ቃ/ሁ/ደ/ት/ቤት ግ/ጨ 001/2019
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ቃሊቲ 2ኛ ደ/ት/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በግልጽ ጨረታ አወዳድረው መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሠረት፦
- የደንብ ልብሶች 2.አላቂ የፅዳት ዕቃዎች 3.የቢሮ የፅህፈት መሳሪያዎች 4.ቋሚ ዕቃዎች 5.የጥገና፣ የቧንቧ እና የኤሌክትሪክ ዕቃዎች 6.የህትመት ስራዎች 7.የተለያዩ የላብራቶሪ ሬኤጀንቶች፣ መድሀኒቶች እና የህክምና መገልገያ መሳሪያዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በዚህ ጨረታ ላይ መሳተፍ የሚፈልግ ድርጅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያወጡና የተሰጣቸው ንግድ ፈቃድ 1(አንድ) ዓመት የሞላው ከሆነ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN No) ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በወጣው ጨረታ ላይ መሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00(ሶስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10(አስር) የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 2:30 እስከ 6:30 እና ከሰዓት ከ7:30 እስከ 11:30 ቢሮ ቁጥር 8 የግዥና ንብረት አስተዳደር ክፍል በአካል በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- መ/ቤቱ ለሚገዛቸው ዕቃዎች ማለትም በጨረታ ሰነዱ ላይ በክፍል 6 ላይ የተዘረዘሩትን የዕቃዎችና ተያያዥ አገልግሎቶች ዝርዝር መግለጫ ላይ ናሙና/ሳምፕል/ እንድታቀርቡ በተጠየቀው መሠረት የተጠየቁትን ናሙና/ሳምፕል/ የጨረታ ሳጥኑ ከመከፈቱ በፊት ቢሮ ቁጥር 8 የግዥ የስ/ሂደት እንድታስገቡ እየገለጽን ናሙና (ሳምፕል) ያልቀረበባቸው እቃዎች ውድቅ እንደሚሆኑባችሁ እውቃችሁ ለምትወዳደሩበት እቃዎች በሙሉ ናሙና(ሳምፕል) እንድታቀርቡ እያሳሰብን የምታቀርቡትን ናሙና/ሳምፕል/ በተመለከተ ት/ቤቱ የራሱን ኮድ ናሙና(ሳምፕል) የሚሰጥ በመሆኑ በምታቀርቡት ናሙና/ሳምፕል ላይ የድርጅታችሁን ስም መጻፍ ወይም መለጠፍ በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡ በተጨማሪም ከጽዳት ዕቃዎች በረኪና፣ ዲቶል ፣ከቢሮ የጽህፈት መሳሪያዎች መካከል እርሳስ፣ እስኪርብቶ፣ ፍሉድ፣ ሉሁ፣ ማርከር እና የማሁተም ቀለም የቃሊቲ 2ኛ ደ/ት/ቤት የጥራት ኮሚቴው ዕቃዎቹን ከፍቶ ጥራቱን የሚፈትሽ/የሚመረምር/ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት /ለሚያቀርቡት/ የላብራቶሪ መገልገያ፣ ጀነሬተር፣ላፕቶፕ ሌሎች መሳሪያዎች የሚገልጽ ማንዋል ወይም ዝርዝር መረጃ ከጨረታው ሠነዱ ጋር ተያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን እና ደጋፊ ማስረጃቸውን የሚያዘጋጁበት ቋንቋ በአማርኛ መሆን ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ዕቃ የጠቅላላ ዋጋ በሎት 6211-54,875.00 ብር ፣ 6212-25,113.00 ብር ፣ 6213-6,000.00 ብር፣ 6214-3,900.00 ብር 6215-22,159 ብር፣ 6218-29,060.00 ብር ፣6219-9,242.00 ብር፣ 6223-2,000.00 ብር፣ 6313--80,000.00/ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ CPO ከጨረታ ሰነዱ ጋር በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡
- ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ በተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ መስጠት የተከለከለ ሲሆን ነገር ግን ይህ ሆኖ ቢገኝ ከጨረታ ውጪ ይሆናሉ፡፡
- የጨረታው ዋጋ ለ2ወር ጸንቶ ይቆያል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን በሚመለከት አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ ማቅረብ አለባችሁ፡፡
- ተጫራቾች በተሰጣቸው የዋጋ መሙያ ሠነድ ላይ ምንም ዓይነት ስፔስፊኬሽን መጨመርም ሆነ መቀነስ አይችሉም፡፡
- ተጫራቾች የወሰዳችሁትን የጨረታ ሰነድ ሙሉ በሙሉ ሳይገነጣጠል ተመላሽ የምታደርጉ ሲሆን በጨረታ ሰነዱ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ ስነድ ት/ቤቱ የማይቀበልና ከውድድር ውጭ የሚያደርግ መሆኑን ይገልጻል፡፡
- የጨረታ መዝጊያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡ በተጨማሪም ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጭ ሆነው ለወደፊቱም በመንግስት ግዥ እንዳይሳተፉ ይደረጋሉ፡፡ እንዲሁም ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ይወረስባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዕቃ በመለየትና በፖስታው ላይ በመግለጽ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ቃሊቲ 2ኛ ደ/ት/ቤት ግቢ ቢሮ ቁጥር 8 ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት ውስጥ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን የጨረታ ሳጥኑ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ታሽጎ በእለቱ 4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ጨረታው በሚከፈትበት ቦታ፣ ቀንና ሰዓት በራሳቸው ምክንያት ባይገኙ የጨረታ ሳጥኑ እንዲከፈት በማድረግ ውድድሩ ይካሄዳል፡፡
