በአቃቂ ክ/ከተማ በወረዳ 9 ስር የሚገኘው ቂሊንጦ ቁ.2 የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ለትቤቱ አገልግሎት የሚውሉ እቃዎችን በየሎቱ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በአ/ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 09 ትምህርት ጽ/ቤት ቂሊንጦ ቁ.2 ቅድመ አንደኛና አንደኛ ደረጃ ት/ቤት
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥመለያቁጥር 001/2019
በአቃቂ ክ/ከተማ በወረዳ 9 ስር የሚገኘው ቂሊንጦ ቁ.2 የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ለትቤቱ አገልግሎት የሚውሉ እቃዎችን በየሎቱ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ስለሆነም ለየሎቱ ሲ.ፒ.ኦ በማስያዝ ማቅረብ የምትችሉ ተጫራቾች ከዚህ በታች ያሉትን እያንዳንዱ መረጃ/ መስፈርቶች/በጥንቃቄ ትኩረት ሰጥታችሁ በማንበብ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን ፡፡
- ሎት 1. 6211/ የደንብ ልብስ - 30000.00 ብር
- ሎት 2. 6212/ አላቂ የቢሮ ዕቃ- 20000.00 ብር
- ሎት 3. 6214/ አላቂ የህክምና እቃ 15,000.00 ብር
- ሎት 4. 6215/ አላቂ የትምህርት ዕቃ- 20,000.00 ብር
- ሎት 5. 6218/ አላቂ የፅዳት ዕቃ - 35,000.00 ብር
- ሎት 6. 6219/ ልዩልዩ እቃዎች - 10,000.00 ብር
- ሎት 7. 6313/ ቋሚ እቃ -40,000.00 ብር
- በዘርፉ የተሰማሩበት የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ እና ቲንነር /TIN NO/ ያላቸው፡፡
- የዘመኑ ግብር የከፈሉና በአቅራቢዎች ስም ዝርዝር ላይ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልጽ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ/ ከላይ በተጠቀሱት የሎት አይነቶች መሰረት ከጨረታ ሰነድ ጋርአያይዘው ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበት፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ የማይመለስ 400.00/አራት መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በት/ቤቱፋይናንስ ቢሮ ቁ.3 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/ አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነዱን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒውን በመለየት ህጋዊ የድርጅት ማህተማቸውን በማድረግበፖስታ በማሸግ ትሌቱበዘጋጀው የጨረታሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የሚዘጋው በጋዜጣ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን በስራ ቀናት ውስጥ በ4:00ሰአት ይሆናል፡፡እንዲሁም ጨረታው የሚከፈተው በዚሁ ዕለት4:30 ይሆናል፡፡
- የጨረታውአሸናፊ ያሸነፈውን ዕቃ በሚደረገው የውል ስምምነት መሰረት በራስትራንስፖርትቂሊንጦ ቁ.2 የመጀ/ደ/ትቤትማሪሚያ ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለሚያቀርቧቸው ዕቃዎች ጨረታ ከመክፈቱ በፊት የጨረታ ሰነድ ስትመልሱ ከእያንዳንዱ አላቂና ቋሚ እቃዎችን በመለየት ናሙና /ሳምፕል/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡ ፡በተጨማሪ-መምጣት የማይችሉ ከባድ እቃዎችንበመለየት በፎቶ ከነስፔስፊኬሽኑ እንዲታቀርቡልን እናሳስባለን ፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው በሚከፈትበት ሰአት ተጫራቾቸውይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፡፡
- የጨረታ አሸናፊ ሆነው ከተገኙ በኋላ10% /አስር /ፐርሰንት ባሸነፉበት ዕቃ መሰረት የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በምትጫረቱባቸው እቃዎች ላይ መ/ቤቱ 20% የመጨመርም የመቀነስም መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ዋጋ ዝርዝር ስትሞሉ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ ፣ በፍሉድ የጠፋ፣የተነካካ የዋጋ ዝርዝር እንዳይኖር እና በተለያ የእጅ ጽሁፍ፣የተለያ ፊርማ አወዛጋቢ የዋጋ መሙያ ከውድድር ውጪ እንደሚያደርግ ከወዲሁ እናሳስባለን፡፡
- ተጫራቾች በምታቀርቡት ናሙና /ሳምፕል/ ላይ ምንም አይነት የድርጅት ማህተም ፣ስልክ ቁጥር እና ሌሎች ምልክት ካለባቸው ከውድድር ውጪ የሚደረግ መሆኑን እንገልጸለን ፡፡
- ለጥቃቅንና አነስተኛ ተጫራቾች በሀገር ውስጥ ምርት ብቻ መወዳደር ይችላሉ ፡፡ነገር ግን የሀገር ውስጥ ምርት ካልሆነ እንደማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ መግዛት እና ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል ፡፡ስለሆነም የዋስትና ደብዳቤ የማንቀበል መሆኑን ከወዲሁ እንገልጻለን
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-09-20198347/0913-641182 ብለው ይደውሉ፡፡
አድራሻ፡- ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ፊት ለፊት ያለው ት/ቤት
በአቃቂ ክ/ከተማ በወረዳ 9 ስር የሚገኘው ቂሊንጦ ቁ.2 የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት
✨ messages.ai_summary
Qilinto No. 2 Primary School in Akaki Sub-city, Woreda 9, seeks bidders to supply goods for school use across seven lots: uniforms, consumable office, medical, educational and cleaning supplies, miscellaneous items, and fixed assets. Bidders need a renewed business license, TIN, tax compliance, VAT registration, and must submit samples.
