የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ CCTV CAMERA ግዥ እና ገጠማ ስራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Oromia Seed Enterprise (የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ)
ድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር OSE/NCB/006/2019
የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ CCTV CAMERA ግዥ እና ገጠማ ስራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም አስፈላጊውን መስፈርት የምታሟሉ በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፤
ተጫራቾች፡-
- የንግድ ምዝገባ ሰርቲፊኬት
- የዘመኑን የታደሰ ንግድ ፈቃድ
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፊኬት
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin No)
- የአቅራቢነት ማስረጃ(Supplier list)
- የሚፈለግባቸውን የመንግሥት ግብር ስለመወጣታቸው የሚገልጽ ማስረጃ፣ ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው፡፡
ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ፡- ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ በመዋል በ16ኛው ቀን የሚዘጋ እና የሚከፈት ይሆናል፡፡ የጨረታ ሰነድ መግዣ ዋጋ ብር 200.00(ሁለት መቶ) መሆኑን እየገለጽን፣ ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸውን በፖስታ በማሸግ በተጠቀሰው ቀን ከጠዋቱ 2፡30-8፡00 ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት በጨረታው እንድትሳተፉ እንጋብዛለን፡፡
የጨረታ ሳጥኑ በዕለቱ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢንተርፕራይዙ ዋና መ/ቤት ጎተራ አጎና ሲኒማ አጠገብ ባለኤር ህንፃ /Baleker Tower /4 ፎቅ ላይ በሚገኘው የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ ቢሮ ቁጥር 402 ይከፈታል፡፡
ኢንተርፕራይዙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኢንተርፕራይዙ የሥራ ሰዓት፡- ከሰኞ-አርብ ጠዋት ከ2፡30-6፡30 ከሰዓት በኋላ ከ7፡30-11፡30 ነው፡፡
ለበለጠ ማብራሪያ፡- ስ.ቁ 011-416 03 09/011-466-25-27 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
