ድርጅታችን የሶፍት ዋተር ማከማቻ ታንከር (40,000 Liter Stainless Steel Soft Water Storage Tank) ሥራ የሚሰራ ድርጅት በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
National Alcohol and Liquor Factory (ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 003/2019 ዓ.ም
ድርጅታችን የሶፍት ዋተር ማከማቻ ታንከር (40,000 Liter Stainless Steel Soft Water Storage Tank) ሥራ የሚሰራ ድርጅት በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች -
- የታደሰ የንግድ ፍቃድና የዘመኑን ግብር ለመከፈላችሁ መረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
- የማይመለስ ቫትን አካቶ በብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሠነዱን መካኒሳ በሚገኘው ዋናው መ/ቤት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 308 በመቅረብ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፤
- ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ሰነድ ኦሪጅናል እና ፎቶ ኮፒ ለየብቻው በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የሚቀርበው ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለመሆኑ በግልጽ መቀመጥ አለበት፤
- ለጨረታ ዋስትና የሚሆን የሚያቀርቡትን አጠቃላይ ዋጋ 2% በሲፒኦ ለብቻው በኢንቨሎፕ በማሸግ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፤
- ተጫራቾች የሚያስገቧቸውን ሠነዶች ጥቅምት 19 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሠዓት መካኒሳ በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ግዥ ቢሮ 5ኛ ፎቅ ቁጥር 503 ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዚያው ዕለት ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ፖ.ሣ.ቁ. 3516
ፋክስ 011 5 513299
Addis Ababa
Ethiopia
ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ
✨ messages.ai_summary
The National Alcohol and Liquor Factory seeks a qualified firm to supply and install a 40,000-liter stainless steel soft water storage tank. Bidders must submit renewed business license and tax compliance evidence, with separate sealed financial and technical documents stating VAT inclusion.
