Tender Detail

Tender Details

  • Company የደ/ምዕ/ኢት/ያ ሕ/ክ/መ/ግብርና ቢሮ የሚዛን ገጠር ቴክኖሎጂ ማስፋፊያ ማዕከል
  • Address , Phone: 0913855054
  • Website
  • Deadline11 Nov 2026, 5:30 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100(አንድ መቶ ብር)
  • Bid Securityለጣውላ ጨረታ 5000 /አምስት ሽህ ብር ብቻ/; የሕንፃ መሣሪያ ጨረታ 1000 /አንድ ሽህ ብር ብቻ/; የብረታ ብረት ጨረታ 1000 /አንድ ሽህ ብር ብቻ/; የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ጨረታ 800 /ስምንት መቶ ብር/ብቻ; ለፈርኒቸር ግዥ ጨረታ 800 /ስምንት መቶ ብር/ ብቻ
  • opening dateተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ተኛው ቀን 3:30 ሰዓት በመሥሪያ ቤቱ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
  • Categories Building Materials , Wood And Wood Working , Metals And Metal Working

በደቡብ ምዕራብ/ኢት/ሕዝ/ክ/መ/ግብርና ቢሮ የሚዛን ገጠር ቴክኖሎጂ ማስፋፊያ ማዕከል በ2019 በጀት ዓመት ለሚያመርታቸው ምርቶች አገልግሎት የሚውሉ በካፒታል እና በመደበኛ በጀት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

የደ/ምዕ/ኢት/ያ ሕ/ክ/መ/ግብርና ቢሮ የሚዛን ገጠር ቴክኖሎጂ ማስፋፊያ ማዕከል


ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ምዕራብ/ኢት/ሕዝ/ክ/መ/ግብርና ቢሮ የሚዛን ገጠር ቴክኖሎጂ ማስፋፊያ ማዕከል በ2019 በጀት ዓመት ለሚያመርታቸው ምርቶች አገልግሎት የሚውሉ በካፒታል እና በመደበኛ በጀት

  • ሎት 1. የተለያዩ መጠን ያላቸው የሀገር ውስጥ ጣውላዎች ጥድ
  • ሎት 2. የሕንፃ መሣሪያዎች
  • ሎት 3. የተለያዩ ብረታ ብረቶች
  • ሎት 4. የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
  • ሎት 5. የቢሮ ወንበሮች

በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተለውን መስፈርት ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

  1. ተጫራቾች የተሰማሩበትን የሥራ ዘርፍ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN NO) ያላቸው
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ የሆኑ
  4. ተጫራቾች የተሠማሩበት የሥራ ዘርፍ ጋር በተያያዘ ለተሰማሩበት የሥራ ዘርፍ በሚመለከተው አካል የተሰጠው የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
  5. ተጫራቾች ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ከታወቀ ባንክ የሚሰጥ የተረጋገጠ የከፍያ ማዘዣ ቼክ፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም የተረጋገጠ ሌተር አፍ ክሬዲት ለሚዛን ገጠር ቴክኖሎጂ ማስፋፊያ ማዕከል በማለት ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
    • ለጣውላ ጨረታ 5000 /አምስት ሽህ ብር ብቻ/
    • የሕንፃ መሣሪያ ጨረታ 1000 /አንድ ሽህ ብር ብቻ/
    • የብረታ ብረት ጨረታ 1000 /አንድ ሽህ ብር ብቻ/
    • የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ጨረታ 800 /ስምንት መቶ ብር/ብቻ
    • ለፈርኒቸር ግዥ ጨረታ 800 /ስምንት መቶ ብር/ ብቻ
  6. የጨረታ አሸናፊ የሚሆነው ተጫራች ያሸነፈባቸውን ጥራትና ደረጃን የጠበቀ እቃዎች እስከ ግዥ ፈጻሚው መሥሪያ ቤት ድረስ በራሳቸው ወጪ በተገባው ውል መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. የተጫራቾች ስለጨረታው ሙሉ ዝርዝር ሁኔታ የያዘ የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣ ቀን ጀምሮ ለ15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ ብር/በመክፈል በተቋሙ ግዥና ክፍያ ንብረት አስተዳደር የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 9 ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይቻላል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ማስታወቂያው ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን ባሉት ተከታታይ የሥራ ቀናት በሥራ ሰዓት ከ2:30 እስከ 11:30 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 9 በመቅረብ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር በ15ተኛው የሥራ ቀን 11:30 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ተኛው ቀን 3:30 ሰዓት በመሥሪያ ቤቱ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
  10. መሥሪያ ቤቱም የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ይሁን ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0913855054 ወይም 0913651440 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  12. በጨረታው ማስታወቂያ ላይ የትርጉም ለውጥ ቢኖር በጨረታው ሰነድ የተገለጸው ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡

የሚዛን ገጠር ቴክኖሎጂ ማስፋፊያ ማዕከል /ሚዛን አማን/

✨ messages.ai_summary
The Mizan Rural Technology Promotion Center seeks suppliers for five lots: local timber planks, building tools, various metals, electronics, and office chairs. Bidders must hold a valid business license, TIN, VAT registration, and a supplier certificate.
Save Tender