- በጨረታው ላይ ሁለት እና ከሁለት በላይ የሆኑ እጩ ተወዳዳሪዎች በግምገማው እኩል ውጤት ካቀረቡ ቅድሚያ ለሀገር ውስጥ አምራች ለሆኑ ዕድሉን የምንሰጥ ሲሆን አምራች ተወዳዳሪ ካሌለ አሸናፊውን ለመለየት አብላጫ ኢታዎችን ላሸነፈው እድሉን እንሰጣለን፡፡
- የጨረታ ውጤቱ ይፋ ሆኖ አሸናፊና ተሸናፊ ተጫራቾች እንደተለዩ በማስታወቂያ ላይ ከተገለጸ በኋላ ተሸናፊ ተጫራቾች ያስያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ የይመለስልኝ ደብዳቤ በመጻፍ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡ አሸናፊ ተጫራች ግን የውል ስምምነት እንዲፈጸም በተገለጸው ጊዜ ውስጥ ከአሸነፈበት ዕቃ/አገልግሎት/ ጠቅላላ ዋጋ 10% የግገር የውል ማስከበሪያ ሲያስይዙ ቀደም ብለው ያስያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ 2% ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
- ገገርው መ/ቤት በጨረታ ማስታወቂያ የተጠየቀውን ዕቃ ካቀረበው መጠን /ብዛት/ላይ 20% ከውል በፊት የመጨመርና የመቀነስ መብት አለው፡፡
- አቅራቢው በገባው የውል ስምምነት መሰረት የዕቃውን ዓይነት፣ መጠን እና ጥራት ጠብቆ በውሉ ላይ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ካላቀረበ የግገር ፈጻሚ መ/ቤቱ በጨረታ ሰነዱ በክፍል 8 በልዩ የውል ሁኔታዎች ላይ በተገለጸው መሠረት አሸናፊ ተጫራች ካሸነፈው ጠቅላላ ዋጋ ላይ 0.01% በየቀኑ ዕቃውን እስከሚያስረክብበት ቀን ድረስ ተቀናሽ ሆኖ ለመስሪያ ቤቱ የጉዳት ካሳ ገቢ ይሆናል፡፡ በተጨማሪም አቅራቢው ያሸነፈበትን ዕቃ ፈጽሞ ካላቀረበ ያስያዘው የውል ማስከበሪያ 10% መ/ቤቱ ይወርሳል፡፡
- በግገር ፈጻሚ እና በአቅራቢው መካከል የተለየ ስምምነት ከሌለ በስተቀር የተያዘው የውል ማስከበሪያ ዋስትና አቅራቢው ግዴታውን ሙሉ በሙሉ እንደተወጣ ሲረጋገጥ ወዲያውኑ ተመላሽ ይደረግለታል፡፡
- በጨረታ ሂደቱ ላይ ጉዳት ደርሶብኛል ወይም በጨረታ ግምገማ ውጤት ላይ ቅር የተሰኘ ማንኛውም ተጫራች ጨረታው በድጋሚ እንዲታይለት የጨረታ ውጤት ይፋ ሆኖ በማስታወቂያ ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ቅሬታውን በግገር ፈጻሚ መ/ቤት የበላይ ኃላፊ በጽሁፍ ቅሬታውን ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ ሆኖም በተሰጠው ቀናት ውስጥ ቅሬታውን ሳያቀርብ ቀርቶ ቀነ ገደቡ ካለፈ በኋላ የሚመጣ ቅሬታ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- በውድድር ወቅት በአንዱ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ መካከል ልዩነት ቢኖር በአንዱ ዋጋ መሰረት እና በአሃዝና በፊደል በሚገለጽበት ወቅት ልዩነት ቢኖር በፊደል በተገለጸው መሰረት በማስተካከል ይገመገማል፡፡
- ተጫራቾች ያቀረቡት ናሙና/ሳምፕል/ በሚመረመርበት ወቅት በራሱ ተፈጥሮ ቢጠፋ ወይም ቢበላሽ መ/ቤቱ ካሳ አይከፍልም፡፡
- ያቀረቡት ናሙና የጨረታ ውጤት ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 60/ስልሳ/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ እንዲወስዱ ተገልጾላቸው ጠይቀው ካልወሰዱ ለመንግስት በውርስ ገቢ ይደረጋል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቧቸውን ዕቃዎች እስከ መ/ቤቱ መጋዘን ድረስ በራሳቸው ትራንስፖርት/ወጪ/ በማጓጓዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪም የሚያቀርቡት የዕቃ አይነት ተገጣጣሚ ከሆነ በራሳቸው ወጪ ገጣጥመው ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታው ሠነድ ላይ ግልጽ ያልሆኑ ጉዳዮች አስመልክቶ ማብራሪያ ቢያስፈልጋችሁ በጽሁፍ ቃሊቲ 2ኛ/ደ/ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 8 በአካል በመምጣት ማቅረብ /መጠየቅ/ ትችላላችሁ፡፡
- ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ቃሊቲ 2ኛ ደ/ት/ቤት
✨ messages.ai_summary
Kaliti 2nd Primary School seeks suppliers for uniforms, cleaning supplies, office stationery, furniture, maintenance/plumbing/electrical items, printing, and laboratory reagents, medicines and medical equipment. Bidders need a valid/renewed business license, TIN, VAT registration, supplier registration, Amharic documents, and samples; the school may adjust quantities by 20%.
